የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኮት ዲ ኦር የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከ ቀኑ 10:00 ላይ ይደረጋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያ ጨዋታው ላይ ወደ ሲሺየልስ አቅንቶ በሳልሀዲን ሰዒድ ሁለት ጎሎች ኮት ዲ ኦር አቻውን 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በኩል በመልስ ጨዋታው ውጤቱ አስጠብቆ ለመውጣት እና ዙር ወደ ቀጣዮ ለማለፍ መልኩ ዝግጅታቸውን እንደሚያደርጉ ታውቋል።አላስፈላጊ እንግልት እና ድካምን ለማስቀረት ወደ ሀዋሳ ቀደም ብለው መጓዛቸውም ተገልፃል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ የሲሺየልሱ ኮት ዲ ኦር እግር ኳስ ክለብ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኮት ዲ ኦር መካከል በሀዋሳ የሚደረገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፊዴሬሽንም የስታድየም መግቢያ ዋጋ ይፋ አድርጓል፡-
ትሪቡን 100ብር፣ ካታንጋ 20ብር፣ ዳፍ እና ሚስማር 10ብር መሆኑን አስታውቋል በተጨማሪም የመሀል የትሪቡን መቀመጫ 200 መቶ ወንበር የተዘጋጀ ሲሆን ለክብር እንግዶች እና ጥሪ ለተደረገላቸው ግለሰቦች እንደሆነም ተገፆዎል።