ዛሬ ማለዳ በተደረገው 21ኛው የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በአንደኝነት አጠናቀዋል፡፡ በወንድ ኦሊቃ አዱኛ በሴቶቹ ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ኦሊቃ ማራቶኑን ለመጨረስ 2፡06፡15 ፈጅቶበታል፡፡ ኬንያዊው ኢሪክ ኪፕሮኖ ሁለተኛ የወጣ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ጽዳት አበጄ በሶሰተኛነት አጠናቋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሴቶቹ ደግሞ የ2017 ባለድሏ ወርቅነሽ ደገፋ ዘንድሮም ደግማዋለች፡፡ ወርቅነሽ ርቀቱን በ2፡19፡37 በመግባት አሸንፋለች፡፡
በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማንንም ጣልቃ ሳያስገቡ እሰከ 9ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡