ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በስዊድን ሁለተኛ ዲቪዝዮን ለሲሪያንስካ ተጫውቶ ያሳለፈው ቢንያም በላይ ሌላኛውን የስዊድን ክለብ ኡምአ ኤፍሲን(Umea Fc) በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከስዊድን 3 ዲቪዝዮን ወደ 2 ዲቪዝዮን(ሱፐር ታታን) ያደጉት ኡምአ ኤፍሲን የ2020 የውድድር ዓመትን ከሁለት ወር በኃላ በሜዳቸው ዳልኩርድን በመግጠም ይጀምራሉ።
- ማሰታውቂያ -
ባሳለፍነው ዓመት ከስሪያንስካ ጋር በግሉ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ስከንደርቡ(አልባንያ) እና ስሪያንስካ(ስዊድን) ተጨዋች ቢንያም በላይ ሊጠናቀቅ የቀናቶች እድሜ በቀረው የጥር ወር የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በስዊድን ሁለተኛ ዲቪዝዮን ለሚጫወተው ኡምአ ሊቀላቀል ችሏል።