የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት የዕለተ ቅዳሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ
በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ የሚደረግ ይሆናል።
በቅዳሜ ብቸኛ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ጎንደር አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ መደረግ እያለበት በአንዳንድ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት በገለልተኛ ሜዳ እንዲደረግ የተወሰነው የፋሲል ከተማ እና መቐለ ከተማ ጨዋታ ዛሬ(ቅዳሜ) 10፡00 ሲል አ/አ ስታዲየም ላይ የሚደረግ ይሆናል።
በ10ኛው ሳምንት አ/አ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከተማ መከላከያን ገጥሞ በራምኬል ሎክ ብቸኛ ግብ 1-0 ሲያሸንፍ መቐለ ከተማ በአንፃሩ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ አቻምፖንግ አሞስ እና አማኑኤል ገ/ሚካኤል ባስቆጠሯቸው ግቦች 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል።
- ማሰታውቂያ -
መቐለ ከተማ ካደረጋቸው 9ጨዋታዎች ማድረግ ከሚገባው 5 የሜዳው ውጪ ጨዋታዎች 4ቱን ከሜዳው ውጪ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ወደ አ/አ ተጉዞ 5ኛ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ ይሆናል፡፡ መቐለ ከተማ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ወደ ሶዶ ተጉዞ በጋይስ አምፖንግ ብቸኛ ግብ ወላይታ ድቻን ያሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛው ከሜዳው ውጪ ያስመዘገበው ድል ሆኖ ተመዝግቦለታል። አርባምንጭ ላይ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር እና ሀዋሳ ላይ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተመሳሳይ ያለግብ 0-0 እንዲሁም ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር አ/አ ስታዲየም ላይ ያለ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል። ከወልድያ ጋር የሚያደርገው ቀሪ ጨዋታ ረቡዕ ጥር 09 2010 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል።
ፋሲል ከተማ በአንፃሩ ማድረግ ከሚገባው 4 የሜዳው ላይ ጨዋታዎች 3ቱን ተጫውቷል። ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ማድረግ የሚገባው ጨዋታ ለረቡዕ ጥር 09 2010 መተላለፉ ይታወሳል። ካደረጋቸው 3 የሜዳው ላይ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻን 1-0 በሆነ ውጤት ብቸኛው በሜዳው ያስመዘገበው ድል ሆኖ ተመዝግቦለታል ከሀዋሳ ከተማ ጋር 2-2 እንዲሁም ከወልድያ ጋር 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአጠቃላይ በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከተማ 9ጨዋታዎችን አድርጎ 3ጨዋታዎችን አሸንፎ በ6 አቻ ተለያይቶ ያለምንም ሽንፈት 15 ነጥቦችን ሰብስቦ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቐለ ከተማ በአንፃሩ 9ጨዋታዎችን አድርጎ 3ጨዋታዎችን አሸንፎ 5ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ 1ጨዋታ ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 27ነጥቦች 14ቱን አሳክቶ ከፋሲል ከተማ በ1 ነጥብ አንሶ 6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ከፋሲል ከተማ በኩል አይናለም ኃይሉ እና ይስሀቅ መኩሪያ በጉዳት እንዲሁም አብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው) በቅጣት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የማይኖሩ ይሆናል። በመቐለ ከተማ በኩል አሌክስ ተሰማ እና ሚካኤል አካፉ በጉዳት ለቡድናቸው ግልጋሎት የማይሰጡ ይሆናል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አ/አ ስታዲየም ላይ 10፡00 ሲል የሚጀምር ይሆናል።