የሁለተኛው ዙር አካል የሆነው 16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ጨዋታዎች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሚካሄዱ 2 ጨዋታዎች እና በክልል ስታዲዬሞች በሚደረጉ 5 ጨዋታዎች ይጀምራል፡፡ሀትሪክ ስፖርት በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ ገፃችን በክልል ስታዲዬሞች በተመሳሳይ 9:00 የሚካሄዱ 5 ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ዳሰነዋል ፡፡
በዛሬው ጨዋታ በጥር የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን ሲለቁና ሲያስፈርሙ የሰነበቱ ክለቦች ሜዳ ላይ መሻሻል ያሳያሉ ወይስ በዛው ይቀጥላሉ ተጨዋቾችስ በአዲሱ ክለባቸው የተሻለ ነገር ያሳያሉ ወይ የሚለው በደጋፊዎች በኩል የሚጠበቅ ነው፡፡
☞ መቐለ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
ዛሬ በክልል ስታዲየሞች ከሚካሄዱ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው የመቐለ ከተማና አርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታ ከቀኑ በ9:00 ሰዓት በትግራይ ስታዲይም የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በተለያየ ወቅታዊ አቋም ላይ ሁነው መገናኘታቸው ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገዋል፡፡
መቐለዎች በጥር የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን ቢለቁም በምትኩ ያስፈረሙት የአማካኝ ስፍራ ቴክኒሺያኒ ጋቶች ፓኖም በጉዳት በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም፡፡መቐለ ከተማ ለሊጉ እንግዳ ቢሆኑም በመጀመሪያው ዙር ያስመዘገቡት ውጤት የሊጉ የመጀመሪያው ዙር ክስተት ቡድን አስባሏቸዋል፡፡በአንፃሩ አርባምንጭ ከተማ በዝውውሩ ተጨዋቾችን በማምጣት እና በመልቀቅ የነበረው ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር፡፡እነ ዬናታን ከበደና፡ ታዲዬስ ወልዴን ሲለቅ እነ በረከት አዲሱንና ሌሎች ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡አዞዎቹ በሊጉ የተጠበቀውን ያህል ተፎካካሪ ሳይሆኑ የመጀመሪያውን ዙር በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ሆኖ በማጠናቀቁ የመውረድ ስጋት ከተጋረጠባቸው ክለቦች ቀዳሚው ነው፡፡
ባለሜዳዎቹ መቐለ ከተማዎች ተጋጣሚያቸውን በሜዳቸውና በደጋፊዎቻቸው ፊት በማሸነፍ እውነተኛና ጠንካራ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆናቸው ለማሳየት የሚጫዎቱ ሲሆን ፡አዞዎቹ ከተደቀነባቸው ከሊጉ የመውረድ ስጋት በጊዜ ለመትረፍ የነገውን ጨዋታ በማሸነፍ ለቀጣዩ ጨዋታቸው የተስፋ ስንቅ መሰነቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
መቐለ ከተማ ከመሪው ደደቢት ያለውን የነጥብ ልዩነት ከማጥበብም ባሻገር ከተከታዮቹ ያለውን ልዩነት ለማስፋት የሚጫዎት ሲሆን አዞዎቹ ቢያሸንፉም ከወራጂ ቀጠናው ለመውጣት የሌሎችን ውጤት መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡መቆለ ከተማ በ25 ነጥብ በደረጃ በሰንጠረዡ 3ኛ ላይ ተቀምጦ ለጨዋታው ሲቀርብ አርባምንጭ ከተማ በ13 ነጥብ በሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የጉዳት ዜና ስንመለከት ባለሜዳዎቹ መቐለ ከተማ በኩል ጋቶች ፓኖም እና አሌክስ ተሰማ በጉዳት፡አመለ ሚልክያስ በ5ቢጫ ካርድ ምክንያት ቅጣት በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም፡፡በእንግዳዎቹ አዞዎቹ በኩል ፀጋዬ አበራ እና
እስራኤል ሻጎሌ ከ20አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመሄዳቸውበዛሬው ለቡድናቸው ግልጋሎት አይሰጡም፡፡
በመጀመሪያው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች ቦዲቲ ላይ ያደረጉት ጨዋታ፡ያለ ግብ ነጥብ ተጋርተው መለየታቸው ይታወሳል፡፡
ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ዳዊት አሳምነው በመሃል ዳኝነት እንደሚመሩት ታውቋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
☞ ሀዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር
የሊጉ ነባር ክለብ ሀዋሳ ከተማና የሊጉ እንግዳና የመጀመሪያው ዙር ክስተት ቡድን ጅማ አባጅፋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላኛው ክልል ላይ በሀዋሳ ስታዲዬም 9:00 የሚካሄድ ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡ሀዋሳ ከተማ በ18 ነጥብ 8ኛ ደረጃ በመያዝ ቢያጠናቅቁም በመጀመሪያው ዙር ወጥ ያልሆነ እንቅስቃሴ ካሳዩ ክለቦች አንደኛው ሲሆን ተጋጣሚው ጅማ አባጅፋር የመጀመሪያው ዙር ከሳምንት ሳምነት በጥሩ መሻሻል ውጤት በማስመዘገብ በ25 ነጥብ በሰንጠረዡ በ2ኛነት ያጠናቀቀ ቡድን ነው፡፡የዛሬው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሁለቱም በትልቅ መነሳሳት ላይ የሚገኙ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ነው፡፡ ባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎች በሊጉ ተፎካካሪ ለመሆን በጥር የዝውውር መስኮት እነ አብዱልከሪም ሀሰን ጋር ሲለያይ በምትኩ ተጨዋቾችን አምጥቷል፡፡ሀዋሳ ከተማ ይህን ጨዋታ በሜዳቸው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡እንግዳዎቹ አባጅፋሮች በሊጉ ታሪክ አሁንም ክስተት በመሆን በዋንጫ ፉክክሩ ለመቆየት የዛሬውን ጨዋታ ባያሸንፉም ነጥብ መጋራት ያስፈልጋቸዋል፡፡ጅማ አባጅፋር አሁንም በጥንካሬው ለመቀጠል እነ ነጂብ ሳኒን አምጥቷል፡፡በጨዋታው በባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎቹ በኩል፡አዲስአለም ተስፋዬ በ5ቢጫ ካርድ ቅጣት የማይሰለፍ ሲሀሆን፡መሳይ ጳውሎስ፡ዮሐንስ ሴጌቦና፡ፀጋአብ ዮሴፍ ከ20አመት በታች ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በመሄዳቸው ክለቡ የነሱን ግልጋለሎት አያገኝም፡፡
በጅማ አባጅፋር በኩል እስካሁን ምንም አይነት የቅጣትም ሆነ የጉት ዜና የለም፡፡ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር የሊጉ 1ኛ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ አባጅፋሮች ጅማ ስታዲዬም በሜዳቸው 2ለ ምንም ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ጨዋታውን በመሃል ዳኝነት ፌደራል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ይመሩታል፡፡
☞አዳማ ከተማ ከ ወልዲያ ከተማ
በቅርብ አመታት ሁሌም በዋንጫ ፉክክሩ የማይጠፋው አዳማ ከተማ በሜዳው፡ በጥሩ መነቃቃት ላይ ያለውን ወልዲያ ከተማ ከቀኑ በ9:00 አበበ ቢቂላ ስታዲዬም ላይ ያስተናግዳል፡፡አዳማ ከተማ በመጀመሪያው ዙር በ23 ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ በ5ኛነት ሲያጠናቅቅ ተጋጣሚው ወልዲያ ከተማ በመጨረሻ ሳምንታት ባስመዘገባቸው ድሎች ከወራጂ ቀጠና ወጥቶ በ18 ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ በ11ኛነት ተቀምጧል፡፡አዳማ ከተማ ዘንድሮም በዋንጫ ፉክክሩ የሚያቆየው በወጣቶች የተገነባ ስብስብ ያለው ክለብ ስለመሆኑ በርካቶችን የሚያስማማ ነው፡፡እንግዳው ወልዲያ ከተማ በርካታ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ቢያዛውርም በተለያዩ ምክንያቶች የሚጠበቀውን ያህል ውጤት ሳያስመዘገብ መሃል ሰፋሪ ሁኖ የሁለተኛውን ዙር ይጀምራል፡፡ወልዲያ ከተማ አሁንም እንደ ክረምቱ ተጨዋቾችን ቢያመመጣም ከክለቡ የለቀቁ ተጨዋቾች ቁጥር የሚሸፍን አይደለም፡፡አደማ ከተማ ተጨዋቾችን ከማምጣት ይልቅ ማሰናበት ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር፡፡በዚህም የሁለቱም ክለቦች ሜዳላይ የሚያሳዩት እንቀቅስቃሴ የሚጠበቅ ነው፡፡በአዳማ ከተማ በኩል በዚህ ጨዋታ ሚካኤል ጆርጅ፡ሙጂብ ቃሲም፡ተስፋዬ በቀለ እና ሱራፌል ዳኛቸው፡በጉዳት ምክንያት የማይሰለፉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡በእንግዳዎቹ ወልድያዎች በኩል፡ብሩክ ቃልቦሬ፡እና ምንያህል ተሾመ በጉዳት በዚህ ጨዋታ እንደዚሁ ማይሰለፉ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡በመጀመሪያው ዙር፡1ኛ ሳምንት ሁለቱ ክለቦች በወልዲያ ሼህ ሙሃመድ አሊአላሙዲን ስታደዲዬም ባደረጉት ጨዋታ ባለሜዳዎቹ አዳማ ከተማን 2ለ ምንም አሸንፈዋል፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ሚካኤል አርዓያ ይመሩታል፡፡
☞ ድሬድዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዬርጊስ
ይሄኛው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በውጤት ቀውስ ውስጥ ሁነው እርስ በርስ የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡ባለሜዳዎቹ ድሬዎች ባለፈው አመት በመጨረሻ ከተረፉበት የወራጅ ቀጠና ዘንድሮም የባለፈው አመት ስጋት ከፊታቸው ሲጠብቃቸው ፈረሰኞቹ ከሚታወቁበት የአሸናፊነት ጉዞ በተቃራኒው መጓዝ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡በሊጉ በሜዳቸውም ሆነ ከሜዳቸው ውጭ ካሸነፉ ወራቶች ከመቆጠራቸው ባሻገር በአፍሪካ መድረክ ከሚሳተፉበት የካፍ ቻምፒዬንስ ሊግ በጨዋታ ግብ ሳያስቆጥሩ 1 ግብ ተቆጥሮባቸው መሰናበታቸው ይታወቃል፡፡ድሬድዋ ከተማ በመጀመሪያው ዙር በ13 ነጥቦች ወራጂ ቀጠና ውስጥ ሁኖ ለጨዋታው ሲቀርብ ፡ ፈረሰኞቹ በ23 ነጥብ ከሊጉ መሪ ደደቢት በ6 ነጥቦች ተበልጠው የዛሬውን ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ያደርጋሉ፡፡
በመጀመሪያው ዙር ሁለቱ ክለቦች በአዲስ አበባ ስታዲዬም ባደረጉት ጨዋታ 1ለ1 መለያዬታቸው ይታወሳል፡፡በድሬዳዋ ከተማ በኩል በዚህ ጨዋታ የኢማኑኤል ላሪያን ግልጋሎት የማያገኝ ሲሆን ፡በእንግዳዎቹ በቅ/ጊዮርጊስ፡በኩል ሮበርት ኦዶንካራ ለሀገሩ ዩጋንዳ ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ምክንያት ከኬሲሲኤ ጨዋታ እስካሁን ባለመመለሱ ፡የማይኖር ሲሆን
ሳላዲን ሰዒድ ና ናትናኤል ዘለቀ በጉዳት ለጨዋታው ወደ ድሬድዋ አልሄዱም፡፡በመጀመሪያው ዙር 1ኛ ሳምንት ፈረሰኞቹ በሜዳቸው በአዲስአበባ ስታዲዬም ድሬድዋ ከተማን ባስተናገዱበት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው መለያዬታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጨዋታውን ኢንተርናሺናል ዳኛ በላይ ታደሰ የሚመሩት ይሆናል፡፡
☞ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዬጵያ ቡና =ቡና ደርቢ
በዘንድሮው የሊግ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ቢጠበቅም፡ጥሩ ጊዜን ያላሳለፉት ሁለቱ ቡናዎች ዛሬ ክልል ላይ ከሚደረጉ 5 ጨዋታዎች በደርቢነት ፉክክር እንደሚስተናገድበት የሚጠበቅ ጨዋታ ይሄው ሁለቱ ቡናዎች የሚገናኙበት ጨዋታ ብቻ ነው፡፡ኢትዬጵያ ቡና የመጀመሪያውን ዙር በአሰልጣኝ መቀያዬር ቡድኑ አለመረጋጋት ውስጥ ሆኖ የሚጠበቅበትን ውጤት ባለማስመዝገቡ በደጋፊው በኩል ከፍተኛ ጫና የነበረበት ክለብ ነበር፡፡ አሁንም ከዚህ ችግሩ ለመላቀቅ ሁነኛ አማራጭ ያላቸውን የውጭ ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾችን አምጥቷል፡፡ ሲዳማ ቡናም ቢሆን በውጤት ማጣት ምክንያተት አሰልጣኝ እስከመቀዬር ደርሷል፡፡ኢትዬጵያ ቡና የመጀመሪያውን ዙር በ20 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 7ኛ ላይ ሆኖ ሲያገባድድ ባለሜዳዎቹ ሲዳማዎች በተጋጣሚያቸው በ2 ነጥብ ተበልጠው በ18 ነጥብ 10 ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ሁለቱ ቡናዎች በቅርቡ በ7ኛው የህዳሴ ዋንጫ ለፍፃሜ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና 1ለ ምንም ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ሲዳማ ቡና ዛሬ በሜዳው ምላሽ ይሰጣል ወይ የሚለው የሚጠበቅ ነው፡፡ሲዳማ ቡና ይህን ጨዋታ በሜዳው የሚያሸንፍ ከሆነ በሰንጠረዡ ተጋጣሚውን የመብለጥ አጋጣሚ አለው፡፡ሲዳማ ቡና በጨዋታው
ባዬ ገዛኸኝን በ5ቢጫ ቅጣት ምክንያት የማያሰልፍ ሲሆን ሚካኤል ሀሲሳ፡ዮናታን ፍሰሀና ሙጃይድ መሀመድ ከ20አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመሄዳቸው ግልጋሎታቸውን አያገኝም፡፡በእንግዳው ኢትዮጵያ ቡና በኩል
አክሊሉ አያናው እና አለማየሁ ሙለታ በጉዳት የማይሰለፉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያው ዙር 1ኛ ሳምንት አዲስአበባ ስታዲዬም ላይ ባደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ነበር፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ይመሩታል፡