የወቅቱ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ የሆነውን የደቡብ አፍሪካውን ማማሎዲ ሰንዳውንስን የሚገጥመው ቅ.ጊዮርጊስ ነገ 2፡00 ሠዓት የአዲስ አበባን መሬት ለቀው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይበራሉ።
የቅ.ጊዮርጊስ ቡድን ነገ 12:00 ሠዓት ኤርፓርት ደርሰው አስፈላጊውን ምርመራ ካደረጉ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ወደ ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ቀጥታ በረራ የሚያደርጉ ሲሆን ከጆሃንስበርግ ጨዋታው ወደሚደረግበት ፕሪቶሪያ የሚጓዙ ይሆናል።
በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ በመግባት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ክለብ የሆነው ቅ.ጊዮርጊስ ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሲደርስ ከፍተኛ አቀባበል የሚጠብቀው ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የክለቡ ደጋፊዎችና በርካታ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ለማድረግ እየተዘጋጁ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።የመረጃ ምንጮች በተለይ ለ hatricksport.com ከስፍራው በስልክ እንደገለጹት ለቅ.ጊዮርጊስ ደማቅ አቀባበል ለማድረግና ቡድኑን ለመደገፍ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
የቅ.ጊዮርጊስ ቡድን ነገ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጋዘው 18 ተጫዋቾችን ይዞ ሲሆን አጥቂው ሳላህዲን ሠይድ በሁለት ቢጫ፣ምንተስኖት አዳነ በቅጣት፣በኃይሉ አሰፋ ቱሳ በጉዳት ከቡድኑ ውጪ ሲሆኑ ለረዥም ጊዜ በጉዳት ከቡድኑ ተለይቶ የነበረው ምንያህል ተሾመ ግን ከቡድኑ ጋር እንደሚጓዝ ተረጋግጧል።
ከክለቡ ጋር ከሚጓዙት ውስጥ 2 ግብ ጠባቂዎች እና 16 ተጨዋቾችን ይዞ ይጓዛል። ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑት ፈረሰኞች የሚከተሉት ናቸው፦
- ማሰታውቂያ -
ግብ ጠባቂዎች
♦ሮበርት ኦዶንካራ
♦ዘሪሁን ታደለ
ተከላካዮች
♦ደጉ ደበበ
♦አስቻለው ታመነ
♦ሳላዲን በርጊቾ
♦አበባው ቡጣቆ
♦መሃሪ መና
♦ፍሬዘር ካሳ
አማካዮች
♦ናትናኤል ዘለቀ
♦ተስፋዬ አለባቸው
♦አብዱልከሪም ኒኪማ
♦ምንያህል ተሾመ
♦ያስር ሙገርዋ
አጥቂዎች
♦አዳነ ግርማ
♦ራምኬል ሎክ
♦አቡበከር ሳኒ
♦ፕሪንስ ሰቬሪንሆ
♦ብሩኖ ኮኔ
በተያያዘ ዜና በርካታ የቅ.ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ልክ እንከዚህ ቀደሙ ሁሉ “በድል ተመለሱ”በማለት በመዝሙር የታጀበ ደማቅ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በርካታ የቅ.ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ለመደገፍ አ.አ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ የሁሉንም ሊባል በሚችል መልኩ ኤምባሲው ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረጉ መበሳጨታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለፅ ላይ ናቸው።