የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ የኘሪሚዬር ሊግ 15ኛ ሳምንት ቀሪ 1 ተስተካካይ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ እና ወልዲያ ከተማን ዛሬ በሶዶ ስታዲዬም ከቀኑ በ9:00 በሚያገናኝ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
የዛሬው የወላይታ ዲቻና የወልዲያ ከተማ ጨዋታ የሊጉ የመጀመሪያው ዙር የማጠቃለያ ብቸኛ ጨዋታ እንደመሆኑ በደረጃ ሰንጠረዡ ተጋጣሚዎቹ ከፍ የሚሉበት አጋጣሚ እንደመኖሩ ፡ኢትዬጵያ ቡና፡ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አሁን ካሉበት ደረጃ የመውረድ ስጋት ተጋርጦባቸዋል፡፡
በቀሪ ተስተካካይ መርሃ ግብር በይደር ተይዞ የቆየው የወላይታ ዲቻና ወልዲያ ከተማ ጨዋታ ዛሬ ሶዶ ላይ ሲካሄድ ሁለቱም ቡድኖች በጥሩ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ላይ ሁነው መገናኘታቸው ጨዋታው ከፍተኛ ፍክክር እንደሚስተናገድበት ከወዲሁ የሚጠበቅ ሁኗል፡፡
ባለሜዳዎቹ ወላይታ ዲቻዎች የአሰልጣኝ ለውጥ ካደረጉ በሇላ በሊጉ በተከታታይ ድሎች ወራጂ ቀጠናውን ለቀው የወጡበትን ጥሩ ውጤት ሲያስመዘግቡ፡በሊጉ 14ኛ ሳምንት ከሜዳቸው ውጭ ወደ ጅማ አቅንተው በጅማ አባጅፋር የ2ለ1 ሽንፈት ቢያስተናግዱም፡ ባለፈው ሳምንት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የግብፁን ሀያል ክለብ የ5 ጊዜ አፍሪካ ሻምፒዬንስ ሊግ አሸናፊውን ዛማሌክ በሜዳቸው 2ለ1 ማሸነፋቸው በትልቅ የአሸናፊነት ስነ ልቦና እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
እንግዳዎቹ ወልዲያ ከተማዎች በበኩላቸው በወቅታዊ የከተማቸው ሁኔታ 1 ወር ያህል ከጨዋታ ርቀው ከተመለሱ በሇላ ባደረጓቸው 3 ተከታታይ የሜዳቸው ጨዋታዎች 2ቱን ሲያሸንፉ በ1 አቻ በመለያየት ከ9 ነጥብ 7ቱን አሳክተው ከወራጂ ቀጠና የራቁበትን ውጤት ከማስመዝገባቸው ባሻገር ባለፈው ሳምንት በሜዳቸው የሊጉን መሪ ደደቢት ማሸነፋቸው የበለጠ ለዚህ ጨዋታ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸው የሚጠበቅ ነው፡፡
በሌላ በኩል ባለሜዳዎቹ ዲቻዎች ለካፍ ኮንፌደሬሽን ካኘ የመልስ ጨዋታ ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ያሳርፋሉ ወይስ ለጨዋታው ትኩረት ሰተው ያሰልፋሉ ፡የሚለው የሚጠበቅ ሲሆን፡ በወላይታ ድቻ በኩል ዳግም በቀለ ወደ ሜዳ ሲመለስእርቅይሁን ተስፋዬና ፀጋዬ ብርሃኑ እማይኖሩ ይሆናል በወልዲያ ከተማ በኩል ከጉዳት የተመለሰው ተስፋዬ አለባቸው ወደ ሶዶ ቢጓዝም የመሰለፉ ነገር 50/50 ሲሆን ተስፋሁን ሸጋውና ሰለሞን ገ/መድህን ከጉዳት ባለመመለሳቸው ወደ ወላይታ ሶዶ ከአሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዩርጊስ ስብስብ ጋር አለመሄዳቸው ተነግሯል ፡፡
ባለሜዳዎቹ የጦና ንቦች በተጋጣሚያቸው በ2 ነጥብና በ2 የግብ ክፍያ ተበልጠው በደረጃ ሰንጠረዡ በ14 ጨዋታ በ16 ነጥብና በ2 የግብ ዕዳ 11ኛ ደረጃ ተቀምጠው ይህን ጨዋታ የሚያደርጉ ሲሆን የሚያሸንፉ ከሆነ ነጥባቸውን ከ16 ወደ 19 ከፍ በማድረግ ደረጃቸውን ከ11ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ድረስ ከፍ የሚሉበትን ዕድል በራሳቸው መወሰን የሚያስችላቸው አጋጣሚ ይኖራል፡፡
እንግዳዎቹ ወልዲያዎች በደረጃ ሰንጠረዡ በ14 ጨዋታ በ18 ነጥብ ያለምንም ጎል 10ኛ ደረጃ የተቀመጡ ሲሆን ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የግብ ክፍያ የሚያሸንፉ ከሆነ አሁን ካሉበት 10ኛ ደረጃ 3ደረጃዎችን በማሻሻል የመጀመሪያውን ዙር የሊግ ጨዋታ በ7ኛነት ማጠናቀቅ ይችላሉ፡፡
በጨዋታው ሁለቱ ክለቦች ነጥብ ተጋርተው የአቻ ውጤት የሚያስመዘግቡ ከሆነ ባለሜዳዎቹ ዲቻዎች የመጀመሪያው ዙር አሁን ያሉበትን 11ኛ ደረጃ ይዘው ለማጠናቀቅ የሚገደዱ ሲሆን፡ለወልዲያዎች የአቻው ውጤትም ተጠቃሚዮች የሚያደርጋቸው ሲሆን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ 2 ደረጃዎችን በማሻሻል ወደ 8ኛነት ከፍ በማለት ዙሩን ሊያገባድዱ ይችላሉ፡፡
እስከአሁን ሁለቱ ቡድኖች ወላይታ ዲቻና ወልዲያ ከተማ ባለፈው ዓመት በመጀመሪያው ዙር 8ኛው ሳምንት ሶዶ ላይ ተገናኝተው ባለሜዳዎቹ 1ለ0 ሲያሸንፉ በሁለተኛው ዙር ወልዲያ ላይ በሊጉ 23ኛ ሳምንት ሲገናኙ ባለሜዳዎቹ ወልዲያዎች1ለ0 አሸንፈዋል፡፡
የዛሬውን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ፌዴራል ዳኛ ወልዱ ንዳው የሚመሩት ይሆናል፡፡