ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የአመቱ ኮከብ የተባለው ግብ ጠባቂው አቤል ማሞ እንግዳችን ነው…. ” የሃይማኖትና የብሄሮች መቻቻል የሚታይባት ኢትዮዽያን ማየት እፈልጋለሁ” የሚለው አቤል ለአሰልጣኝ ካሳዬ ያለው ፍቅር ይለያል…
“የምናደንቃቸው አሰልጣኞች ማርሴሎ ቢየልሳና ፔፕ ጋርዲዮላኮ የእርሱን ፍልስፍና ነው ይዘው የመጡት ፤ እነሱን አድንቆ ካሳዬን መርሳት አይቻልም” ሲልም አሰልጣኙ ተገቢውን ክብር አለማግኘቱ ልክ አይደለም ሲል ይሞግታል።
*…የከፍተኛ ሊጎቹ ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የሚደረገውን ፉክክር ዛሬ ጀምረዋል…. ከሶስቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር በእኩል ዓይን ላንታይ እንችላለን የሚል ስጋት ገብቷቸዋል… ውድድሩ ዛሬ ሊጀመር እስከ ትላንት ድረስ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ውድድሩ በሜዳው እንደሚካሄድ አያውቅም…
የዩኒቨርስቲው ሴኪዩሪቲ ስለ ግጥሚያው አላውቅም አላስገባም ብሎ ነበር…
ሀዋሳ ያሉት የፌዴሬሽኑ አወዳዳሪ አካላት የመረጃ ልውውጥ አላደረጉም አንድ የሊግ ካምፓኒው አመራር ጣልቃ ገብቶ ከጉድ አትርፏቸዋል…
- ማሰታውቂያ -
*….የሴካፋ ሻምፒዮና ባህር ዳር ላይ ከቀናት በኋላ ይጀመራል….የኢትዮዽያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አባል የሆነው ሃይሌ ገ/ትንሳኤ ደግሞ “የሴካፋ አዘጋጅ እንደመሆናችን ከጥሩ አጨዋወት ጋር ዋንጫውን ለማንሳት ተዘጋጅተናል” ሲል ፎክሯል።
*….የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በእስራኤል ሙሉ ወጪ ተችሎ እስራኤል መሰንበቱ ይታወቃል…በፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ የተመራው የልኡካን ቡድን ከወዳጅነት ጨዋታዎች ውጪ ወርቃማ የተባለ ስምምነት ተፈራርሟል። ከኮቪድ 19 የተነሳ ግን ኢየሩሳሌምን የማየት ዕድል ሳያገኝ ቀርቷል።
*….ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ባልተለመደ ሁኔታ ለአራት አመታት ዋንጫ ጠፍቷል ኮከቦች ይገባሉ ለውጥ የለም… የቡድኑ አባል የሆነው የአብስራ ተስፋዬ “እንደ ግልም እንደቡድንም ላጣነው ውጤት ተጠያቂ ነን” ሲል ተናግሯል።
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*….. የአውሮፓ ዋንጫው ወደ ወሳኙ ጥሎማለፍ ተሸጋግሯል.. ከውድድሩ ኮከቦች መሃል አንዱ ስለ ሆነው የሶስቱ አናብስት ተስፋ ቡካዮ ሳካ ያዘጋጀው ዘገባ አለ…..
*…ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ መድረክ እየነገሰ ነው….ሪከርድ ሰባሪውና ድል የተራበው ሮናልዶ “እግርኳስ ሁሉንም ነገር ሰጥቶኛል” ሲል ይናገራል…..
*…..የማን.ዩናይትዱ ኮከብ ማርከስ ራሽፎርድ “የእግርኳስ ህይወቴን በኦልድትራፎርድ ማጠናቀቅ እፈልጋለሁ” ሲል ተናግሯል።
*…እድሜ ጠገቡ ኮከብ ጂያንሉጂ ቡፎን “ከዕድሜ ጋር ተያይዞ ብዙ አልጨነቅም አሁንም ድረስ የወጣትነት ስሜት ይሰማኛል” ሲል እድሜው መግፋቱ እንደማያሳስበው ገልጿል…
*….የፈረንሳዩ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ሃገሩን ከጫና ውጪ ለማድረግ ያሰበ ይመስላል…”ፈረንሳይ ለዋንጫ የተሻለ ግምት ቢሰጣትም ዕድሉ ያላቸው አምስት ሀገራት ናቸው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ። ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……