የ22ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ትናንት ጎንደር ላይ በተካሄደ 1 ጨዋታ ሲጀምር ዛሬ ይርጋለም፡ድሬድዋ፡እና አዲስ አበባ ስታዲዬሞች በሚደረጉ 3 ጨዋታዎች ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ ገፃችን ተመልክተነዋል፡፡
☞ሲዳማ ቡና ከ ደደቢት
ይሄ ጨዋታ ዛሬ ይርጋለም ላይ በ9:00 ሰዓት የሚደረግ ሲሆን ሲዳማዎች ባለፈው ሳምንት ሰበታ ላይ የቅርብ ተፎካካሪያቸውን ወልዲያ ከተማን አሸንፈው ለጨዋታው በጥሩ መነቃቃት ላይ ሲገኙ ቡድኑ በወራጂ ቀጠናው አፋፍ ላይ እንደመገኘቱ በጊዜ ከመውረድ ስጋት ለመውጣት የጨዋታው ውጤት እጂጉን ያስፈልጋቸዋል፡፡በእንግዳዎቹ ደደቢቶች በኩል ባለፈው ሳምንት በመቆለ ከተማዎች በሜዳቸው ከደረሰባቸው ሽንፈት በማገገም ቡድኑ በሁለተኛው ዙር በውጤት ማጣት በአነጋጋሪነቱ ሲቀጥል በትክክልም የወንጫ ተፎካካሪ ሁኖ ለመዝለቅ ከመሪዎቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ በዛሬው ጨዋታ ሶስት ነጥብ ከማግኘት ሌላ አማራጭ የለውም፡፡
በዘንድሮው የሊግ ውድድር እንዳለው የተጨዋቾች ስብስብ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን ያልቻሉት ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች በቅርብ ሳምንታት መሻሻል እያሳዩ ነው፡፡በተለይም የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ከወራጂ ቀጠና ስጋት እንደሚርቁ ይጠበቃል፡፡በአስደናቂ ብቃት የመጀመሪያውን ዙር በ1ኛነት ያጠናቀቁት ደደቢቶች በሁለተኛው ዙር ተከታታይ ሽንፈቶችን ቢያስተናግዱም አሁንም በዋንጫው ፉክክር ውስጥ እንደመሆናቸውን የዚህ ጨዋታ 3ነጥብ በቀጣይ ሳምንታት ተፎካካሪ ሁነው ለመበቆየት ያግዛቸዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የዛሬው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በሜዳው በተደጋጋሚ ሽንፈትን የሚያስተናግደው ሲዳማ ከሜዳው ውጭ ለማሸነፍ ከሚቸገረው ደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታ ሲዳማ ቡና አሸንፎ ከወራጂ ቀጠናው ይርቃል ወይስ ደደቢት ከመሪዎቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ያጠባል የሚለው በጉጉት የሚጠበቅ ነው፡፡
በጉዳትና ቅጣት ዜና በበላሜዳዎቹ ሲዳማዎች በኩል፡ ምንም አይነት የጉዳትም ሆነ ቅጣት ስለመኖሩ የተነገረ ነገር የለም፡፡እንደውም ውዝግብ ላይ የነበሩት መሀመድ ኮናቴና ኦሻዮ ኬነዲ ከክለቡ ጋር ስምምነት በመድረሳቸው ለጨዋታው ዝግጁ ናቸው፡፡በደደቢት በኩል ኤፍሬም አሻሞ በቅጣት ይሄ ጨዋታ የሚያልፈው ሲሆን የጉዳት ዜና የለም፡፡
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር አዲስአበባ ላይ በነበራቸው ግንኙነት በባለሜዳዎቹ ደደቢቶች የ5-2 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ሚካኤሌ አርዓያ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
☞ድሬድዋ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
የዛሬው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ድሬድዋ ላይ በ9:30 የሚካሄድ ሲሆን ድሬድዋ ከተማ ባለፈው ሳምንት ከሜዳው ውጭ ወደ አዳማ አቅንቶ በአዳማ ከተማ ተሸንፎ ሲመለስ እንግዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች በሜዳቸው በመከላከያ አስደንጋጭ ሽንፈት ያስተናገዱ ሲሆን ሁለቱም ክለቦች ከሽንፈት እንደመመለሳቸው ወደአሸናፊነት ለመመለስ ብርቱ ፍክክር እንደሚስተናገድበት ይሄ ጨዋታ የሚጠበቅ ነው፡፡
በ18ነጥብ ወራጂ ቀጠና ያሉት ባለሜዳዎቹ ድሬዎች ይህን ጨዋታ አሸንፈው ከወራጅ ቀጠናው ለጊዜውም ቢሆን ለመውጣት የሌሎችን ውጤት መጠበቅ የግድ ይላቸዋል፡፡ቢሆንም ግን ጨዋታውን አሸንፈው ነጥባቸውን ወደ 22 ለማድረስ የሚጫዎቱ ሲሆን እንግዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ቢያሸንፉም አሁን ላይ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ መመለስ ባይችሉም መሃል ሰፋሪ ሁነው የሚቀጥለውን ሳምንት ለመጠበቅ ጨዋታውን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሜዳው የተሻለ ጠንካራ እንደሆነ የሚነገርለት ድሬድዋ ከተማ በሁለተኛው ዙር በሜዳው ካደረጋቸው 2 ጨዋታዎች ሽንፈት ሳያስተናግድ በ1ጨዋታ ሲያሸንፍ ሌላውን የአቻ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን እንግዳዎቹ ሀዋሳዎች ከሜዳቸው ውጭ ሲዎጡ ያን ያህል ይቸገራሉ ባይባልም ውጤታማ ናቸው ለማለትም ያስመዘገቡት ውጤት አያስደፍርም፡፡በሁለተኛው ዙር ከሜዳቸው ውጭ ካደረጓቸው 3ጨዋታዎች ያስመዘገቡት ትልቁ የአቻ ውጤት ቢሆንም ሽንፈትን አለማስተናገዳቸው በጥሩ ጎን ይነሳል፡፡
በጉዳትና ቅጣት ዜና በድሬዳዋ ከተማ በኩል በርከት ያሉ ተጨዋቾች ከጉዳትና ከብሄራዊ ቡድን ግልጋሎት እንደተመለሱ ሲነገር፡ጀማል ጣሰው፡አትራም ኩዋሜና ዬሴፍ ደሙዬ ከጉዳት ሲመለሱ ዮሃንስ ሴጌቦና መሳይ ጳውሎስ ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግልጋሎት የተመለሱ ሲሆን በባለሜዳዎቹ በኩል የቅጣት ዜና አለመኖሩ ተነግሯል፡፡በሀዋሳ ከተማ በኩል በ5ቢጫ ምክንያት ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን በጨዋታው የማይሰለፍ ሲሆን ጅብሪል አህመድና ታፈሰ ሰለሞን ከጉዳት መልስ ለቡድኑ ግልጋሎት እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ሀዋሳ ላይ በነበራቸው ግንኙነት ባለሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች 1-0 አሸንፈዋል፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ይርጋለም ወ/ጊዬርጊስ በመሃል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
☞ ኢትዮ ኢለክትሪክ ከ ወልዲያ ከተማ
ከወራጂ ለመተረፍ ብርቱ ፍክክር እንደሚደረግበት የሚጠበቀው ይሄ ጨዋታ አዲስአበባ ላይ በ10:00 ይጀምራል፡፡በታችኛው የሊጉ ግርጌ የተቀመጡት ኢለክትሪኮችም ሆኑ የመውረድ ስጋት ተደቅኖባቸው በወራጂ ቀጠናው አፋፍ ላይ የተቀመጡት ወልዲያ ከተማዎች እርስበረሳቸው ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ የፍፃሜ ያህል ትርጉም ያለው ጨዋታ ነው፡፡ባለፈው ሳምንት በሽንፈት ለዚህ ጨዋታ የቀረቡት ሁለቱ ቡድኖች ኢትዮ ኢለክትሪክ ጅማ ላይ በጅማ አባጅፋር ሲሸነፍ ወልዲያዎች ሰበታ ላይ በሲዳማ ቡና በሽንፈት ተመልሰዋል፡፡
በመሀከላቸው ባላቸው የ2 ነጥብ ልዩነት በደረጃ ሰንጠረዡ 16ኛና 13ኛ የተቀመጡት ኢለክትሪክና ወልዲያ ከተማ አንደኛው ክለብ ተጋጣሚውን አሸንፎ ከመውረድ ለመትረፍ የሚያደርጉትን መልካም ጉዞ ለመቀየስ ይሄን ጨዋታ ባሸናፊነት መወጣት ለሁለቱም ቡድኖች ያለው ዕድል ተመሳሳይ ነው፡፡የዛሬው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አሸናፊው ቡድን በተሸናፊው ቡድን ላይ ቀጥተኛ የሆነ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡በተለይም በጨዋታው ወልዲያ ከተማ የሚሸነፍ ከሆነ ወራጂ ቀጠናውን ከመቀላቀሉ ባሻገር ከሜዳ ውጭ ባሉ ችግሮች ተከቦ ቡድኑ ሌላ ጫና ውስጥ እንዳይገባ የሚያሰጋ ሲሆን ኢለክተትሪክ 1ተስተካካይ ቀሪ ጨዋታ እያለው አሸናፊ ከሆነ ለመትረፍ በሚያደርገው ጉዞ መልካም አጋጣሚን መፍጠሩ አይቀርም፡፡
በቅጣትና ጉዳት ዜና በሁለቱም ቡድኖቸች በኩል የጉዳት ዜና አለመኖሩ የተነገረ ሲሆን፡የኢለክትሪኩ በሃይሉ ተሻገርና የወልዲያው ምንያህል ተሾመ በቅጣት የማይሰለፉ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር በነበራቸው ግንኙነት 1-1 መለያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ብሩክ የማነብርሃን ይመሩታል፡፡