ከኢንግሊዛዊው ስቲዋርት ሃል ጋር የከተለያዩ በኃላ አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ ተጠምደው የነበሩት ፈረሰኞቹ ሰርቢያዊውን ሰርዲያን ዚቮንጆቭን በዋና አሰልጣኝነት መቅጠራቸውን ዛሬ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቀዋል።
ከዚህ ቀደም የታንዛንያውን ያንግ አፍሪካን እና የዩጋንዳውን ቪላ ክለብ ማሰልጠን የቻሉት ሰርዲያን በሚቀጥሉት ቀናት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሚጀምሩ ይሆናል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰርዲያን ዚቮንጆቭን መቅጠሩን ተከትሎ በታሪካቸው የቀጠርዋቸውን ሰርቢያውያን አሰልጠኞች ቁጥር ሥስት ማድረስ ችለዋል።ከዚህ ቀደም ፈረሰኞቹ በሰርጂዮቪች ሚቾና በኮንዲክ ዱሳን መመራታቸው ሚታወስ ነው።