በ25ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ተካሂዷል።
ከቀትር በኋላ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአዳማ ከተማ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
አዲስ ህንጻ፣ ዳዋ ሁቴሳ እና ሙጂብ ቃሲም ለአዳማ ከተማ የአሸናፊነት ጎሎችን ሲያሰቆጥሩ ለአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ አሊ አያና ማስቆጠር ችሏል።
ክልል ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ሃዋሳ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ ደግሞ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
አስቻለው ግርማ የአሸናፊነቷን ጎል ለኢትዮጵያ ቡና ማስቆጠር ችሏል።
ጅማ ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው ጅማ አባ ቡና በበኩሉ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ለጅማ አባቡና ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል በ91ኛ ደቂቀ ላይ ሀይረዲን ሸረፋ የማሸነፊያዋን ጎል አስቋጥሯል
10 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ሊጉ ነገም ሲቀጥል ደደቢት ከድሬዳዋ ከተማ 8 ሰዓት ከ 30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ 10 ከ 30 ላይ ይካሄዳል።
ክልል ላይ በሚደረግ ጨዋታ ወልድያ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናግዳል።
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እያለው ከሲዳማ ቡና ጋር 43 ነጥብ በመያዝ በጎል ልዩነት ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ በእኩል 42 ነጥብ ይከተላሉ።
ነገ የሚጫወተው ደደቢት በ41 ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዟል።
ወላይታ ዲቻ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ አሁንም የሊጉን ግርጌ ይዘዋል።
ደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 23 | 21 | 43 |
2 | ሲዳማ ቡና | 25 | 7 | 43 |
3 | ኢትዮጵያ ቡና | 25 | 11 | 42 |
4 | አዳማ ከተማ | 25 | 8 | 42 |
5 | ደደቢት | 24 | 14 | 41 |
6 | ፋሲል ከተማ | 23 | 1 | 35 |
7 | ሀዋሳ ከተማ | 25 | 1 | 32 |
8 | አርባምንጭ ከተማ | 25 | -2 | 31 |
9 | መከላከያ |
25 | -10 | 31 |
10 | ወልዲያ ከተማ | 24 | -1 | 30 |
11 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 24 | -1 | 28 |
12 | ድሬዳዋ ከተማ | 25 | -6 | 28 |
13 | ጅማ አባቡና | 25 | -4 | 27 |
14 | ወላይታ ድቻ |
25 | -11 | 26 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
24 | -15 | 20 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 25 | -14 | 19 |