በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሚሆነው አዲስ አዳጊው ባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል። በኢትዮጵያ ቡና ለ2 አመታት የተጫወተው እና በ2010 ዓ.ም ዉሉ የተጠናቀቀውን ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ ሀሪስተን ሄሱ ለክለቡ ፈርሟል። ሀሪስተን ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ተያይዞ የነበረ ቢሆንም ለ1 አመት የሚያቆየውን ውል ከባህርዳር ከተማ ጋር ተፈራርሟል። አዲስ አዳጊው ባህርዳር ከተማ (የጣናው ሞገድ) ሀሪስተን ያስፈረመው 7ኛ ተጫዋቹ ሲሆን እስከ ዝውውሩ መጨረሻ ድረስ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።