ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ መድረክ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻና ቅዱስ ጊዬርጊስ በካፍ ኮንፌደሬሺን ካኘ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት በሚደረገው የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ እርስ በርስ ሊገናኙ ይችላሉ:: ቅዱስ ጊዬርጊስ ይሳተፍበት ከነበረው የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር በዩጋንዳው ኬሲሲኤ ተሸንፎ ወደ ኮንፌደሬሺን ካኘ ሲወርድ ወላይታ ዲቻ የግብፁን ዛማሌክ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፉ ሁለቱም ክለቦች በኮንፌዴሬሽን ካኙ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በኮንፌዴሬሽን ካኘ ተጋጣሚያቸውን በደርሶ መልስ ውጤት ያሸነፉ 16 ክለቦችና በቻምፒየንስ ሊጉ በተጋጣሚያቸው ተሸንፈው ወደ ኮንፌደሬሽን ካኘ የወረዱ 16 ክለቦች በድምሩ 32 ክለቦች በእጣ ተደልድለው በደርሶ መልስ ውጤት አሸናፊ የሚሆኑት 16 ክለቦች ምድብ ድልድሉን የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡
በ1 ቋት ውስጥ የሚገኙ ክለቦች እርስ በርስ የማይገናኙ ሲሆን በተለያዩ ቋቶች የሚገኙት ቅዱስ ጊዬርጊስና ወላይታ ዲቻ እርስ በርስ የመገናኘት እጣ ፋንታ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ ሀገራችን በምድብ ድልድሉ በ1 ክለብ ብቻ መወከሏ ከወዲሁ ይረጋገጣል፡፡
ካፍ ዛሬ ምሽት በግብፅ ካይሮ ለሚወጣው የእጣ ድልድል ክለቦችን በ4 ቋቶች ከወዲሁ ይፋ ሲያደርግ ከቻምፒዬንስ ሊጉ የመጡት ፈረሰኞቹ በቋት 1 ላይ ሲካተቱ ዛማሌክን የረቱት የጦና ንቦች በቋት 4 ላይ ተካተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
☞ቋት1=አል ሂላል /ሱዳን/፡ቅዱስ ጊዮርጊስ /ኢትዮጵያ/: ኤኤስ ቪታ ክለብ /ዲ.ሪ/ ኮንጎ/ ፡ዛናኮ /ዛምቢያ/
☞ቋት2= ዩኒየንስ ስፖርቲቭ መዲናአልጀር /አልጄሪያ/: ሱፐርስፖርት ዩናይትድ /ደቡብ አፍሪካ/:አል ሂላል ኦብዬድ /ሱዳን/:ኢኒየምባ /ናይጄሪያ/
☞ቋት3= አሴክ ሚሞሳስ /ኮትዲቯር/:ሲኤፍ ሞናና /ጋቦን/:ያንግ አፍሪካንስ /ታንዛኒያ/ዊልያምስቪል /ኮትዲቯር/:አዱና ስታርስ /ጋና/:ጎር ማሂያ /ኬንያ:ዩዲ ሶንጎ /ሞዛምቢክ/: ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ /ናይጄሪያ/:ፕሌቶ ዩናይትድ /ናይጄሪያ/ራዮን ስፖርት /ሩዋንዳ/ጄኔሬሽን ፉት /ሴኔጋል/:ቤድቬስት ዊትስ /ደቡብ አፍሪካ/
☞ቋት 4=ሲአር ቤሎዝዳድ /አልጄሪያ/:ላማንቻ /ኮንጎ ሪፐብሊክ/:ካራ ብራዛቪል /ኮንጎ ሪፐብሊክ/:አል መስሪ /ግብፅ/: ዲፖርቲቮ ኒፋንግ /ኤኳቶሪያል ጊኒ/ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ)፣ ፎሳ ጁኒየርስ :ማዳጋስካር/:ጆሊባ /ማሊ/ ሬኔሳንስ በረካን /ሞሮኮ/ ራጃ አትሌቲክ ክለብ /ሞሮኮ/: ኮስታ ዶ ሶል /ሞዛምቢክ/አክዋ ዩናይትድ /ናይጄሪያ/
ቋት 1 ከ ቋት 4
ቋት2 ከ ቋት3
የቋት3 ቀሪ ክለቦች ከቋት 4 ቀሪ ክለቦች በእጣ የሚደለደሉ ሲሆን ቋቱ የተደለደለው ክለቦች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ነው፡፡
በኮንፌድሬሽን ካኙ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው የመጡ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ሲያደርጉ ከቻምፒዬንስ ሊግ የመጡ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
በዚህም ምክንያት ቅዱስ ጊዬርጊስ በሜዳው ሲጫዎት ወላይታ ድቻ ከሜዳው ውጭ የሚጫወት ይሆናል፡፡