የኢትዮጵያ ፕሪሚየር እንዲህ እንዲያ እያለ እነሆ 6ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል። ሊጉ እስካሁን ድረስም ለ5 ሳምንታት በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት እና እንግዳ ክለብን በመልካም አቀባበል እየተካሄደ ሲሆን ይህም ይበል የሚያስብል ሆኖ እስከ ሊጉ ፍፃሜ መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን።
በሊጉ 6ኛ ሳምንት 8ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚካሄዱ ሲሆን አርብ እና እሁድ አንድ አንድ እንዲሁም ቅዳሜ ስድስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል 5ቱ ጨዋታዎች ክልል ላይ ሲደረጉ ቀሪዎቹ 3ጨዋታዎች ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ነገ(ቅዳሜ) ጎንደር ላይ ፋሲል ከተማ ከባህርዳር ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ቅድመ ዳሰሳ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ፋሲል ከተማ ከባህርዳር ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 24/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌዴራል አርቢትር ሄኖክ አክሊሉ
የጨዋታ ቦታ: አጼ ፋሲለደስ ስታዲየም
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት ነገ አጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከተማ ከባህርዳር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ በፌዴራል አርቢትር ሄኖክ አክሊሉ መሪነት 9:00 ላይ የሚጀምር ይሆናል። ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻል እያሳዩ የሚገኙ ሲሆን በ4ኛው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ተለያይተዋል። በ4ኛው ሳምንት ፋሲል ከተማ ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ድራማዊ ክስተት በታየበት ጨዋታ እስከ 90ኛው ደቂቃ 3-1 ሲመራ ቢቆይም በመጨረሻ ደቂቃዎች በተቆጠሩበት 2ግቦች ከሰበታ ከተማ ጋር 3አቻ ተለያይቶ ሲመለስ ባህርዳር ከተማ ደግሞ በሜዳው የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን ሀዲያ ሆሳዕናን አስተናግዶ ሁለት ጊዜ ቢመራም ሁለት ግቦች ተቆጥረውበት መሪነቱን ማስጠበቅ ሳይችል ሁለት አቻ ተለያይቷል። ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።
- ማሰታውቂያ -
ሁለቱ ቡድኖች በ5ሳምንት የሊጉ ጉዞ በደረጃ ሰንጠረዡ ተቀራራቢ ቦታ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ሲዳማ ቡና ከመሪዎቹ ወልዋሎ አ.ዩ እና መቐለ 70 እንደርታ በ 1ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ በ9ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ተጋጣሚው ድሬደዋ ከተማ ደግሞ የሊጉ ግርጌ ላይ ካለው ሀዲያ ሆሳዕና 2ነጥቦች ከፍ ብሎ በ2ነጥቦች 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በፋሲል ከተማ በኩል እንየው ካሳሁን እና ያሬድ ባዬህ በጉዳት የማይኖሩ ሲሆን ይህ ቅድመ ዳሰሳ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በባህርዳር ከተማ በኩል የተሰማ የጉዳት ዜና የለም።