በ19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት እና ወልድያ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።
ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ደደቢት 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ጌታነህ ከበደ በ18ኛው እና 42ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሽመክት ጉግሳ በ68ኛው ደቂቃ ለደደቢት የአሸናፊነት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ሀዋሳ ከተማ በ80ኛው ደቂቃ የተገኘችውን ፍፁም ቅጣት ምት በፍሬው ሰለሞን አማካኝነት አስቆጥሯል።።
- ማሰታውቂያ -
በሼህ መሀመድ አሊ አል አሙዲ ስታዲየም መከላከያን ያስተናገደው ወልድያ ከተማ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ብቸኛዋን ግብም ያሬድ ብርሃኑ በ23ኛው ደቂቃ ከመረብ አዋህዷል።
ጅማ ላይ ጅማ አባቡና ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ሶዶ ላይ ወላይታ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።
በነገው እለት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9 ስአት ላይ የሚጫወት ሲሆን፥ በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ 11 ስአት ከ30 ላይ ድሬዳዋ ከተማን ያስተናግዳል።