በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ቡድኑን አንደ አዲስ እያዋቀረ ሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ሶሆሆ ሜንሳህን ከሃዋሳ በአንድ ዓመት ውል ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል።
ባሳለፍነው ዓመት ከሃዋሳ ከተማ ጋር ያሳለፈው ቶጋዊው ግብ ጠባቂ የወልቂጤ ከተማ የክረምቱ 17ተኛ ፈራሚያቸው መሆን ችሏል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከተክለማርያም ሻንቆ ጋር አየተፈራረቀ የሀይቆቹን የግብ ክልል የጠበቀው ሜንሳህ መቼ አንደሚጀምር በማይታወቀው የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አዳጊዎቹን ወልቂጤ ከተማን በልምዱ ሊያግዛቸው አንደሚችል ይገመታል።