በኢትየጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ሲቀጥሉ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።
የመወዳደሪያ ክፍያን በተመለከተ ብዙ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የነበረው ከፍተኛ ሊጉ አሁንም ክፍያውን አጠናቀው ያልከፈሉ ቡድኖች ስለሚገኙ የምድብ ሀ 4 ጨዋታዎች ብቻ እንደሚደረጉ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ባህርዳር ላይ ባህርዳር ከተማ አክሱም ከተማን ሲያስተናግድ ሽሬ ላይ ሽሬ እንደስላሴ ከኢትዮጵያ መድን የሚጫወቱ ይሆናል። ውድድሩ እሁድ ሲቀጥል 9፡00 ላይ የካ ክፍለ ከተማ ከሰበታ ከተማ አ/አ ላይ ሲገናኙ አማራ ውሃ ስራ ከ የኢትዮጵያ ኮ/ሥ/ኮ 10:00 ሲል ባህርዳር ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።
ቀሪ የምድብ ሀ እና የምድብ ለ ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ወደፊት እንደሚገልፅ አክሎ አሳውቋል።
በኢትየጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይደረጋሉ።
Managing Editor at Hatricksport Website