“ቀነኒሳን መቀነስ አይደለም በአንድ እግሬ እንኳን
ልሩጥ ቢለኝ እሺ ለማለት ሁለት ጊዜ አላስብም”
* “ፊዚካልንና ሜንታልን እኩል ማሰራት ከቻሉ
አትጠራጠር የእኛ ልጆች ሞ ፋራህን ያሸንፉታል”
የትራክ ንጉስ ነው፡፡ በሩጫ ዘመኑ
ሪከርዶችን በሙሉ እንደማገዶ ሰባብሯቸዋል፤
ሪከርዶች በሙሉ ለእሱ ፀጥ ለጥ
ብለው ተገዝተዋል፡፡ የአለም አትሌቲክስ
በውጤታማነታቸውና በንጉስነታቸው ሁሌም
የማይዘነጋቸውና ሲያስታውሳቸው ከሚኖሩ
አትሌቶች አንዱ ነው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ
አትሌቲክስ በሙያው ባለፉ የስፖርቱን
ቋንቋ አቀላጥፈው መናገር በሚችሉ ሰዎች
መመራት አለበት የሚል የጠነከረ አቋም ይዞ
በመታገል አዲስ የለውጥ አብዮት የፈጠረውና
በአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ የምስረታ ታሪክ
ፌዴሬሽኑን ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሬዚዳንትነት
የመራ አትሌትም ለመሆን በቅቷል፡፡
ወደ አትሌቲክሱ ወንበር ያመጣኝ
እልህና ቁጭት እንጂ የወንበር ጥማት
አይደለም የሚለው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ
በፕሬዝዳንትነት የተቀመጠበት ወንበር ከመ
መቸቱ ይልቅ ክፉኛ ይፋጃል በማለትም ይና
ገራል፡፡
ከዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን
/IAAF/ እና ከሻምፒዮናም አዘጋጅ ሀገር ኮሚቴ
/LOC/ በስሙ የቀጥታ ግብዣ የመጣለት
የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ
ይስሐቅ በላይ የአዲስ አበባን መሬት
ለቆ ወደ ለንደን ከመብረሩ በፊት ከጀግናው
አትሌት ጋር ለአለም ዋንጫው ስለተደረገው
ዝግጅት፣ ስለቀነኒሳ በቀለ መቀነስ፣ ከውድድሩ
ምን እንደሚጠበቅና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች
ዙሪያ ጣፋጭ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንት
ኃይሌ ለሀትሪክ አንባቢያን ጥያቄ ዋጋና
ክብር ሰጥቶ ስላስተናገደን በአንባቢያን ስም
እናመሰግናለን፡፡
——————————–
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ
ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነህ ወደ ስልጣን
ከመጣህ ስምንት ወር ጨርሳችሁ ወደ
አንደኛው ዓመት እየተጓዛችሁ ነው…
ኃይሌ፡- /ድንገት አቋረጠኝና በፈገግታ
ታጅቦ/… ስምንት ወር ሞላን… እንዴ?…
እንዴት ጊዜው ይሮጣል ባክህ…?
ሀትሪክ፡ …እንዴት ዘነጋቨው ክቡር ፕሬዝ
ዳንት…? …መቼም… የጊዜን ጉዳይ… ከአንተ
በላይ የሚያውቀው… አለ ብዬ አላስብም…፤
አሁን ስምንተኛ ወራ ችሁን ጨርሳችሁ ወደ
አንደኛ ዓመት እየተጠጋችሁ ነው…ለመሆኑ
ለስምንት ወራት የተቀመጥክበት የፌደሬሽኑ
ወንበር ይፋጃል…?…ወይስ…የተደላደለና ምቹ
ነው?
ኃይሌ፡- /እየሳቀ/… አይ ምቹ…!…
ምንድ ነው… የሚባለው… እሳትን
በተመለከተ… አንድ የሚባል ነገር አለ…
ሀትሪክ፡- … ምንድነው… አስታውሰኝ…
እስቲ…?
ኃይሌ፡- …“እሳት ከሩቅ ይሞቃል…
ሲጠጉት ይፋጃል…” …የሚባል አባባል
አለ… የፌዴሬሽኑም ወንበር እንዳዛው ነው…
ከሩቅ ስታየው የሚሞቅ ነበር የሚመስለው…
ተጠግቼ ስቀመጥበት ግን… በጣም ነው
የሚፋጀው… (በጣም እየሳቀ)
ሀትሪክ፡- በፕሬዝዳንትነት ስምንት
ወራትን ያስቆጠረው የቀድሞው ውጤታማ
አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ ምን አይነት ፕሬዘዳንት
ነው…?… አምባገነን…? …ዲሞክራት…?
ወይስ ለዘብተኛ…?
ኃይሌ፡- (እየሳቀ)…Both… (ሁሉንም)…
ሀትሪክ፡- …ማለት…?
ኃይሌ፡- …በፊት… በፊት… ገና
ወደ ስልጣን እንደመጣሁ… ዲሞክራት…
ወይም ለዘብተኛ… የምትለው አይነት
ነበርኩኝ… አሁን አሁን ግን እንደ አትሌቲስስ
ፌዴሬሽን ሶስቱንም እንደ አስፈላጊነነቱ፣
እንደየቦታው የሚጠቀም ፕሬዝዳንት እየሆንኩ
ነው፤ በፊት የነበረው እምነቴ በማባባል፣
በማግባባት፣በማስተማር ወደ ተሻለ ነገር
መሄድን ነበር የማስቀድመው፤ በዚህ ርቀት
ብዙ መጓዝ እንደማይቻል የገባኝ ወዲያውኑ
ነው፡፡ ምክንያቱም አትሌቲክሱ ባለፉት ሰባትና
ስምንት ዓመታት ትንሽ ለቀቅ ያሉ ነገሮች
ነበሩበት። ሁሉም ነገሮች ለቀቅ ያሉ ሰነለበሩ…
“ተወው” ማለት ጀመሩ። አትሌቲክሱ አካባቢ
ይሄንን ለዘብተኛ ወይም ዲሞክራት ብቻ
ሆነህ አታስካክለም፤አንዳንዴም ኮስተር ማለት
ይኖርበሃል፡፡ ሲያስፈልግም አረንጓዴውን
መፅሐፍ ገለፅ ገለፅ እያደረግን፤ ህግና አንቀፅ
እየጠቀስን መጓዝ ግድ የሚሆንበት ሁኔታ
አለ፤ ስለዚህ ከሶስቱም እንደ አስፈላጊነቱና
እንደ ሁኔታው እጠቀማለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ህይወት ከሩጫው በኋላ
በፕሬዝዳንትነት ምን ይመስላል?
ኃይሌ፡- …ኦው…! በጣም ከባድና
አስቸጋሪ ነው፤ ያው እንደምታየኝ በጠዋት
አዲስ አበባ ስቴዲየም ተገኝቼ የልጆቻችንን
ዝግጅት እየተከታተልኩ ነው፤ ማታም በጊዜ
ወደ ቤት መግባት የለም፤ ከእኩለ ሌሊት በፊት
አልጋ ለይ ጋደም ብሉ ማረፍና ህልም ማለም
ሁሉ ቀርቷል፡፡ ምክንያቱም ከአምስት ሰዓት
በኋላ ነው ወደቤት የምገባው፤ አትሌቲክሱ
ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ ጫና እንደፈጠረብኝ
መካድ አልፈልግም፡፡ ከዚህ ውጪ በግሌ ደግሞ
የማከናውናቸው በርካታ ቢዝነሶች አሉኝ፤
እዛም መሪ ነኝ። ስብሰባ አለ፣ ቤተሰባዊ ጉዳይ
አለ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ሃይሌን ፋታ
አሳጥተውታል፡፡ ያም ቢሆን ግን የህዝብ አደራ
ነውና አትሌቲክሱም ህዝብ የሚደራደርበት
ባለመሆኑ ነፍስ ውጪ ግቢ ቢሆንብኝም የግል
ቢዝነሴንም ደቆስ አድርጌ ኃላፊነቴን ከሌሎች
አመራር ጓደኛቼ ጋር በጋራ በመሆን ለመወጣት
እየጣርኩኝ ነው።ከላይ ከጠቀስኩልህ ውጪ
በርካታ የውጪ ጥሪዎችም አሉኝ፤ አሁን
ራሱ የለንደን የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮናን
አስመክልቶ ሲምፖዚየም ነበረብኝ፤ ነገር ግን
ከአገሬ አይበልጥም ብዬ በጊዜ ችግር ምክንያት
ሰርዤዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እዚህ ጋር እንቅልፍ
የማይወስድ ኃላፊነት ስላለብኝ እንዲሁም
ስለማያስችለኝ ውሎና አዳሬ ስቴዲየም ውስጥ
ሆኗል ማለት እችላለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- … ግን ሃይሌ ሀትሪክ ጋዜጣን
ጨምሮ… ጥቂት የማንባል ሰዎች… ለፕሬ
ዘዳንትነት ወንበር… መሮጥህን በጣም
ተቃውመን፤ ተችተን ነበር…?
ኃይሌ፡- … (እየሳቀ) ጥይቄህ ይስተካ
ከል… ሃይሌ ለሪከርድ… ወይም ለሜዳሊያ…
እንጂ ለወንበር አይሮጥም… (አሁንም ሳቅ)
ሀትሪክ፡- ለሪከርድና…. ለሜዳልያ
መሮጥህ የማይካድ ነው… ፤ ለፕሬዝዳንትነት
መወዳደርህን ግን በተለይ እንደ ሀትሪክ
አጠንክረን ተቃውመናል፤ ምክንያቱም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሃይሌ ፕሬዜዳንት
ሳይሆን በፊትም ከእነ ችግሩም ቢሆን
ውጤት ነበረው፤ አሁን ኃይሌ ፕሬዝዳንት
ሆኖም የሚለወጥ ነገር አይኖርም፤ ከዚህ
ሀቅ መነሻነት ኃይሌ ለፕሬዝዳትነት ወንበር
ከሚሮጥ ይልቅ ለምን ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ
ፈጣሪነቱን ተጠቅሞ ለአገሩና ለአትሌቲክሱ
ጥቅም በሚሰጥ ነገር ላይ አይሮጥም የሚል
የከረረ ተቃውሞ ነው ያለን፤ ይሄንን የጠነከረ
ተቃውሞ እንዴት ነው የምታስተናግደው…?
ኃይሌ፡- አሁንም ኃይሌ ፕሬዝዳንት
ሆኖ እየሰራ ያለው ለአገሩና ለአትሌቲክሱ እኮ
ነው… ! …ወንበር ለእኔ ምኔም አይደለም፤
እኔ ሁሌም አንድ የማይገባኝ ነገር አለም
አቀፋዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነቱን ተጠቅም ሲባል
ምን ማለት ነው…? …እኔ በግሌ ብንቀሳቀስ
ብቻዬን ምን እፈጥራለሁ? ይልቁንስ ይበልጥ
ተጠቃሚ የሚያደርገንን ስራ ለመስራት እንደ
አገር ወይም እንደ ፌደሬሽን ብንንቀሳቀስ
ነው የሚመረጠው፤ በግሌ የተለያዩ
ጥያቄዎችን ለተቋማት ባቀርብ “ኃይሌ በጣም
እናደንቅሃለን፤እናከብርሃለንም… ግን…”
የሚል መልስ ነው የሚበዛው፤አሁን ግን እንደ
አገር እንደ ፌዴሬሽን የትኛውን በር ብናንኳኳ
ይከፈታል፤ እንደ ፌዴሬሽንም ተገቢው
ክብር ተሰጥቶን ነው እንጂ የምንስተናገደው
“እናደንቅሃለን፤ እናከብርሃለን ግን ይቅርታ”
የሚል ምላሽ አይሰጡኝም፤ ለዚህም ነው እንደ
ፌዴሬሽን ተንቀሳቅሰን ብዙ ስራ የሰራነው።
በተለይ በዚህ በዶፒንግ ጉዳይ ላይ የሰራነው
ስራ ቀላል አይደለም፤ አገራችንን ከቅጣት
የታደግንበት ብዙ ስራ ነወ የሰራነው፤ ስለዚህ
ጥያቄው በዚህ መልኩ መልስ ቢያገኝ ደስ
ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ከአንተ ጋር ቃለ-ምልልስ
በማደርግበት ሰዓት የለንደን የአለም አትለቲክስ
ሻምፒዮና ሊጀመር ከስድስት የማይበልጡ
ቀናት በቀሩበት ሰአት ላይ ነውና እንደ
ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በውድድሩ ስኬታማ
ለመሆን እየተደረገ ያለውን ዝግጅት እንዴት
ትገልፀዋለህ?
ኃይሌ፡- በጠዋት አዲስ አበባ ስተድየም
የተገኘሁት አሁን በጥያቄህ ያነሳኸውን
ለመከታተል ነው፤ እንደምታየው አትሌቶቹ
በሁሉም ኤቨንቶች (ውድድሮች) ዝግጅት ላይ
ናቸው፡፡ እኔ ግን እንደማየያቸው …እ…ሙሉ
አልሆነልኝም… የሆነ የጎደለ ነገር ያለ ያህል
ይሰማኛል… ለዚያም ነው ያንን ለሟሟላት
እዚህ በጠዋት የመጣሁት…
ሀትሪክ፡-…ሙሉ አልሆነልኝም ስትል…?
ኃይሌ፡- …በቃ… አለ አይደለም…
ሙሉ አልሆነልኝም… ማለት ምን ማለት
ነው… ይሄ ሙሉ ሱፍ… ለብሰህ…ለብሰህ…
በመጨረሻ የሚቀር ከረባት ነገር አይነት
የለም… በቃ…እሷ ነገር ጎላለች፡፡ በቃ…
ዛሬም… እዚህ የምታየኝ …እሷን ለመፍጠር
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …እንደዚህ የተሰማህ… ከምን
መነሻነት ነው…? …ጎደለ… የምትለውስ
ምንድነው…?
ኃይሌ፡- …እኔ… እንጃ… በቃ…
ምን ልበልህ…ሁሉ ነገር ተሟልቶ ቅር
የሚልህ ነገር የለም? እንደዛ አይነት ስሜት
ነው። ልጆቹ ዛሬም እንደምታየው እየፈጉ
ነው፤ ለውድድሩም በቂ ዝግጅት እያደረጉ
ነው፤የትሬይኒንግ ችግርም አይደለችም፤
የጉልበት ነገርም እይደለችም፤… በቃ…
ይሄ ምንድነው…? …የቡድን… የአሸናፊነት
መንፈስ… (Winning Sprit)የምትባለው
ነገር ጎደል ብላብኛለች፤ እሷ ነገር ጎዶሎ
ሆና ትታየኛለች፡፡ በተፈረ ልጆቹ ህዝባቸውን
በውጤት ለማስደሰት ፈግተዋል፤ ጫካውንም
ስቃዩንም ተቋቁመው እየሰሩነው። በተለይ
አሁን ያለንበት የክረምት ወር ከባድ ነው። ዝናቡ
እንደ ዘንድሮ ሆኖ አያውቅም፤ ያም ቢሆን
ግን መልፋታቸውን አላቆሙም፤የሚሆነውን
አብረን እናያለን፡፡
ሀትሪክ፡- በለንደን የአለም አትለቲክስ
ሻምፒዮና ላይ አገራችንን ወክለው
የሚካፈሉትን አትሌቶች ስም ዝርዝር
ለማሳወቅ ብዙ እንደተጨነቃችሁና የተለያዩ
ውጥረቶች እንደነበሩ ነው መታዘብ የተቻለው፤
የዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው ብሎ መናገር
ይቻላል?
ኃይሌ፡- በነገራችን ላይ ይሄን አይነቱ
ነገር ዛሬ ብቻ የተከሰተ አይደም፤ ሁሌም
ይሄን መሰል ውድድር ሲኖር የሚፈጠር
ነው፤ በአትሌቲክስ በምርጫ ወቅት ይሄ
የተለመደ ባህሪ ነው። አትሌት በባህሪው
“ስለተሸነፍኩ ነው፤ ከእኔ የተሻለ ሰው
ስላለ ነው ያልተመረጥኩት” ብሎ አምኖ
አይቀበልም፤ ይሄ ለምን ሆነ ብለህ ግን
መቃወም አይቻልም፤ምክንያቱም በአትሌቲክስ
ሽንፈትን አምነህ ተቀብልክ ማለት እስከ
ወዲያኛው ትሸነፋለህ ማለት ነው፤ ለሽንፈት
ፊት መስጠት ተገቢ አይደለም፤ ሁሌም
መታገል ነው ያለብህ። እኔ በርቀቱ የተሻልኩ
ነበርኩ፤ የእናንተ ተፅዕኖ ነው እንጂ ብሎ
ቅሬታ ማቅረብ መብት ነው ለምን ሆነ ብለን
አንጠይቅም፡፡
ሀትሪክ፡- እንደ ፕሬዝዳንትነትህ አትሌ
ቶችን ለመምረጥ ያወጣችሁት መስፈርት
ትክክለኛውን ሰው ለማግኘት ረድቶናል፣ አሳ
ማኝ ነው መስፈርቱ ትላለህ? ምክንያቱም
መስፈርቱ ብዙ ጫጫታዎችንና ቅሬታዎችን
ሲያስነሳ ሰለሰማሁ ነው?
ኃይሌ፡- መስፈርት የሚባለው
በአትለቲክስ ማነው ከፊት ያለው የሚለው
ነው፤ እሱ መስፈርት እንዳለ ሆኖ ምን ታያለህ
መሰለህ ለውድድሩ የሚያበቃውን ሚኒማ
አምጥቷል ወይ? ያለው ሰአትስ ምን ያህል
ነው? የሰጠነውን ነገር በብቃት ተውጥቷል
ወይ? የሚሉና ሌሉች በርካታ መመዘኛዎችን
አይተህ ትመርጣለህ፡፡ ከዚህ ውጭ እከሌ
የሆነ አገር ሄዶ አሸንፏል እዛም በጥሩ ሰአት
ገብቷል ሚኒማ አምጥቷል ተብሉ ይመረጥና
በኋላ ውድድር ላይ ገብቶ ኋላ ከቀረ፣ ጭራ
ሆኖ ከጨረሰ ምንልታደርጉ ነው ይዛችሁት
የሄዳችሁት በሚል ወቀሳ ይቀርባል፤ ይሄን
ወቀሳ ለመከላከል የኢትዮጵያ ሻምፒዮና
ላይ መሳተፍ አለበት፣ ትሬይኒንጉን ሄደን
እናያለን፣ ወቅታዊ ብቃቱንና የጤንነቱን ሁኔታ
እንከታተላለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቴክኒካል
ግምገማ አድርገን ነው የምንመርጠው፡፡
ሀትሪክ፡- ኃይሌ አሁን አንተ ይሄን
ብትልም አንድ የጤንነቱ ሁኔታ በጥሩ ደረጃ
ለይ የማይገኝ አትሌት ህምሙን ደብቆ ወደ
ለንደን ሊሄድ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ሹክ
ብሎናል፤ በዚህ በኩል የምታደርጉት ጥንቃቄ
እስከምን ድረስ ነው?
ኃይሌ፡- ይሄ ነገር እናንተ ጋርም
ደርሷል? አሁን እኔም ዛሬ በጠዋት የመጣሁት
(ቅዳሜ ጠዋት ማለቱ ነው) ይሄንን አትሌት
ለመከተታተል ነው። አትሌቱ ታሟል ግን
ለለንደኑ ውድድር ተመርጧል ፤አትሌቱም
ህመሙን ደብቆ መሄድን መርጧል፡፡ አማራጭ
ስለሌለ በለው በሌላ ይሁን ብቻ መርጠውታል፡
፡ ይሄ በጣም የሚያሳዝን ነው፤ አንድ አትሌት
ከታመመ ለምንድነው “እኔ ስለታመምኩ
ከእኔ የተሻለ ጤንነት ያለው አትሌት ይሂድ”
የማይለው? ለምንድነው በአገር ገንዘብና በአገር
ውጤት ላይ የምንቀልደው? ታሞ ደብቆ ሲሄድ
እኮ ራሱንም አገርንም ነው የሚያዋርደው፤
ጤነኛ ነኝ ካለ ቢሄድ ምንአለበት ምቀኝትነት
ካልሆነ የሚባል ነገር አለ፡፡ የምናስቀደመው
አገርን ነው መሆን ያለበት። የአገር ገንዘብ
ባከነ ማለት ከሁላችንም ኪስ የሚወጣ ገንዘብ
ባከነ ማለት ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የዚህ አትሌት ማንነት
ታውቋል? ከታወቀ ሌሉች አማራጮችስ
የሉም?
ኃይሌ፡- …እስቲ አሁን… ተወኝ…
ሁኔታውን ለማየት ነው ዛሬም የመጣሁት…
እየተከታተልነው ነው… የሚሆነውን አብረን
እናያለን…፡፡
ሀትሪክ፡- የፌዴሬሽኑ መስፈርት
ከምርጫው ውጪ ካደረጋቸው አትሌቶች
አንዱ ውጤታማው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
ነው፤ የእሱ መቀነስ ብዙዎችን አላሳመነም።
ብቃቱ /ፐርፎርማንሱ/ ጥሩ አይደለም
በሚል የቀረበው ምክንያት ወቅታዊ ብቃቱ /
ፐርፎርማንሱ/ እያደገ ሊሄድ የሚችል ነው፤
አሁን ያለው ወቅታዊ አቋምም ከሌሎች
ያነሰ አያደርገውም ብለው አመለመመረጡን
የሚቃወሙና ከእሱ መቀነስ በስተጀርባ አንድ
የተደበቀ ምስጢር ሊኖር ይችላል ብለው ጥያቄ
የሚያነሱ አሉ ለእነዚህ ሞጋቾች መልሰህ
ምንድነው?
ኃይሌ፡- (እንደመሳቅ ብሎ) ከቀነኒሳ
አለመመረጥ ጋር በተያያዘ ምንም የተደበቀ
ነገር የለም፤ የእኛ ፍላጎት እንደውም ምን
እንደሆነ ልንገርህ ቀነኒሳ ለንደን ላይ ሲሮጥና
ሲያሸንፍ ማየት ነበር ግን አልሆነልንም፡፡
በጥያቄህ እንዳነሳኸው የእኛ ፍላጎት ባለው
ብቃት (ፐርፎርማንስ) እንዲሄድ ፈልገን
ነበር ብቻ ሳይሆን ጠይቀነዋልም፡፡ እሱ ግን
“በፍፁም አልችልም፤ በቃ እኔን ተውኝ” አለ፤
ተውኝ ማለቱ ምን ማለት ነው በቃ ያለኝ
አቅም አይደርስልኝም፤ ጥሩ አይደለሁም
ማለት ነው። እንደ ቀነኒሳ አይነቱን ትልቅ
አትሌትን በግድ መሄድ አለብህ ብለን
ወስደነው እዛ የማይሆን ሽንፈት ቢገጥመው
ሽንፈቱ በጣም ያማል።“አልችልም” አለ በቃ
አመነው ተቀብለንሃል አልነው፤ እውነታው
ይሄ ነው። ከዚህ ውጪ ቀነኒሳን መቀነስ
አይደለም በአንድ እግሬ ልሩጥ ቢለኝ ሂድ
ሩጥ ነው የምለው፡፡
ሀትሪክ፡- አንተስ በግልህ ቀነኒሳ ለንደን
ላይ ማራቶን ሲሮጥ አለማየትህ ምን ስሜት
ፈጠረብህ?
ኃይሌ፡- የቀነኒሳን አለመሄድ ስሰማ
በጣም ነው የደነገጥኩት፤ የእሱ አለመኖር
በሙሉ ቡድኑን ጎደሎ ያደርግብናል። ለምን
ያልክ እንደሆነ ልጁ ቀነኒሳ በቀለ ነው፤
የእሱ ከልዑካን ቡድኑ ውጪ መሆን እኛን
እንዳስደነገጠ ሁሉ ተፎካካሪዎቻችንን
ጮቤ ነው የሚያስረግጠው። እነደ ቀነኒሳ፣
አልማዝና ጥሩዬን የመሳሰሉ ውጤታማና
ልምድ ያላቸው አትሌቶችን በቡድንህ ውስጥ
ስትይዝ ብዙ ጥቅም አለው፤ እነዚህ ልጆች
ምልክት (ፊገርስ) ናቸው። ቀነኒሳ በቀለን
ይዘህ ስትሄድ በጣም ትልቅ ሆነህ ገዝፈህ
ትታያለህ፤ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት
አትሌቶች ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለስነ-ልቦና
የበላይነትም ይጠቅሙሃል፡፡
ሀትሪክ፡- በለንደን የአለም አትለቲክስ
ሻምፒዮና ስንት ሜዳሊያ እናስመዘግባለን
ስትባል ጥያቄውን አትወደውም፤ ከዚህ በፊት
ከነበረው ልምድ አንፃር ይሄንን ለመናገር
ለምን ድፍረት ያጣኸው ?
ኃይሌ፡- አሁን ይሄ ድፍረት ማጣት
ነው ብለህ ነው? አሁን እንግዲህ እኔ ሩጫውን
አልሮጠው፤ የሚሮጡት ልጆቹ ናቸው፤ እኔ
እዚህ ተቀምጬ እከሌ ይሄን ያህል ወርቅ፤
እከሌ ደግም ይሄን ያህል ብር ያመጣል
እያልኩ የምደለድለው እንዴት ነው? ከእኛ
እኩል ወርቅና ብር ለማምጣት የሚሮጡ
አሉ እኮ፤ከዚህ በፊት ይሄንን ያህል ወርቅና
ነሐስ እናመጣለን እየተባለ ሲታቀድ እቃወም
ነበር፤ በሩጫ እንደዚህ ተብሎ አይታቀድም
እያልኩ ስቃወም ነበር፤ አሁን ተነስቼ 8 ወርቅ
እናመጣለን አትጠራጠሩ ብል ከዚህ በፊት
አይታቀድም ብለህ ስትቃወም ነበር አሁን ግን
አንተ ራስ አቅድህ መጣህ ልትለኝ ነው /በጣም
እየሳቀ/ እኔ ግን ከውድድር በፊት ሜዳሊያ
ቁጭ ብሉ ከመቁጠርና ይሄን እናደርጋለን
ብሎ ከመፎከር በፊት መቅደም ያለበትን
ስራ መስራትን ነው የማስቀድመው፤ በጥሩ
ዲሲፒሊን ጥሩ ውድድር አድርገው በጥሩ
የቡድን አንድነት ውስጥ ሆነው እንዲወዳደሩ
ነው የምፈልገው፡፡
ሀትሪክ፡- ዓለም ለሜዳሊያ እያጨን ብቻ
ሳይሆን ቅድሚያ ግምት እየሰጠን ከሜዳሊያ
ይልቅ የቡደን አንድነትና ዲሲፒሊንን ነው
የማስቀድመው ማለትህን የታዘቡ፤ይሄ ለእኛ
ሳይሆን የሩጫ ካርታ ውስጥ ለሌሉ እንደ
ፖኪስታን ላሉ አገሮች የሚሰነዘር አስተያየትን
ኃይሌ እንዴት ይሰጣል? በማለት የሚቃወሙህ
አሉ እውነት እኛ ፖኪስታንን ነን?
ኃይሌ፡- (በጣም ሳቀ) ጥያቄውን
ወዴት ወዴት ነወ የምትወስደው? እኔ
ሌሎች ለወርቅ ለአሸናነፊነት ሲያጩን እኔ
ከእነሱ በተቃራኒ ተሰልፌ መስሎህ ከሆነ
ተሳስተሃል፤ ወርቁንም ብሩንም አፍሶ
ለመምጣት በመጀመሪያ ዲሲፕሊን ከዚያ
የቡድን የአንድነት መንፈስ ያስፈልጋል፡
፡ እነዚህ ለውጤታማነት ምሰሶዎች ናቸው፡
፡ እነዚህን ከያዝክ የምትፈልገውን ታገኛለህ
እነዚህን ካልያዝክ የምትፈልገውን ታጣለህ
ነው መልዕክቴ።
ሀትሪክ፡- እሺ ጥያቄዬን ለውጥ አድርጌ
ልምጣ እስቲ… ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት
ቤጂንግ ላይ 5 ወርቅ በአጠቃላይ ስምንት
ሜዳሊያዎች ነበሩን፤ ዘንድሮስ ከዚያ የተሻለ
የማግኘት ተስፋው አለን…? ብልህ እንዴት
ነው ምላሽ የምትሰጠኝ?
ኃይሌ፡- አሁንም በዚህ ጥያቄ
አንስማማም፤ የስፖርት አንዱ ትልቅ
ችግር ምንድነው ወደኋላ ሄዶ መተሳሰብ
ነው። ሁልጊዜም ቢሆን አገርን ወደኃላ
ሄደህ አታወዳድርም፤ ማወዳደር ያለብህ
ከተወዳዳሪዎቻችን ከተፎካካሪዎቻችን አንፃር
ነው። ሁሉም ነገር መወዳደርና መዳኘት ያለበት
ከጊዜው ከወቅቱ ጋር ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፈው
ሶስት ወርቅ አምጥተናል፤ ዘንድሮ አራት
ወርቅ አምጥተን ተፎካካሪዎቻችንን ስምንት
ወርቅ ቢያመጡ ካለፈው አንፃር የተሻልን ነን
ሊባልነው? በእርግጥ ካለፈው አንፃር የተሻልን
ሊመስለን ይችላል ምክንያቱም በአንድ ወርቅ
ከፍ ብለናል፤ ከተፎካካሪዎቻችን አንፃር ግን
በአራት ዝቅ ብለናል፤ ደረጃም የሚሰጠን
ካለፈው የተሻለ አምጥታችኋል በሚል
ሳይሆን ከተፎካካሪዎቻችን አንፃር ካገኘነው
ጋር ተነፃፅሮ ነው፤ መለኪያችን ወደኋላ ሄደን
ሳይሆን ከተወዳዳሪዎቻችን አንፃር ነው የሚል
አቋም ነው ያለኝ። አሁን የቅርቡን አንድ ነገር
ልንገር እኛ የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሺፕ አልጀሪያ
ላይ የወጣቶች ደግሞ ጎረቤታችን ኬኒያ ላይ
ሲካሄድ ውጤታቸውን አይተን “ዋው” ብለናል፡
፡ ከተወዳዳሪዎቻችን አንፃር ምንም አንልም
በተለይ ይሄ ውድድሩ ኬኒያ ላይ ስለተደረገ
ከእነሱ አንፃር መዝነነው እነዚህ ልጆች የዛሬ
ሁለት ዓመትና ለሚቀጥለው ኦሎምፒክ በጣም
ጥሩ ደረጃ ይደርሳሉ ብለን ገምግመናል፤ እኔ
የማይስማማኝን አንድ ነገር ልንገርህ…
ሀትሪክ፡- …ንገረኝ…?
ኃይሌ፡- …አንዳንዶች የሆነ ውጤት
ሲመጣ ይነሱና “በኢትዮጵያ አትሌቲክስ
ታሪክ ይሄ ውጤት መጥቶ አያውቅም”
ይሉኛል እንዴት ስላቸው “በዚህ ዓመት ይሄን
ነበር ያገኘነው፤ አሁን ደግም ይሄን” ይሉኛል፤
በዚህን ጊዜ እባካችሁ ወደኋላ ሄዳችሁ ሂሳብ
አትስሩ ያለፈው ጥሩ እርሾ ይሁናችሁ ንፅፅሩና
ፉክክሩ ግን ከተፎካካሪዎቻችን አንፃር ይቃኝ
እላቸዋለሁ፡፡ …እነሱ ምን አገኙ?… እኛስ…?
ብለን የጎደለውን እንሙላ፤ የሞላውን ይበልጥ
እናሳድገው ነው። እኔ የሂሳብ ስሌት መሰራት
ያለበት ከተፎካካሪዎቻችን አንፃር መሆን
አለበት ባይ ነኝ፤ ከዚህ ውጪ ወደኋላ ሄዶ
ሂሳብ መተሳሰብን አልመርጥም፡፡
ሀትሪክ፡- በለንደኑ የዓለም ሻምፒዮና
በውጤት በኩል ውስጥህ እርግጠኛ የሆነው
በየትኛው ርቀት ላይ ነው፤ ብዙዎች በሴቶች
10 ሺህ እና 5ሺህ የእርግጠኝነት ስሜት
ሲያንፀባርቁ ስለማይ ነው?
ኃይሌ፡– እንደ እኔ በውጤት
በምንታወቅባቸው ርቀቶች ጥሩ እንሆናለን
ብዬ ነው የምገምተው፤እንደተባለው በሴቶች
በ5 እና በ10ሺህ፤ በወንዶች በተመሳሳይ ርቀት
ተስፋው አለን፡፡ ሴቶች 5 ሺህ ላይ አራት
ተወዳዳሪዎች ናቸው ያሉን፤ በጣም ቆንጆ
ፉክክር ያደርጋሉ ብዬ ነው የምገምተው፡፡
ወንዶች 5 ሺህ ላይም ተመሳሳይ ስሜት ነው
ያለኝ፤ ማራቶኖች በተለይ ሴቶች ጥሩ ፍክክር
ያደርጋሉ፤ በዚህም አራት አትሌቶች ናቸው
ያሉን በአጠቃላይ አራት አትሌት ባሰለፍንበት
ቦታ የተሻለ ተፎካካሪ እንደምንሆን ነው
የምገምተው፡፡
ሀትሪክ፡- ዘንድሮስ ዋነኛ ተቀናቃኛችን
ኬኒያ ናት ወይስ ሌሎች አገሮች አሉ?
ኃይሌ፡- የኬኒያ ምንም ጥያቄ የለውም፤
ዋነኛ ተቀናቃኛችን ብትሆንም እንደ ሞፋራህ
አይነት ብቅ እንደሚሉንም መዘንጋት
የለብንም፡፡ እነ ሞ ፋራህ አንድ ሁለቷን
ነጥቀውን ለመሄድ ነው የሚመጡብን፤
በአብዛኛው ቡፊያችን ላይ ያለው ሌላ
ነው፤ እንግዲህ እዛው ቴብል ላይ ያላቸው
ተወስደችብን ማልቀስ የለብንም ሲሆን እሷንም
አለማስወሰድ ነው ያለብን፡፡
ሀትሪክ፡- ያልተጠበቀ (ሰርፕራይዝ)
የሚያደርገን ብለህ የምትጠብቀውስ አለ?
ኃይሌ፡- እ… (እንደ ማሰብ እያለ) 3
ሺህ የሴቶችና የወንዶች መሰናክል አካባቢ
አንድ የሆነ አዲስ ነገር የማይ ይመስለኛል፤
ከዚህ በፊት ያልተለመደ ነገር። በ1500 ሜትር
ወንዶችም እንደዛው ተመሳሳይ ስሜት ነው
ያለኝ፤ ከበፊቱ አንፃር ሲታይ በዚህ ኢቨንት
ሜዳሊያ ብዙም አናውቅም፡፡
ሀትሪክ፡- እንግሊዝያዊው ሞ ፋራህ
ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮና
ሜዳሊያዎችን ነጥቆናል፤ ለሶስተኛ ጊዜ በአገሩ
እንዳይነጥቀን “አሁንስ ይበቃሃል” ብለው
የሚያቆሙት አትሌቶች አሉን?
ኃይሌ፡- እንግዲህ አንድ እውነት
ልንገርህ በ 5 ሺህ እና በ10 ሺህ የእኛን
ልጆች አይቻቸዋለሁ፤ በጣም ይበልጡታል፡፡
ምንድነው መሰለህ ብልጥ አለመሆናችን ብቻ
ነው፤ ብልጠት ካለ ይበልጡታል፤ ችግራችን
ካልኩልሽን ላይ ነው፤ፊዚካልንና ሜንታልን
እኩል ማሰራት ከተቻለ አትጠራጠር የእኛ
ልጆች አሳምረው ያሸንፉታል፡፡ የእኛ ልጆች
በ5 ሺ እና በ10 ሺህ ሲሰሩ አይቻቸዋለሁ፤52
እና 53 ይሮጣሉ፤እሱ ደግሞ 55 እና 54
ነው፤ በተለይ ደግሞ ከፈጠነበት ከባድ ነው
የሚሆነው። በአጭሩ ካልኩሌት ማድረግ
ነው፤ ብልጥ መሆን ነው ሌላው ነገር ሁሉ
አላቸው። ይሄንን እንዲተገብሩ ደጋግምመን
ተመካክረናል፡፡
ሀትሪክ፡- አንተ ባቆምክበት ሰዓት
የኢትዮጵያዊያንን የበላይነት መንጠቁ
አያበሳጭህም? ከቁጭት ባለፈስ ምነው በኖርኩ
ያልክበት ጊዜስ የለም?
ኃይሌ፡- ወደ አትሌቲክሱ ያመጣኝ
ይሄው ቁጭት አይደለም እንዴ? …
ከውጭ ሆነህ ስታይ ያምሃል። ትናደዳለህ፤
ትቆጫለህ። እኛ ጋ ይሄ ሁሉ ሰው እያለ
እሱን የሚያሸንፉ ጠ ፋ? ብለህ በቁጭት
መብሰልሰልህ አይቀርም፡፡
ሀትሪክ፡- ሞ ፋራህ እያሸነፈ ለቁጭት
ቢዳረገንም የአትሌቲክሱ ዓለም ቁንጮ መ
ሆኑን መካድ አይቻልምና የለንደኑ ሻምፒዮና
የእሱና የአለማችን ፈጣኑ ሰው ዩዜይን ቦልት
መሰናበቻ ነው፤ይህ ሁኔታ ምን ስሜት
ፈጠረብህ …? የዓለም አትሌቲክስ የውድደር
አድማቂዎቹ ያጣ አይመስልህም?
ኃይሌ፡- ይሄ ሂደት ነው…፤ ሞ
ፋራህና ዩዜይን ቦልት ይወጣሉ ሌሉች
አዳዲስ ኮከቦች ደግም ተፈጥረው ብቅ ይላሉ፤
በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ አዳዲስ ኮኮቦችን
ፈጥሮ እንደሚያሳየን የጊዜ ሂደት አስተምሮን
አልፏል፤ ቅብብሎሽ ስለሆነ ሌላ ኮኮብ የእነሱን
ዱካ ተከትሎ የአለም ኮከብ መሆኑ ይቀጥላል፡፡
ሀትሪክ፡- ባልተለመደ ርቀት በማሸነፍ
አገራችንን በአጭር ርቀት ዝርዝር ውስጥ
የከተተው መሀመድ አማን በጉዳት ረጅም ጊዜ
ከውድድር ርቆ ቆይቶ በለንደን ሀገርን ወክሎ
መቅረቡን እንዴት ታየዋለህ…? …ብዙዎች
በዚህ በኩል የጠነከረ ስጋት ስላላቸው ነው…?
ኃይሌ፡- ወደድንም ጠላንም በ800
ሜትር በአሁን ሰዓተ ሚኒማ ያመጣው እሱ
ነው፤ ማሙሽ በዚህ ርቀት ይገባል ብለን
ጠብቀን ነበር አወዳዳሪው አካል (IAAF)
የማሙሽ አይቻልም የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ
ስለሰጠን በርቀቱ አገራችራን የሚወክለው
መሃመድ አማን ነው። የብዙዎች የስጋት
ምንጭ ይገባኛል፤ መሃመድ ላለፍት ሁለት
ዓመታት ያህል ውጤቱም ጤንነቱም ጥሩ
እንዳልነበር መካድ አያስፈልግም፡፡ ሌላ ሚኒማ
ያሟላ ሰው ቢኖር ልታማርጥ ትችላለህ፤
አሁን ግን የለም፤ ያለው እሱ ነው። ረጅም
ጊዜ ከውጤትና በጉዳት ርቆ በመቆየቱ
ምንም አታመጣም ብሎ መከላከሉ ትርጉም
አያመጣም፤ ውድድር ላይ ገብቶ የሚሆነውን
ማየት ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ለንደን ለመጓዝ ጥቂት
ቀናት በቀራችሁ ወቅት የቡድኑ ካምፕ
በዲሲፕሊን ችግር የታመሰበት ሁኔታ
ተፈጥሯል፡፡ አትሌት ጫላ አሰልጣኙን
ሻምበል ዮሃንስን የመታበት አጋጣሚ
መፈጠሩና አናንተም የቅጣት ውሳኔ በፍጥነት
ማስተላለፋችሁ የቡድኑን የአንድነት መንፈስ
አያደፈርሰውም?
ኃይሌ፡- እንደዚህ አይነት ነገር ማንም
ይከሰታል ብሎ አላሰበውም፤ ተከስቷል።
በአትሌቲክሱም ያልተለመደ ነው፤ ትንሽ ጉዳዩ
አትሌት ወደ አሰልጣኝ ሆነ እንጂ አሰልጣኝ
አትሌቱን ቢመታው ኖሮ ችግር አልነበረውም፡
፡ ከዚህ ውጪ ጉዳዩ እኛ በቅርበት ያለነውን
ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አሳዝኗል፡፡ በተፈጠረው
ነገር የቡድናችንን ሰላም እንዳያደፈርስ
የማረጋጋት ስራ ሰርተናል፡፡ ዲሲፒሊን
ዲሲፒሊን የምንለው ይሄን አይነቱን መስመር
የሳተ ነገር ለመከላከልና ውጤታማ ለመሆን
ነው። ፌዴሬሽኑ ከለዘብተኝነት ወጥቶ
ዲክታተር እንዲሆንም ያስገድደዋል፡፡ እንደዚህ
አይነት አጋጣሚ ሲፈጠር አረንጓዴውን
መፅሐፍ ገለፅ የምታደርግበትና አንቀፅ
ጠቅሰህ ውሳኔ ለማስተላለፍ ትገደዳለህ። በዚያ
መሰረት አትሌቱ ላይ በስራ አስፈፃሚ ደረጃ
ተመጣጣኝ ያልነውን ውሳኔ አስተላልፈናል።
በፊት ከውሳኔ ይልቅ በመማር፣ በመመካከር
እንፈታለን ማለታችን ትንሽ የጎዳን
ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ አንቀጥልም፤
በእግር ኳስ ቀይና ቢጫ ካርድ ባይኖር ይሄ
ሜዳ የጦርነት አውድማ አይሆንም ነበር?
እኛ መስመር እያስያዝን ካልሄድን የጦርነት
አውድማ ሆኖ ብዙ ሰዎችን ከሚያጠፋ በተቻለ
መጠን እያስተማርን አረንጓዴውን መፅሀፍም
ገለፅ እያደረግን ህጉን ተግባራዊ እያደረግን
እንሄዳለን፡፡
ሀትሪክ፡- ሃይሌ ለንደን የሚገኘው
በፕሬዝዳንትነቱ…፣… በቢቢሲ ተንታኝነቱ…፤
ወይስ በክብር እንግድነት…?
ኃይሌ፡- ለንደን በመክፈቻው ላይ
አልገኝም፤ በግል ምክንያቴ አልገኝም፡፡ ይሄንን
ስልህ ወደ ለንደን አልሄድ ማለቴ አይደለም
የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ግን
እኔን እዛው ታገኘኛለህ… ከዚያ በኋላ እስከ
ወዲያኛው አለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …በመጨረሻ ቀረ የምትለው
ነገር ካለ ክቡር ፕሬዝዳንት አመስግኜህ
ልለይህ…?
ኃይሌ፡- …ምንም የቀረ ነገር የለም
የምንለውን ሁሉ ብለናል… ስፖርቱን
በተመለከተ ስፖርቱ ሁሉንም ወደ ሜዳ
ቢያመጣ ይሻላል ኳስ የሚሉ ኳሱን፤ ሩጫውን
የሚሉም ሩጫውን ብለው ቢመጡ ከዚህ
በስተጀርባ ያለውን ባናየው፤ ህብረተሰቡም
ባያየው በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ከዚህ ውጪ
ሲሆን የስፖርቱ መንደር ሰላም ይደፈርሳል፡
፡ ስፖርት በመርህ ደረጃ እንደሚታወቀው
ከፖለቲካ፣ ከዘርና ከሃይማኖት የፀዳ
በመሆኑ ለቫዮለንስ/ለረብሻ/ ከሚዳርጉ ነገሮች
ልንጠብቀው ይገባል፤ ከግል አጀንዳችን ይልቅ
የአገር አጀንዳን እናስቀድም ነው የምለው፡፡
“በፕሬዝዳንትነት የተቀመጥኩበት ወንበር ከምቾት ይልቅ ይፋጃል” ፕሬዝዳንት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዙሪያ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት (Exclusive!)
Managing Editor at Hatricksport Website