ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነቱን አረጋገጠ
28ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞኞች ተካሂደዋል።
የሊጉ ባለ ክብረወሰን ቅዱስ ጊዮርጊስም የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናገዱት ፈረሰኞች፥ በአዳነ ግርማ የ68ኛ ደቂቃ ጎል 1 ለ 0 መሸነፍ ችለዋል።
የዛሬውን ውጤት ተከትሎም ሊጉን ለ14ኛ ጊዜ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ፈረሰኞቹ የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፋቸው ነጥባቸውን 55 ሲያደርሱ፥ ተከታዮቹ ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ጥለዋል።
ደደቢት ዛሬ በመሸነፉ ባለበት 48 ነጥብ ላይ ሲቆም፥ ሲዳማ ቡና አቻ በመለያየቱ ነጥቡን ከደደቢት እኩል 48 አድርሷል።
ተከታዮቹ የቀራቸው ሁለት ጨዋታ ብቻ ሲሆን፥ ጊዮርጊስ ነጥቡን 55 በማድረሱ ቀሪ ጨዋታዎቹን ቢሸነፍም በአንድ ነጥብ ልዩነት ሻምፒዮንነቱን ያስከብራል።
ክልል ላይ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች፥ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናገደው ወላይታ ዲቻ፥ በሜዳው የ 1 ለ 0 ሽንፈትን አስተናግዷል።
ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 93ኛ ደቂቃ ጎሏን አስቆጥራል።
ከጎልዋ መቆጠረ በኃላ በስታዲየሙ ውስጥ ረብሻ ተነስቶ ጉዳት ደርሷል፡፡
በፋሲለደስ ስታዲየም መከላከያን ያስተናገደው ፋሲል ከተማም ጨዋታውን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
ጎሎቹን አብዱራህማን ሙባሪክ በ10ኛና በ34ኛ ደቂቃ ሲያስቆጥር ቴዎድሮስ በቀለ በ46ኛ ደቂቃ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ወልዲያ ላይ ጅማ አባቡናን ያስተናገደው ወልዲያ ከተማ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቋል።
በተመሳሳይ ይርጋለም ላይ የተደረገው የሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታም ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ጨዋታ ሆኗል።
ወደ አዳማ ያቀናው ደደቢት ደግሞ በአዳማ 2 ለ 1 ተሸንፏል፤ ዳዋ ሁቴሳ እና ታፈሰ ተስፋዬ ለአዳማ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ።
የቀድሞውን የኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ ዮርዳኖስ አባይን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን ለመስበር የተቃረበው ጌታነህ ከበደ ለደደቢት የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆጥሯል።
ወደ ድሬዳዋ ያቀናው ሃዋሳ ከተማ በድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በ36ኛው ደቂቃ ሱራፌል ዳንኤል የመሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል
ደረጃ ሰንጠረዥ