ቢንያም በላይ ለክለቡ ሲይሪያንስካ የዓመቱ ሁለተኛ ግቡን አስቆጠረ
በስዊድን ሁለተኛ ዲቪዝዮን 17ኛ ሳምንት በሜዳው ኦስተርስን የገጠመው ሲይሪያንስካ በቢንያም በላይ እማካኝነት በ49ኛው ደቂቃ በተገኘች ግብ በሜዳው ከመሸነፍ ተርፏል።
16 ክለቦችን በሚያሳትፈው የስዊድን ሁለተኛ ዲቪዝዮን እየተሳተፈ ሚገኘው ስይሪያንስካ ትላንት ባገኘው እንድ ነጥብ ታግዞ ደረጃውን ወደ 12 ከፍ ማድረግ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ቢንያም በላይ በስዊድኑ ክለብ ላይ ከተለመደው ቦታው በተለየ በመሃል ሜዳ እማካኝነት በቀዋሚነት እየተጫወተ ይገኛል።