በ26 ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የመጨረሻው የሳምንቱ ጨዋታዎች
ቀደም ብሎ 9 ስአት ላይ በፋሲለደስ ስታዲየም የተጀመረው ፋሲል ከነማ አርባምንጭ ከተማን አስተናገዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በህመም ምክኒያት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ያሰናበተው ፋሲል ከነማ በምትካቸው የተካውን በአስልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ እየተመራ ወደ ሜዳ ገብቶ በአቤል ያለው እና ኤፍሬም አለሙ ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከነማ በአምስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ38 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
- ማሰታውቂያ -
በድሬዳዋ በፌዴሬሽኑ ዲስኘሊን ወሳኔ ካለ ተመልካች 10 ሰዓት ላይ የተጀመረው ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ድሬዳዋ ከተማን የገጠመው ወልዲያ ከተማ
በበኩሉ በ1ኛው ደቂቃ ላይ በበረኛው
ቤሊንጌ ኖኸ ቀዳሚ ሲሆን ሁለተኛውን ጎል አንዱአለም ንጉሴ በ16 ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሌላ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናክሯል ዝርዝሩን ይህን http://wp.me/s7SLd5-3603 ተጭነው ይመልከቱ
የኘሪሜየር ሊግ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 25 | 23 | 49 |
2 | ሲዳማ ቡና | 26 | 9 | 46 |
3 | ደደቢት | 26 | 15 | 45 |
4 | ኢትዮጵያ ቡና | 26 | 11 | 43 |
5 | አዳማ ከተማ | 26 | 8 | 43 |
6 | ፋሲል ከተማ | 25 | 0 | 38 |
7 | ወልዲያ ከተማ | 26 | 0 | 33 |
8 | መከላከያ | 26 | -9 | 32 |
9 | ሀዋሳ ከተማ | 26 | 0 | 31 |
10 | አርባምንጭ ከተማ | 26 | -3 | 31 |
11 | ወላይታ ድቻ | 26 | -10 | 29 |
12 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 26 | -2 | 28 |
13 | ጅማ አባቡና | 26 | -4 | 28 |
14 | ድሬዳዋ ከተማ | 26 | -9 | 28 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
26 | -13 | 24 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 26 | -16 | 19 |
ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች