የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ29ኛው ሳምንት ሶስተኛ ቀን ጨዋታ መከላከያ እና አዳማ ከተማ ያለምንም ጎል ነጥብ ተጋርተዋል፡፡ 10:30 እዲጫወቱ መርሃ ግብር ተይዞላቸው የነበረው የደደቢት እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ለረቡዕ ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በ10:30 እዲጫወቱ ቀን ተቆርጦላቸዋል ፡፡
በ29ኛ ሳምንት በተደረጉ 7 ጨዋታዎች ፤ ላለመውረድ እሚደረጉ አጎጊ ትእይንቶች ቀጥለዋል፡
በ ሊጉ ትናንት አምስት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።በመርሃ ግብሮች የመውረድ ስጋት የተደቀነባቸው ቡድኖች አሸናፊ መሆን ችለዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በከፍተኛ የደጋፊዎች ተቃውሞ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን በቢኒያም አሰፋ በቢንያም አሰፋ ሁለት ጎሎች በ በተመሳሳይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
- ማሰታውቂያ -
ክልል ላይ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ ያለምንም ጎል ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።
አርባ ምንጭ ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ ደግሞ በሜዳው በፈቱዲን ጀማል ግብ የ1 ለ 0 ሽንፈትን አስተናግዷል።
በአዲስ አበባ ቃሊቲ መድን ሜዳ ላይ ፖሊስ በሰዓቱ ባለመገኘቱ መጀመር ከነበረበት 40ደቀቃዎችን ዘግይቶ የተጀመረው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዳዊት እስጢፋኖስ እና አዲስ ነጋሽ(ፍ.ቅ.ም) በተቆጠሩ ሁለት ጎሎች ወልዲያ ከተማን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
ጅማ ላይ የተደረገው የጅማ አባ ቡና እና የሃዋሳ ከተማ ጨዋታበሃይደር ሸረፋ እና ሱራፈል አወል ሁለት ጎሎች በጅማ አባቡና 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎም ላለመውረድ የሚጫወቱ ቡድኖች ትንቅንቅ 30ኛ ሳምንትን ተጠባቂ አድርጎታል ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ31፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ 32 ነጥቦችን ይዘው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታቸውን ይጠብቃሉ።
ደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 29 | 28 | 59 |
2 | ደደቢት | 28 | 15 | 48 |
3 | ሲዳማ ቡና | 28 | 9 | 48 |
4 | አዳማ ከተማ | 29 | 8 | 48 |
5 | ኢትዮጵያ ቡና | 29 | 11 | 47 |
6 | ፋሲል ከተማ | 29 | 2 | 43 |
7 | መከላከያ | 29 | -11 | 36 |
8 | ሀዋሳ ከተማ | 29 | -2 | 34 |
9 | ወልዲያ ከተማ | 29 | -3 | 34 |
10 | አርባምንጭ ከተማ | 29 | -5 | 33 |
11 | ወላይታ ድቻ | 29 | -10 | 33 |
12 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 29 | -1 | 32 |
13 | ጅማ አባቡና | 29 | -3 | 32 |
14 | ድሬዳዋ ከተማ | 29 | -9 | 32 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
29 | -10 | 31 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 29 | -21 | 20 |
በ30ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ዲቻ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልዲያ እና ሃዋሳ ከተማም በመጨረሻው ሳምንት ተሸንፈው ከታች ካሉ ቡድኖች አንዳቸው ማሸነፍ ከቻሉ ምናልባት አንደኛውን የወራጅ ኮታ የሚሞሉበት አጋጣሚ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።