የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከአውሮፓውያን ተጫዋቾች አልፎ የአፍሪካውያን ተጫዋቾችን በማጥቃት ላይ ይገኛል ::
ከዚህ ቀደም ሁለት ተጫዋቾች በቫይረሱ ሲያዙ ሶስተኛ ተጫዋች መያዙን መረጃዎች ያሳያሉ ::
በቫይረሱ በቀዳሚነት ከአፍሪካውያን ተጫዋቾች የተያዘው በቱኒዚያው ሊግ ለቤን ጉርዴን ክለብ በፊት መስመር አጥቂነት የሚጫወተው ኦማር ዘክሪ ነው ::
- ማሰታውቂያ -
በጉዙፉ እና ከባዱ የአፍሪካ ሊግ ኦርላንዶ ፓይሬትስ የሚጫወተው የመሀል ሜዳ ተጫዋች ቤን ሞትሽዋሪ በቫይረሱ የተያዘ ሁለተኛው ተጨዋች መሆኑ ይታወሳል ::
ዛሬ በወጣ መረጃ መሰረት ለሊቢያው ሊግ አል ኩምስ ክለብ በግብ ጠባቂነት የሚጫወተው አህመድ ቤሪሽ ሶስተኛው በቫይረሱ የተያዘ ተጫዋች መሆኑ ተገልጿል ::