በፋሲካ በዓል ምክንያት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ቀኗን ጠብቃ ዛሬ ለመውጣት ባለመቻሏ ይቅርታ እየጠየቅን ነገ ረቡዕ ግን በገበያ ላይ ትውላለች፤ እንዳታመልጦት
ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በበዓል ምክንያት ዛሬ ባትወጣም ነገ ረቡዕ ግን ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የሚወዷቸውን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ እንድታነቧትም ጋብዘንዎታል፤ ሀትሪክ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ ይዛሎት የምትቀርበው ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ስኬታማ ውጤት እያስመዘገቡ ከመጡት ክለቦች መካከል ለኢትዮጵያ ቡና በተከላካይ ስፍራ እየተጫወተ የሚገኘው ኤፍሬም ወንድወሰን በክለቡ ዙሪያ ለቀረቡለት ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽን የሰጠ ሲሆን ከእነዚያ ውስጥ ‘‘ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወት ዳኞች ይደነግጣሉ” የሚል ምላሽን ሰጥቷል፤ ሌላው በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ በመሳተፍ ላይ ካሉት ሁለቱ ክለቦቻችን መካከል ለቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የሚጫወተው በኃይሉ አሰፋ /ቱሳ/ ቡድናቸው የኮንጎውን ክለብ ካራ ብራዛቪልን ድል ካደረገበት ጨዋታ በኋላ ስለ ግጥሚያው እና በመልሱ ጨዋታ ምን ውጤት ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ የሰጠው ምላሽ ይገኝበታል፤ ሀትሪክ በነገው እትሟ ሌላ የምታስነብቦት ፋሲል ከተማን ለማሰልጠን ሰሞኑን ከስምምነት ላይ የደረሰውና ስራውን የጀመረው የቀድሞው የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስለአዲሱ ክለቡ፣ ስለሙያውና ሌሎችንም ጉዳዮች አካቶ ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ይገኝበታል፤ አሰልጣኝ መሳይ ከተናገረው ውስጥ ‘‘ከተጨዋቾች ገንዘብ መቀበል ቡኩርናን የመሸጥ ያህል ነው የሚል ይገኝበታል፤ በሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው እትም ሌላ ይዘንሎት ከምንቀርበው ዘገባ ውስጥ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ ዓምዳችን ላይ በእዚህ እትም ይዘንላችሁ የምንቀርበው ተጨዋች በክለብ ደረጃ ለኢትዮጵያ ቡና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለሰሚትና ለወንጂ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈውን ሳምሶን ሽፈራው /ጆሮን/ ሲሆን ተጨዋቹ በአስገራሚና አዝናኝ በሆነው የኳስ ሕይወቱ ዙሪያ የሚወዷቸውን ምላሹን ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገ ለእናንተ ልታስነብቦት ከተዘጋጀችው መረጃዎች ውስጥ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ስለሚከናወኑት የጁቬንቱስና የሪያል ማድሪድ እንዲሁም ስለባየር ሙኒክና ሲቪያ የመልስ ጨዋታን አስመልክተን እንደዚሁም በአሁን ሰዓት የሳምንቱ መነጋገሪያ ስለሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሰፊና የሚወዱት መረጃን ይዘንሎት የቀረብን ሲሆን ሌላው በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ክለቡን ለስኬት ስላበቃው የማንቸስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ እና ለአርሰናል የማሸነፍ ጉዞ አስገራሚ ብቃቱን እያሳየ ስላለው ዳኒ ዌልቤክ ይዘነው የቀረብነው ዳሰሳ ይጠቀሳል፡፡ሀትሪክ የእናንተ ናት ያንብቧት ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
በፋሲካ በዓል ምክንያት ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ቀኗን ጠብቃ ዛሬ ለመውጣት ባለመቻሏ ይቅርታ እየጠየቅን ነገ ረቡዕ ግን በገበያ ላይ ትውላለች፤ እንዳታመልጦት
Managing Editor at Hatricksport Website