በተደጋጋሚ በኮንፌደረሽን ካኘ የመሳተፍ ዕድል ያገኘው መከላከያ ስፖርት ክለብ የካሜሮኑ ያንግ ስፖርት አካዳሚ ክለብ በ አዲስ አበባ ይገጥማል በመጀመርያው ዙር የኢትዬጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ጥሩ የኳስ ፍሰት እና ጠንካራ ስነ ልቦና አዳብረን እንገኛለን ይላሉ መከላከያዎች እሁድ በሚደረገው የኮንፌደሬሽን ካኘ ጠንካራ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በካሜሮን ከ13 አመት በፊት በ2004 በአንድ ካሜሮናዊ ዳኛ የተቆረቆረው ያንግ ስፖርት አካዳሚም ወጣት ተጫዋቾችን ይዞ ጥሩ ውጤት በማምጣት በካሜሮን የስፖርት አፍቃሪዎች ተወዳጅነት ያተረፈ በመሆኑ ፊልሚያው አጓጊ ያደርገዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የአንደኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር 15 ጨዋታዎችን አድርጎ አራቱን አሸንፎ ከስምንቱ አቻ ሲለያይ በሶስቱ ተሸንፎ 15 ግቦችን አስቆጥሮ 16 ተቆጥሮበት በአንድ የግብ እዳ 20 ነጥብ በመያዝ ስምንተኛ ደረጃ ይዞ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መሀል ላይ በመቀመጥ አጠናቅቋል ፡፡