ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን ከቅዱስ ጊዮርጊስ 6 አመታት ቆይታ በኋላ ወደ ፋሲል ከነማ ያቀናውና የሰሞኑ መነጋገርያ የነበረው አስቻለሁ ታመነ እንግዳችን ነው… በርካታ ጉዳዮችን ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያወጋው አስቻለሁ ታመነ “ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፋሲል ከነማ ያደረኩት ዝውውር ከሻምፒዮን ወደ ሻምፒዮን ያደረኩት ነው”ሲል ተናግሯል…አስቻለሁ”እግዚአብሄር ለአዲስ ታሪክ አዘጋጅቶኛል ብዬ ነው የማስበው”ሲልም ስለነገው ተስፋ ተናግሯል።
*…..ወደ ኢትዮዽያ ቡና ባደረገው ዝውውር ደስተኛ የሆነው ግብ ጠባቂው በረከት አማረ
“ኢትዮዽያ ቡናን የለቀኩት በቤተሰብ ችግር እንጂ በገንዘብ አይደለም ወደ ቤቴም በመመለሴ ደስ ብሎኛል” ሲል ተናግሯል።
*… ባለመግባባትና በቅጣት ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተለየውና ለገብረ መድህኑ ሲዳማ ቡና የፈረመው ሙላለም መስፍን/ዴኮ/ “እውነቱን ለመናገር በቅዱስ ጊዮርጊስ ውልህን አድስ ቢባል የሚጠላ ተጨዋች የለም” ሲል ተናግሯል።
*…….ነገ ባህርዳር ላይ ስለሚጀመረው የሴካፋ ሻምፒዮና ዙሪያ ያጠናከርነው ዘገባም አለን…
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*….. “ቲየሪ ኦነሪን መቼም ከማልረሳቸው ተጨዋቾች አንዱ ነው” የሚለው ወጣቱ ኑኖ ታቫሬዝ አዲሱ መድፈኛ ኤምሬትስ ደርሷል…..
*……”በድጋሚ መጫወት እስክንጀምር ጓጉተናል” ባለው የማን.ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊጎናር ሶልሻየር ዙሪያ የተዘጋጀ ዘገባ አለን….
*…. የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የረገን ክሎፕ ስለቀጣዩ አመት ዝግጅት..ስለ ሞሳላህና ሳዲዮ ማኔ የሚሉትን ዘገባ ይዘናል……
*… ጂያንሉጂ ዶናሩማ በአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን ለስኬት ካበቃ በኋላ አዲሱ ክለቡ ወደሆነው ፒ ኤስ ጂ ያቀናል…ዶናሩማ ለፒኤስ ጂ ምን ይጨምራል..?በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘገባ አለን….
*…. በአውሮፓ ዋንጫ ያንጸባረቁ ወጣቶች ወደየተኛው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ያመሩ ይሆን..? በዚህ ዙሪያም የተዘጋጀ ዘገባ ይዘናል
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
Hatricksport team