THE BIG INTERVIEW with Kenenisa Bekele
በይስሀቅ በላይ
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- ቀነኒሳ እኔንም አንባቢዎ ቼንም
አክብረህ ለቃለ-ምልልሱ ስለተባበረክኝ ከልብ
አመሰግናለሁ…?
ቀነኒሳ፡- …እኔም እንግዳ አድርገህ
ስለጋበዝከኝ በጣም አመሰግናለሁ….
ሀትሪክ፡- …ቀነኒሳ ወደ ዋናው ጥያቄዬ
ከመግባቴ በፊት የበርሊኑን ማራቶን
በማሸነፍህ፣ ሁለተኛውን የዓለም የማራቶን
ሰዓት በማስመዝገብህ እንኳን ደስ አለህ…?
ቀነኒሳ፡- …እንኳን አብሮ ደስ አለን….
ሀትሪክ፡- …አሁንም ከበርሊኑ ማራቶን
ድልህ በፊት ስለቤተሰብህ አጫውተኝ እስቲ…?
ቀነኒሳ፡- …ምን ላጫውትህ…?…
(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …ከባለቤትህ ዳናዊት ገ/
እግዚብሔር ጋር ትዳር መስርታችሁ በአንድ
ጣሪያ ስር መኖር ከጀመራችሁ ከ1ዐ አመት
በላይ የሆናችሁ ይመስለኛል… ወለዳችሁ…?…
ከበዳችሁ…?… የትዳር… ህይወትህስ… እንዴት
ነው…?
ቀነኒሳ፡-…ከባለቤቴ…ከዳናዊት ጋር…
በትዳር ተጣምረን ደስተኛ ቤተሰብ መስርተን
መኖር ከጀመርን ረዘም ያለ አመታትን
አስቆጥረናል…፤…በእነዚህም አመታትም
በጣም ጥሩና ደስተኛ የሆነ ቤተሰብ
መስርተን…ጣፋጭ የትዳር ህይወትን
እየመራን ነው…(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …በጣም ደስ ይላል…ግን
ምነው…ወለዳችሁ…?…ከበዳችሁ…?…የሚለው
ጥያቄዬን ዘለልከው…?
ቀነኒሳ፡- …(ሣቅ)…አልዘለልኩትም…
እግዜአብሔር ይመስገን… ወልደናል…
ከብደናል…የሶስት ልጆች ማለትም የሁለት
ሴቶችና የአንድ ወንድ አባትም ለመሆን
ችያለሁ…የመጀመሪያዋ ልጄ 12 አመት…
ሁለተኛዋ 11ዓመትዋ ሲሆን ሶስተኛው ልጄ
ደግሞ ገና 7 አመቱ ነው፡፡ ባለቤቴም ልጆቼም
በሙያዬ ስኬታማ እንድሆን ህይወቴም
ጣፍጭ እንዲሆን የቅመም ያህል ስለሆኑልኝ
ከልቤ ነው የማመሰግናቸው…፡፡
ሀትሪክ፡- …አልፎ አልፎ የዘፋኝ ልጅ ዘፋኝ…
የአርቲስት ልጅ አርቲስት ሆነው የሚታዩበት
አጋጣሚ አለ…የቀነኒሳ ልጆችስ የአባታቸውን
ዱካ ተከትለው አትሌት የመሆን ፍላጎት
ይታይባቸዋል…?
ቀነኒሳ፡- …እ…ምን መሰለህ…ልጆቼ
መሮጥም…ስፖርትም ይወዳሉ…ትምህርት
ቤታቸው ይሮጣሉ…፤…ሶስቱም ላይ የሩጫ
ፍላጎት ታይባቸዋለሁ…፡፡…ግን ከወዲሁ
እንደ እኔ አትሌት ይሆናሉ ብሎ ለመናገር
ገና ጊዜ ነው የሚሆው፤ አሁን ገና ልጆች
ናቸው….እንደዚህ ይሆናሉ ብሎ ለመደምደም
ያስቸግራል…ከፍ ሲሉ ፍላጎታቸው ሯጭ
መሆን አለመሆኑ የሚለይ ይመስለኛል ማለት
ብቻ ነው የምችለው…፡፡
ሀትሪክ፡- …አሁን…ከአንተ ጋር እንድገናኝ
ምክንያት ወደሆነኝ የበርሊን ማራቶን ጣፋጭ
ድልህ ዙሪያ እንወራ …ቀነኒሳ ወደ በርሊን ሲጓዝ
ምን አስቦ ነው…?…ከአዕምሮህ ለስከንድም
ቢሆን ሪከርድ ስለመስበር ያስበበት ጊዜ ነበር…?
ቀነኒሳ፡- …እውነት ለመናገር ስለሪ
ከርድ ቀርቶ ስለማሸነፍ እርግጠኛ አልነበ
ርኩም…፤…ምክንያቱም ረዘም ያለውን ጊዜ
በህመም ስሰቃይ ነበር ያሳለፍኩት።…ከዚህ
በፊት በሮጥኩባቸው ውደድሮች ላይም ጥሩ
አልሮጥኩም…ውድድር ያልጨረስኩበት
ሁኔታም ነው የነበረው……በዚህ ሁኔታ
ውስጥ ሆነህ ከአሸናፊነት በተወሰነ ርቀት ላይ
ተቀምጠህ ስለሪከርድ ማሰብ ከባድም ነው።…
እኔ ወደ በርሊን ስጓዝ ከተሳካልኝና የጤንነቴ
ጉዳይ ጥሩ ከሆነ ከዚህ በፊት የሮጥኩባቸውን
ሰዓቶች ለማሻሻል…፣…ብቃቴን አሣይቼ
ውድድሩን በጥሩ ሁኔታ መጨረስን አስቤ
ነበር የሄድኩት እንጂ…ስለሪከርድ…
ለስከንድም ቢሆን …አላሰብኩም…፡፡
ሀትሪክ፡- …በዚህ ሁኔታ የተጓዝው ቀነኒሳ
በቀለ…በውድድሩ ከማሸነፍ በዘለለ…ለሪከርድ
የቀረበ ሁለተኛውን የማራቶን ምርጥ ሰዓት
አስመዝግበሃል…በውጤቱ የእርካታን ጥግ
አግኝተሃል…?
ቀነኒሳ፡- …(ሳቅ)…እንደ ስፖርተኛ…
እንደ አትሌት…ያገኘሁት ውጤት መጥፎ
አይደለም…፤…በተለይ ለእንደ እኔ አይነቱ
ረዘም ያለውን አመት ከጉዳት ጋር
ሲታገል…፣…ከአሸናፊት ጋር ተጣልቶ
ለቆየ አትሌት ትልቅ ውጤት ነው…፡፡ …
በሌላ ጎንም ስታየው…የታሪካዊው የበርሊን
ማራቶንን አሸንፊያለሁ…ከዚህ በዘለለም
በታሪክ የተመዘገበ ሁለተኛውን የዓለም ምርጥ
የማራቶን ሰዓትን ነው ያስመዘገብኩትና…
አልተከፋሁም…በጣም ተደስቼያለሁ…ግን…
ሀትሪክ፡- …ግን…ምን…?
ቀነኒሳ፡- …ግን ለዓለም ሪከርድነት
ተጠግቼ ከምመለስ ሪከርዱን ሰብሬ የአለም
ሪከርድ ባለቤት ብሆን ደግሞ የበለጠ እደሰት
ነበር…ያም ቢሆን ግን በተገኘው ውጤት
አልተከፋሁም በጣምም ደስተኛ ነኝ…ለሪከርድ
ቀርበህ በ2 ሰከንድ ምክንያት ያንን ታሪክ
ባሳካው ኖሮ የበለጠ እደሰት ነበር ካላልኩ
በስተቀር በጣም ደስተኛ ነኝ አልተከፋሁም…፡፡
ሀትሪክ፡- …በሁለት ሰከንድ እንቅፋ ትነት
ሪከርድ ባለመሰበርህስ … ውስጥህ በቁጭት
አልተንገበገበም… ?
ቀነኒሳ፡- …ምንም ልደብቅህ አልፈል
ግም… እንኳን እኔን ዋናውን የጉዳዩን
ባለቤት ተወውና አንተንም ሌላውን ጉዳዩን
በቅርበት የተከታተሉትን ሁሉ ያንገበግባል
ይቆጫል…፤…የሚደርሱኝ አስተያየቶችም…
የምስማውም የሚያረጋግጠልኝ ይሄንኑ
ነው፡፡ ወደ እኔ ስትመጣ በማራቶን ሪከርድ
ለመሰበር ተቃርበህ በሁለት ሰከንድ ምክንያት
አለመስበር ማለት እውነቴን ነው የምልህ
በጣም ያማል…ያንገበግባል…ደግሞም በጣም
ይቆጭሃል…።…ነገሩ ካለፈ በኋላ በእኔም
ስሜት ውስጥ የተፈጠረው ይሄን አይነቱ
የቁጭት ስሜት ነው…፤…ግን ይሁን
የተባለውን የተፈቀደውን መቀበል ነው…፡፡
ሀትሪክ፡- …እስከ 37ኛው ኪ.ሜትር ድረስ
የነበረው አሯሯጥህ የሪከርድ ሰዓት ውስጥ
እንደነበርና ምናልባት አለም በማራቶን
ሌላ አዲስ ዜና እንደሚሰማ…ሩጫውን
የሚያስተላልፉት ኮሜንታተሮች ሳይቀሩ
በስሜት ይናገሩ ነበር… ከ37ኛው ኪ.ሜትር
በኋላ ምን ገጠመህ…?
ቀነኒሳ፡- …እውነት ነው እንዳልከው ነው
የነበረውሁኔታ…4ዐ ኪ.ሜትሩን እንዳለፍኩ
ትንሽ ጥሩ ስሜት አልተሰማኝም…ጉልብቴ
አካባቢ የህመም አይነት ስሜት ተሰምቶኝ
ነበር…፡፡…ከዚያ በኋላ ያለውን 2 ኪሎ
ሜትር አካባቢ ከሩጫው ጋር ብቻ ሳይሆን
ከህመሜ ጋር ጭምር እየታገልኩ ነበር ስሮጥ
የነበረው…፡፡…የህመም ስሜት ቢሰማኝም
ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ወይም ከራሴ ጋር
የተነጋገርኩት ነገር ምንድነው…ፍጥነቴን
መጨመር እንኳን ባልችል የያዝኩትን
ፍጥነት (ፔስ) ሳልቀንስ ውድድሩን መጨረስ
አለብኝ የሚል ነበር…።…መጠነኛ የህመም
ስሜት ከሩጫው ባልተናነስ በቀረው ኪሎ
ሜትር መፍታኑን ነው እንደ ምክንያት
የማነሣው፡፡
ሀትሪክ፡- …ግን…እኮ…ወደ መጨረ ሻው
መግቢያው አካባቢ 1 ሼ ሜትር አካባቢ ሲቀርህ
ወደ ሪከርድ ሰዓት ተመልሰህም ታይተሃል…
በዚህ ላይስ ምን ትላለህ…?…
ቀነኒሳ፡- …ትክክል ነው…ከተሰኝ የህመም
ስሜት ጋር እየታገልኩም ቢሆን ወደ 2ዐ እና
3ዐ ሜትር አካባቢ ሲቀረኝ ሰዓቴን ስመለከት
ለሪከርድ በጣም የቀረበ ስለነበር ያለኝን አቅም
አማጥቼ በመጠቀም ለመጨረስ የሚቻለኝን
ሁሉ አድርጌያለሉሀ…፤…3ዐ ሜትር አካባቢ
ሲቀረኝ የሪከርድ ሰዓት ውስጥ መሆኔን
በማወቄ የህመም ስሜቴን ለጊዜው ለመርሣት
ሞክሬ ፍጥነቴን ለመጨመር ጥሬያለሁ…
ያው…መጨረሻ ላይ አልሆነልኝም…እንጂ…፡
፡
ሀትሪክ፡- …ይሄንን ፍጥነቴን ምነው
ቀደም ብዬ ባደረኩት…የሚል የቁጭት ስሜትስ
ወደ አዕምሮህ መጠቶ አልረበ ሸህም…?…
ቀነኒሳ፡- …በጣም ይቆጭሃል…
ይረብሸሃል…መጨረሻ ላይ 2ዐ እና
3ዐ ኪ.ሜትር ሲቀረኝ ህመሜን ረስቼ
የጨመርኩትን ፍጥነት 5ዐዐ እና 6ዐዐ
ሜትር ወይም 1ሺ ሜትር አካባቢ ሲቀረኝ
ባደርገው ኖሮ አይደለም 2 የአምስት ሰከንድ
ልዩነት ላመጣ እችል ነበር…፤…
ግን ይሄን አላደረኩትም፡
፡ ካለፈ በኋላ እንዲቆጨኝ
ያደረገው 1ዐዐ % የራሴን
ጥረት ማድረግ እየቻልኩ
አለማድረጌ ነው…።…
1ዐዐ% ጥረቴን ባደረግ
ኖሮ የውጠቱ ታሪክ ሌላ
ሊሆን እንደሚችልም ነው
ካለፈ በኋላ የሚሰማኝ…፤…
እንደሰው…እዛ ደርሰህ…
ለሪከርድ ተጠግተህ…ስታጣው
ይቆጭሃል…፤…በሌላ
በኩል ግን የተመዘገበው
ነገር ቀላል
ባለመሆኑ
ብዙም
አልከፋም…ምክንያቱም እግዚአብሔር
ይሁን ያለው
የፈቀደው ብቻ ስለሚሆን
ባገኘሁት ነገር አልከፋም ደስተኛ
ነኝ…፡፡…ወደ ኋላ
ተመልሼ ሳስበው ማሸነፍ ራሱ ለአኔ
ሪከርድ የመሰበር ያህል በመሆኑ ተመሰገን
ነው የምለው…፤…አምላክ ጤንነቴን
ሰጥቶኝ ለዚህ ክብር፡፡ በመብቃቴ…፣…
ይሄንን ምርጥ ሰዓት
ማስመዝገቤ…፣…የአሸናፊነት ስነ ልቦናዬ
በመመለሱ ብቻ ለበጎ
ነው ብዬ መቀበልን መርጫለሁ…፡፡…
ሪከርድን አልሰበርኩም ብዬ
ከመቆዘም ይልቅ ወደፊት
እንዴት አሳካዋለሁ…?…
በሚለው ነገር ላይ
ነው ጊዜዬን ማጥፋት
የምፈልገው…፡፡
ሀትሪክ፡- …በበርሊኑ
ማራቶን ሪከርድ
ለመስበር የነበረህ እድል
በ2 ሰከንድ እንቅፋትነት
ከመክሸፉ…፤…በታሪክ
መዝገብ የመመዝገብ እድል
ከማሳጣቱ ውጪ ሌላ ነገር
እንዳሰጣህስ ልብ ብለሃል…?
ቀነኒሳ፡-… (እንደመገረም እያለ)…ሌላ…
ምን…አሳጣኝ…?…
ሀትሪክ፡- …የበርሊን ማራቶንን
በማሸነፍህ…ካገኘኸው 4ዐ ሺህ ዩሮ ወይም 1
ሚሊዮን 301 ሺህ 748 ብር ውጪ የአለም
የማራቶን ሪከርድ ብትሰብር ደግሞ በቦነስ
መልኩ 5ዐ ሺህ ዩሮ ወይም 1 ሚሊዮን 627
ሺህ 266 የኢትዮጵያ ብር 2 ሰከንድ እንዳሳጥህ
ታውቃለህ…?
ቀነኒሳ፡- …እኔ እንደ አንተ ካልኩሌተር
ይዤ ስደምር አልውልም…፤…ስለማሸነፍ
አዲስ ታሪክ ስለማፃፌ እንጂ ስላገኘሁትም
ሆነ አንተ ደምረህ ቀንሰህ የነገርከኝን ገንዘብ
ስለማጣቴ ለሰከንድም ትዝ አላለኝም…፡፡
…ወደ በርሊን ማራቶን ስሄድም የማገኘው
ገንዘብ ወይም በቦነስ መልክ የሚሰጠው
ገንዘብ አጓጉቶኝ አይደለም…፤…አንተ
አሁን የገንዘቡን ቁጥር ስትጠራው ብዙ
መስሎህ ይሆናል እንጂ…ከገንዘቡ በላይ
የሚያንገበግብውና የሚቆጨኝ በዘመኔ
ሌላ ተጨማሪ ታሪክ ለራሴም ለሀገሬም
አለማፃፌ ነው፡፡እኔ ስለ ስላጣሁት ገንዘብ
አላስብኩም ግምት ውስጥም አልከተትኩትም፡
፡ የማራቶንን ፈጣን ሰዓት ሮጠህ ሪከርድ
ሰብረህ የሚሰጠው ገንዘብ አንተ
እንደተገረምክበት ያን ያክል ትልቅ
የሚባል አይደለም…፤…እኔ
በበርሊን ማራቶን ለመሳተፍ
ስወስን ገንዘብ አግኝበታለሁ ብዬ
አይደለም…፡፡…እውነት ለመናገር
የበርሊን ማራቶን በጀት የለውም
በሚል የሚታወቅ በመሆኑ ሰዓት
ለማሻሻል እንጂ ገንዘብን ታርጌት
አድርገህ የምትሄድብት አይደለም፡፡
ደግሞም ገንዘብ ላይ ትኩረት ካደረክ
እኮ ከአዘጋጆቹ ወይም ከስፖንሰሮቹ
መደራደር ትችላለህ ፤ይሄን
ባደርግ ወይም ሪከርድ
ብሰብር ይሄን ያህል
ትሰጡኛላችሁ ብለህ
ትስማማለህ፤አዘጋጆቹ
ወይም ስፖንሰሮቹ
ሪከርድ እየተሰበረ
ሲሄድ ውድ እንደሆነም
ያውቃሉ።
ሀትሪክ፡-የበርሊንን ማራቶን ለአለም
ሪከርድ ባለቤትነት 2 ሰከንዶች ርቀት ላይ
ሆነህ በማሸነፍህ የአለም የማራቶን ሪከርድ
ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ
“…እንኳን ደስ አለህ…፤…በቀጠይም ሪከርዱን
እንደምትሰብር ተስፋ አለኝ” የሚል የደስታ
መልዕክት በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል…በሚል
ተዘግቧል… በኪፕቾጌ የደስታ መልዕክት ምን
ተሰማህ…?…
ቀነኒሳ፡- …እኔ እንደዛ ብሎ ትዊተር
ማድረጉን አላየሁም…፤…ሰዎች ናቸው
እንደዚህ ብሏል ብለው የነገሩኝ… ።የሰው ልጅ
መልካም ምኞት መመኘቱ ክፋት የለውም…
በመልካምነት የምታየው በደስታ ስሜትም
የምትቀብለው ነው…፡፡ …ግን ዋናውና ትልቁ
ነገር ኪፕቾጌ አለ የተባለው ከልቡ ከሆነ
በጣም ደስ ይለኛል… ከልቤም አመሰግነዋለሁ
ነው መልሴ…፤… ምኞቱ ከምለስ ብቻ
አይሁን ከለቡ ይሁን እንጂ።… (ሣቅ)…
ከልቡ ከሆነ…ክብር የምሰጠው መልዕክት
ነው …እግዚአብሔር ይሰጥልኝ…እንደአፉም
ያድርግልኝ ነው የምለው…(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …በርሊን ከሌሎች ማራቶን
ከሚካሄድባቸው ከተሞች በበለጠ በርካታ
ሪከርዶች የሚሰባበሩበት ከተማ ናት…፤…
ቀደም ሲል ብቻ ኃይሌ፣ ኪፕቾጌ አንተ በዚህች
ከተማ ሪከርድ ሰብራችሃል የተሻለ ሰዓትም
አስመዝግባችሃል …የዚህ ምስጢሩ ምንድነው
ማለት ይቻላል …?
ቀነኒሳ፡- …እኔ የተለየ ምስጢር አለው
ብዬ ለመናገር ይቸግረኛል ምናልባት…፤ …
እንዳልከው በተደጋጋሚ ሪከርድ ስለተሰበረባት
የተለየ ምስጢር አለው ሊያስብል ይችላል። …
ምንድነው…የበርሊን ማራቶንን ለእኔ የተለየ
የሚያደርገው…የምለው …የኮርሱ ፍላትነት
(የቦታው ምቹነት)…፣…ሜዳ መሆኑ፣ብዙ
ከርቭ (ጠመዝማዛ መንገዶች) አይበዙበትም፣
አየሩም ለሩጫ በጣም የተመቸ መሆኑ፣ነፋስ
የ ሚበዛበት አለመሆኑ ይመስለኛል በርሊንን
አትሌቶች ታሪክ እንዲሰሩበት ያደረገው …፤
…ግን ይሄ ብቻ አይደለም ሪከርድ እንዲሰበርና
የተሻለ ሰዓት እንዲመዘገብ ያደረገው …
የበርሊን ማራቶን ሜጀር ማራቶን ውስጥ
መግባቱ… በተደጋጋሚ በጣም ጠንካራ አት
ሌቶች ሪከርድ በ መ ስ በ ራ ቸ ው
የተለየ እንዲሆን አድርጎታል ብዬ
ነው የማስበው…፤ … ይሄን
ስልህ ሌላ ከተማ ሪከርድ የሚሰ
በርበት ሁኔታ አይኖርም ብዬ
አልደመደምም፤ምቹ የውድድር ቦታና ብቃት
ያለው ሰው ሌላ ቦታም ሪከርድ ሲሰብር
የምንሰማበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚቻል ነው
መናገር የምፈልገው፡፡
ሀትሪክ፡-.. የበርሊንን ማራቶን
ካሸነፉክ…፣…የዓለም የማራቶን ሁለተ
ኛውን ምርጥ ሰዓት ካስመዘገብክ በኋላ…
ስልክ ደውለህ…ደስታህን በትኩሱ ያጋራኸው
ለማነው…?…ለባለቤትህ ዳናዊት…?…ወይስ…?
ቀነኒሳ፡- …(ሣቅ)…ግምትህ ሠርቶል
ሃል… ትክልል ነህ…ከድሉ በኋላ የጋለውን
የደስታ ስሜቴን የተጋራሁት ከባለቤቴ
ዳናዊት ገ/እግዚአብሔር ጋርና ከልጆቼ
ጋር ነው…፤ …ምክንያቱም በአትሌቲክስ
ህይዋቴ በፈታኝነት ከማነሳቸው በጉዳት
በምስቃይበት ወቅት አብረውኘ ሲሰቃዩ፣
ሲጨነቁ፣ በፀሎት ፈጣሪያቸውን ሲለምኑልኝ
ስለነበር በትኩሱ ደስታዬን የተጋራሁት
ከእነሱ ጋር ነው። ከቤተሰቦቼ በተጨማሪ
የቅርብ ወዳጆቼ፣ ጓደኞቼ፣ማናጀሬ፣ መላው
የኢትዮጰያ ህዝብ አብሮኝ ሲጨነቅ እንደነበር
አውቃለሁ ለእነሱም የከበረ ምስጋና አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- … በርካታ ጊዜያትን በጉዳት
እንዲሁም ውድድሮችን እያቋረጥክ ስትወጣ
በመመልከታቸው ብዙዎች በአንተ ተስፋ
በመቁረጥ ለአሸናፊነት ለማጨት እንኳን
ሲጨነቁ ተስተውሏል …፤ …አንተ ግን ይሄንን
አመለካከት ሰብረህ ማሸነፍህ፣ሁለተኛውን
ምርጥ ሰዓት እስከማስመዝገብ መድረስህን ዛሬ
ላይ ሆነህ ስታየው ምን ትርጉም ይሰጥሃል..?
ቀነኒሳ፡- …ኦው…!…ይሄንን በቃላት
መግለፅ በጣም ይከብዳል …፤…ምክንያቱም
በአትሌቲክስ ህይወቴ እጅግ ፈታኝና
አስከፊ፣ ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያትን
አሳልፌያለሁ።ከስምንት አመታት በላይ
በጉዳት፣በህመም እየተሰቃየሁ ነው
ያሳለፍኩት …፤ …በህመም መሰቃየት ከጀመ
ርኩ ስምንት አመት አልፎኛል፡፡ ከሀገር
ውስጥ አልፌ ውጭ ድረስ ሄጄ ለመታከም
ሞክሬያለሁ፤ህክምና አድርጌ ተሻለኝ ብዬ
ስጀመር እንደገና ያገርሽብኛል …፤…በመሃል
እተወዋለሁ …እንደገና እሞክራለሁ…ተሻለኝ
ብዬ ተስፋ ሣደርግ እንደገና ይመለስብኛል…
በቃ ጉዳት እየተፈራረቀ ያስቸግረኝ ነበር፡፡
በአጭሩ በቃላት መግለፅ የማልችለው ፈተናን
ነው ያሳለፍኩት። አሁን ግን አምላክ በቃህ
ብሎኝ ጤንነቴ ተመልሶ ስሜ ከአሸናፊነት
ጋር መነሣቱ ለእኔ ሞቶ የመነሣት ያህል
የሚቆጠር ነው፡፡
ሀትሪክ፡-.. ስምንት አመት በጉዳት
መሰቃየት በእርግጥም ፈታኝ ነው…፤…ግን
በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ስታልፍ ለተስፋ
መቁረጥ እጅ ለመስጠት አልተቃረብክም…?…
ከዚህ ሁሉ ለምን አልተወውም…ለምን
አይበቃኝም?… ወደሚል መጥፎ ውሳኔስ
የደረስክበት አጋጣሚ አልነበረም…?
ቀነኒሳ፡- …በእርግጥ ነገሮች በጣም
ፈታኞች ነበሩ…በቀላሉ ለተስፋ መቁረጥ እጅ
እንድትሰጥ የሚያደርጉ…፣…ግን ፈተናዎች
ቢበዙም፣ ጉዳቱ ቢፈራረቅብኝም ተስፋ
ለመቁረጥ ልቤ አልተሸነፈም…፡፡ ምክንያቱም
ጉዳቱ ተፈታተነኝ እንጂ አቅሜን፣ ብቃቴን
ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ ለተስፋ መቁረጥ እጅ
እንድሰጥ ከማድረግ ይልቅ ጤንነቴ ከተመለሰ
ሌላ ታሪክ መስራት የምችልበት እድሉ እንዳለኝ
ነው ውስጤ ደጋግሞ የሚነግረኝ…፤…
እድሜዬም ገና 37 ውስጥ ነው… ይሄ ደግሞ
ይበልጥ የምትበስልበት ነው፡፡እየተመላለሰ
ያስቸገረኝ ጉዳትና በዙሪያም የነበረው ሁኔታ
ግን ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር…አሁን ግን
እግዚአብሔር ያንን የፈተና ጊዜ አስወግዶልኘ
ለዚህ በቅቻለሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- …በዙሪያዬ ተስፋ የሚያስቆ
ርጡ ነገሮች ነበሩ…ስትል…አንድ ነገር
ትዝ አለኝ…ለረዥም ጊዜ ከጉዳት
ጋር በመቆየትህ ውድድር ላይ
ገብተህ አለማሸነፍህ ብቻ ሣይሆን
አቋርጠህ በመውጣትህ ብዙዎች
ተስፋ ቆርጠውብህ.. “የቀነኒሳ
ዘመን አከተመ እሱ ጨርሷል..
አብቅቶለታል… ከዚህ በኋላ
አይመለስም…”የሚሉ በተስፋ
መቁረጥ የተሞሉ አስተያየቶች
ይደመጡ ነበር…አንተስ ይሄንን
ታዝበሃል… ?
ቀነኒሳ፡- …(እንደመሳቅ
እያለ)…በጣም እንጂ… አንተ
እንዳልከው ሰው ብቻ መሰለህ…
ተስፋ የቆረጠው…?…
ሀትሪክ፡-. …ሌላ ደግሞ…ማን
ተስፋ ቆረጠ…?…
ቀነኒሳ፡- …(ሣቅ)…አንተ ሰውን
ትላለህ እንጂ…ለረዥም አመታት
አብረውኝ የሰሩት ስፖንሰሮቼም ሣይቀሩ
ተስፋ ቆርጠውብኝ “…አይ የቀነኒሳ ነገር
Over (አበቃ)…ከዚህ በኋላ ወደ ቶፕነት
አይመለስም፤ ጨርሷል አብቅቷል…”ብለው
ተስፋ ከመቁረጥ አልፈው አግሪመንታችንን
(ስምምነታችንን) ሣይቀር ለመሰረዝ
ያሰቡበት አጋጣሚ ሁሉ እስከመፈጠር
ደርሶ ነበር፤ሁሉም ባይባልም በስፖርት
ቤተሰቡና አንዳንድ በዙሪያዬ ባሉ ሰዎችም
ተመሳሳይ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች ነበሩ፡፡
ከህመሙ በተጨማሪ እንደዚህ አይነት የተስፋ
መቁረጥ አመለካከቶችንም መስበር በፅናት
መታገል ይጠበቅብኝ ነበር፤ከእግዚአብሔር
ጋር ታግዬ አልፌ ለዚህ በቅቻለሁኝ፡፡
ሀትሪክ፡- …በእንደዚህ አይነት ፈተናዎች
አልፈህ ለተስፋ መቁረጥ እጅ ያልሰጠህበትን
ምስጢር ምንድነው ማለት እንችላለን…?…
ቀነኒሳ፡-…የጥንካሬዬ ምስጢሬ ሌላ
አይደለም…ብዙ ሰዎች በዙሪያዬ መኖራቸው፣
እኔም ለፈተና አለመንበርከኬና በፅናት
መታገሌ ነው፡፡ በተለይ ቤተሰቦቼ፣የቅርብ
ጓደኞቼ፣ማናጀሬ ጭምር የጥንካሬዬ
ምስጢሮች ናቸው፡፡ በተለይ ቤተሰቦቼ
በፈተናዬ በመሰናክሎችበተከበብኩ፣ ጉዳት
ወደ ተስፋ መቁረጥ እየገፋኝ ባለበት ወቅት
ተስፋ እንዳልቆርጥ፣በፅናት ተቋቁሜ ወደፊት
እንድጓዝ እገዛቸው በቃላት የማይገለፅ ነው፡
፡ የጓደኞቼ የማናጀሬ ድጋፍ ከፍተኛ እንደሆነ
ባምንም ቤተሰቦቼ በተለይ ባjለቤቴ “…ቀነኒሳ
በፍፁም ለፈተናዎች እጅ እንዳትሰጥ…፤…
ተስፋ ቆርጠህ እንዳትሸንፍ… እግዚብሔር
የሚሳነው ነገር የለም…፤…የአሸናፊነት
ቀን፣የአንተን የድል ቀን መልሶ
ያመጣዋል…”…እያለች ታበረታታኝ ነበር፤
ተስፋ የጠፋ በመሰበት ሰዓት ተስፋ ሆነው
ስላገዙኝ ቤተሰቦቼን ጓደኞቼንና ማናጀሬን
ከልብ ለማመስገን እወዳለሁኝ። ማናጄሬ በእኔ
ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እቅሜን ተረድቶ
አብሮኝ ያንን አስቸጋሪ ወቅት ከማለፍ በዘለለ
የተሻለ ህክምና እንዳገኝ እስከማገዝ ሁሉ
ደርሷል፤የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶችም
ናቸው የጥንካሬዬ ቁልፍ ምክንያቶች፡፡
ሀትሪክ፡-አሁን ከረጅም ጊዜ ጉዳትና
ከውጤት ማጣት በኋላ በርሊን ላይ ከማሸፉ
በዘለለ ሁለተኛው የአለም ምርጥ የማራቶን
ሰዓት አስመዝግበሃል…፤…ባለቤትህ “…
የአሸናፊነት ቀን ፤የአንተ የድል ቀን ተመልሶ
ይመጣል…” ያላችው ያ ቀን በርሊን ላይ መጣ
ማለት ይቻላል…?
ቀነኒሳ፡- …(ሳቅ)… አዎን ይቻላል…
በትክከልም ያ ቀን በርሊን ላይ መጥቷል
ቢባልም ስህተት ያለው አይአመስለኝም…፤…
ዛሬ ላይ ሆኜ ሣየው ባለቤቴ በወቅቱ “…
የአንተ የአሸናፊነት፤ የድል ቀን…” ደመጣል
ብላ የተናገረችው ንግግር ሣይሆን የትንቢት
ያህል ነው፡፡ ምከንያቱም በጉዳት፣ በውጣ
ውረዶች፣ በፈተናዎች ሲሰቃይ ለነበረው
ቀነኒሳ በአለም ማራቶን ሁለተኛውን ምርጥ
ሰዓት አስመዝግቦ በማሸነፉ ታሪክ የሰራበት
በመሆኑ በእርግጥም ያ ቀን መጥቷል።
በአለም ላይ ካሉት ሁሉ ይሄንን ምርጥ
ሰዓት የያዝን ሁለት ሰዎች ብቻ ነን…ሌላው
3ኛው ሰው ከአንድ ደቂቃ በላይ ርቀት
በመሆኑ በእርግጥ ያ ቀን ለመመለሱ ማሳያ
ነው…፤…ተስፋ ያደረግንበት እግዚአብሔር
ጤንነቴን ብቻ ሳይሆን ያንን የተባለውን ቀን
መልሶ በታሪክ መዝገብ ላይ ስሜን በማፃፌ
በጣም ደስ ብሎኛል፤ በዚህ አጋጣሚ ይሄ ቀን
እንደሚመለስ ለተስፋ መቁረጥ እንዳልንበርከክ
በሃሣባቸው፣ በፀሎታቸው ላገዙኝና ከጎኔ
ለቆሙት ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ፣ ማናጀሬና
ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ምስጋና
አቀርባለሁ፤ ይሄንን ቀን በጋራ በማየታችን
ደስታዬ መጠን የለውም ለማለት እወዳለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …Breaking 2 የሚል ማራቶንን
ከ2 ሰዓት በታች በመግባት ላይ ያነጣጠረ
ፕሮጀክትን ናይል የተባለው ትጥቅ አምራች
ድርጅት የወቅቱ የማራቶን ሪከርድ ባለቤት
የሆነው ኪፕቾጌ፣ ኤርትራዊው ዘረሰናይና ሌሊሳ
ዴሲሳ ሲታቀፉ አንተ በማራቶን የተሻለ ሰዓት
እያለህ እዚህ ፕሮጀክት ውጥ አልታቀፍክም…
ምክንያቱ ምንድነው፡፡ ?
ቀነኒሳ፡- …በወቅቱ ምን መሠለህ እኔ
ገና ወደ ማራቶን የመጣሁበት ጊዜ ነው በዚያ
ላይ ጥሩ የሚባል ውጤትም አላስመዘገብኩም
ነበር…፤…ምናልባት ዘረሰናይ ካልሆነ በስተቀር
ኪፕቾጌና ሌሊሳ በወቅቱ ጥሩ ውጤት ያላቸው
በዓለም ላይ በውጤታማነት ስለሚታዩ ናይክ
በዚያ መሠረት ነው የመረጣቸው፤ ከዚህ
በተጨማሪ ከናይክ በፊት ይሄንን Breaking
ወይም Sab2 የሚለውን ማራቶንን ከሁለት
ሰዓት በታች መግባት የሚለውን ፕሮጀክት
ቀድሞ ከጀመረው ፕሮፌሰር ጋር የጀመርኩት
ነገር ስለነበር በእነዚህ መሰረታዊ ምክንያቶች
በዛ ፕሮጀክት ውስጥ አልታቀፍኩም፡፡
ሀትሪክ፡- …እንዴ…!ቀነኒሳ Breaking2
የሚለውን ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የመግባት
ፕሮጀክት ሌላ ሰው ነበር የጀመርከው እያልከኝ
ነው…?
ቀነኒሳ፡- …ይሄንን ሃሣብ ያመጣው
እንግሊዝ ሃገር የሚኖር…በዩኒቨርሲቲ
ውሰጥ የሚያስተምር…ጥናትና ምርምር
የሚያደርግ ግሪካዊ ፕሮፌሰር ነው መጀመሪያ
ሃሣቡን ያመጣው…፤…ከዚህ ፕሮፌሰር
ጋር በጉዳቴ ምክንያት ነበር የተገናኘነውና
Sub2 የሚለውን የሰው ልጅ ማራቶንን
ከ2 ሰአት በታች መግባት አለበት የሚል
ሃሣብ ይዞ ተነሣ…፡፡ …ፕሮፌሰሩ ይሄንን
ሃሣብ ለማምጣት ምክንያት የሆነው ሁሌም
በማራቶን የሚመዘገበው ሰዓት፣ የአሯሯጡ
ዘይቤ ተመሳሳይ በመሆኑ “…ለምን ይሄ ነገር
አይለወጥም…፣…የሰው ልጅስ ከ2 ሰዓት
በታች እንዴት አይገባም…?”… ከሚል ተነስቶ
ነው ሃሣቡን ያመጣው…፣…ይሄ ነገር ናይክና
አዲዳስ ጋር ደረሰ…ናይኪ ደግሞ አቅሙም
በጀቱም ስላለው የሄንን የፕሮፌሰሩን ሃሣቡን
ኮፒ አድርጎ ወደዚህ ፕሮጀክት ውሰጥ ተገባ፡፡
ማራቶንን ሰህት ተፈጠሮአዊው በሆነው መነገድ
እንጂ ከቴክኖሎጂ ታግዞ ማሸነፍ ተፈጥሮአዊነቱን
ጣዕሙን ያስጠዋል ይላሉ ቀነኒሳስ በቴክኖሎጂ
ተደግፎ ማሸነፉ ምን ስሜት ይሰጠዋል…?
ቀነኒሳ፡- …አሁን ተፈጥሮአዊ በሆነው
መንገድ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለመግባት
የመቃረብ ነገር ታያለህ፤ የሰው ዘር ከ2 ሰዓት
በታች ለመግባት ይቸገራል በሚለው ነገር
ብዙም አልስማማም፤ተስፋ በቀላሉ መቁረጥም
አልፈልግም፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ይልቅ ይሄንን
እድል አንድ ቀን አገኘዋለሁ ብዬ ነው ተስፋ
የማደረግው። ግን እኔ የማራቶንን ሪከርድ
መስበር ወይም ከ2 ሰዓት በታች በመግባት
ታሪክ መስራት የምፈልገው ኦፌሺያል
ያልሆነ በIAAF እውቅና በሌለውና በታሪክ
የክብር መዝገብ በማይመዘገብ ቦታ ላይ
መወዳደር ብዙም አይዋጥልኝም፤ እንዳልኩህ
በIAAF እውቅና አግኝቶ በይፋ በታሪክነት
በሚመዘገብበት ተቀባይነት ባለው ቦታ ላይ
መሞከሩ ይበልጥ ያስደስተኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ኬንያዊው ኤሊዮድ ኪፕቾጌ
በቴክኖሎጂ ታግዞ አዲስ የማራቶን ሪከርድን
በIAAF ባይመዘገብም 1:59 በመግባባት አዲስ
ውጤት አስመዝግቧል፡፡ በቀጣይ ኦፌሺየል
በሆኑ ውድድሮች ከ2 ሰዓት በታች በመግባባት
የአዲስ ሪከርድ ባለቤት የሚሆነው ማን
ይመስልሃል…?…የእኛው…ቀነኒሳ…?…ወይስ?
ቀነኒሳ፡- …አዲስ ሪከርድ መስበር
የማይፈልግ አትሌት የለም…፤…የእኔም
ምኞት ከዚህ የራቀ አይደለም ግን አሁን
እንደዚህ ነው ማለት አልችልም፤በቀጣይ
ዝግጅቴን አጠናክሬ መቀጠልና ለዚህ
ክብር የሚያበቃ ሥራ ላይ ማተኮርን ነው
የምመርጠው፡፡ ከአራት ከአምስት ወር በኋላ
ባሉ የማራቶን ውድድሮች በአንዱ እሮጣለሁ
ብዬ ነው ለጊዜው የማስበው፤ ሌላውን ጊዜው
ሲደርስ አብሮ ማየቱ የሚሻል ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ከፊታችን የቶኪዮ ኦሎምፒክ
አለ፤የቀነኒሳ አዕምሮ ከወዲሁ ስለ ቶኪዮ
ኦሎምፒክ ማሰብ ጀምሯል…?
ቀነኒሳ፡- …እ…(ሳቅ)…ከወዲሁ ስለ
ቶኪዬ ኦሎምፒክ ማሰብ በጣም አስቸጋሪ
ይመስለኛል…፤…ምክንያቱም የቶኪዩ
ኦሎምፒክ ገና ከአንድ አመት የበለጠ ጊዜ
ስለሚቀረው ዛሬ ላይ እንዲህ ብሎ መናገር
ከባድ ነው፡፡ በኦሎምፒክ መሳተፍ ብሎም
ታሪክ መስራት የሁሉም ምኞት እንደሆነ
ሁሉ መሳተፍ ብሎም ታሪክ መስራት
የሁሉም ምኞት እንደሆነ ሁሉ የእኔም ምኞት
ነው፤ ግን ጊዜው በጣም ገና በመሆኑ ዛሬ ላይ
ሆኖ መናገሩ ደግሞ ከባድ ነው፤እስቲ ጊዜው
ይቅረብና ያኔ እናውራበት፡፡
ሀትሪክ፡- …እስቲ አሁን ደግሞ በቅርቡ ዶሀ
ላይ ተካሄዶ ስለተጠናቀቀው የአለም ሻምፒዮና
እናውራ…፤…ቀነኒሳ ዶሀ ላይ የተገኘውን ውጤት
እንዴት አገኘኸው…?
ቀነኒሳ፡- …ውጤቱ በጣም ደስ
ይላል…፤…ግን ደግሞ የተጠበቁ ኢቬንቶችም
ላይ የተጠበቀው ውጤት አልመጣም፤
በተቃራኒው ደግሞ ባልተጠበቁ ኢቬንቶች
ላይ ያልተጠበቁ ውጤቶችንም አይተናል፤ይሄ
በጣም ደስ ይላል፡፡ ከዚህ ውጪ የዶሀው
የዓለም ሻምፒዮናው አዳዲስ ልጆችንም ያሳየን
ሻምፒዮና ነው፡፡ በአምስት ሺህ ወንዶች
ሙክታርና ሠለሞን ባረጋ ያስመዘገቡት
ውጤት ታሪካችንን የበላይነታችንን ያስጠበቀ
አስደሳች ውጤት ነው፡፡ ሶስት ሺህ ሜትርም
ያልጠበቅነውን ጥሩ የሚባል ውጤት
አግኝተንበታል፡፡ በአጠቃላይ ብዙ መስራት
እንዳለብን የሚጠቁሙ ነገሮች ቢኖሩም
መልካም የሚባል ውጤት ተመዝግቧል ብዬ
ነው የማስበው፡፡
ሀትሪክ፡- አንተ አሁን ትልቅ ውጤት
ያስመዘገብክበትና በምትወዳደርበት ማራቶን
የተመዘገበው ውጤትስ ምን ተስፋ ሰጠህ?
ቀነኒሳ፡- …ኦው…ማራቶን ላይ በጣም
ትልቅ ውጤት ነው የተመዘገበው…፤…
ከሩጫው በላይ በጣም አስቸጋሪ የነበረውን
ሙቀት ተቋቁመው ይሄንን ውጤት
ማስመዝገብ መቻላቸው ለሌሊሳም ለሙስነት
ገረመው ትልቅ ክብር የሚያሰጥ አስደሳች
ውጤት ነው፡፡ብዙዎች እንደተደሰቱት ሁሉ
እኔንም በጣም አስደስቶኛል፡፡ ምክንያቱም
በማራቶን በአለም ሻምፒዮና 1ኛ እና 2ኛ
ከወጣን ብዙ አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይሄንን
ብዙ አመት ያስቆጠረን፣ የጠፋን ውጤት ወደ
ሀገር ቤት እንዲመለስ በመደረጉ ለአትሌቶቹ
ክብርና አድናቆት አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- .. በእናንተ ለመዘናት ተከብሮ
የቆየው የ10 ሺህ ሜትር ውጤትንስ እንዴት
ታዘብከው…?
ቀነኒሳ፡- .. ዮሜፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ ነው
የወጣው…ይህ ውጤት ለእኔ መጥፎ የማይባል
በጣም ጥሩ ውጤት ነው፤ምክንያቱም ዮሜፍ
በዓለም ሻምፒዮና ላይ በ10 ሺህ ሜትር
ሲካፈል የመጀመሪያው ከመሆኑ አንፃር።
ዮሜፍ እምነት የምትጥልበት ልጅም
ነው፤በርቀቱ ወርቅ ስላላመጣ ወይም ወርቅ
ብቻ በሀገራችን ትልቅ ዋጋ ስለሚሰጠው
እንጂ ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ደግሞም እኮ
አንድ ነገር ማወቅ አለብን ሁልጊዜ ወርቅ ብቻ
ላይገኝ ይችላል፤ ከቦታው፣ ከሙቀቱ አንፃር
ስናመዛዝነው ትልቅ ውጤት እንደመጣ
ለመረዳት አይቸግርም። 10 ሺህ ሜትር
በዚያ ሙቀት በጣም በፈጠነ ፔስ ይሄንን
ውጤት ማግኘታችን በጣም ሊያስደስተን
ነው የሚገባው፡፡ እንደ እኔ አሁንም ማለት
የምፈልገው የተመዘገበው ውጤት መጥፎ
አይደለም በቀጣይ ግን በደንብ ተዘጋጅቶ
በበላይነት እንዲያጠናቀቅ ማገዝ ነው ያለብን፡፡
ሀትሪክ፡-በርሊን ላይ ካሸነፍክ በኋላ ለዜና
ሰዎች በሰጠኸው መግለጫ “ማራቶን ወደ ቤቱ
ይመለሳል” ብለሃል በእርግጠኝነት ይሄ ይሆናል…?
ቀነኒሳ፡- …እንዴ ምን ሆነሃል…?…አዎን
በደንብ ይመለሳል…አሁንም እኮ የማራቶን
ሪከርድ በአንድ ሰው መያዙን ካላነሳን
በስተቀር አሁንም ማራቶን ከቤቱ ከኢትዮጵያ
አልወጣም፡፡ በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች
በማሸነፍ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በተለይ
በዚህ አመት የኢትዮጵያዊያንን ያህል
ቀዳሚነቱን የያዘ የለም፤ይሄ የሚያስደስት
ነው፡፡ ሪከርዱ እንጂ ማራቶን ከኢትዮጵያ
አልወጣም፤አትጠራጠር ሪከርዱም ጊዜ ወደ
ቤቱ ይመልሰዋል… (ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- ..አዘወትረህ መመገብ የምትመ
ርጠው የምትወደው ምግብ…?
ቀነኒሳ፡- …በተናጠል ጠርቼ ይሄን
ነው የምወደው ምግብ የለኝም፤ምክንያቱም
የምመገባቸውን ምግቦች ኒውትሪሺኒስቶቼ
በሚያዘጋጁልኝ መሠረት ነው የምመገበው።
በየዕለቱ የተለያዩ ምግቦች ስለሚዘጋጁልኝ
በተለይ የምመርጠው የለም፡፡
ሀትሪክ፡- …እሺ የማይመችህ…በምግብ
ምርጫህ ላይ እንዲቀርብ የማትፈልገው ምግ
ብስ…?
ቀነኒሳ፡- …(ሣቅ)…የማይመቸኝ ምግብማ
ለምን ይቀርብልኛል…? …የማልፈልገው
ምግብ እንዲቀርብልኝ አላደርግም…፤…ከቀረበ
ደግሞ አይቼ የመተው መብቱ እጄ ላይ ነው
(ሣቅ)
ሀትሪክ፡- …በመጨረሻ ማለት የምትለው
ካለ እድሉን ልስጥህ…?
ቀነኒሳ፡- …በጉዳቴ፣ በፈተናዎች ተስፋ
ባጣሁበት ጊዜ ተስፋ ሆነው ከጎኔ ለቆሙት ለእኔ
ለተጨነኩት ከራሣቸው በላይ ለእኔ ለፀለዩት
የዛሬዋን የአሸናፊነት ቀን እንድትመለስ ተስፋ
አድርገው ከጎኔ ላልተለዩት ለደገፉኝ በሙሉ
ከልብ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ለማለት እወዳለሁ፡፡ አንተም እንግዳህ
ስላደረከኝ እንደዚሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …ቀነኒሳ ውድ ጊዜህን ሰውተህ
ለእኔም ለአንባቢዎቼ ክብር ሰጥተህ ለቃለ-
ምልልሱ ስለ ተባበርከኝ ከልብ አመሰግናለሁ፡
፡ በቀጣይም ስምህ ዳግም ከፍ የሚልበት
የአንተም የሀገርህም ስም በሌላ ድል በሌላ
አዲስ ታሪክ እንዲጠራ ምኞቴ ነው፡፡