ባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው /ማንጎን/ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ፡፡
በአሰልጣኝነት ከብዙ ክለቦች መስራት የቻለው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ከሰለጠናቸው ክለቦች ውስጥ ሱልልታ ከተማ፤ኢትዮጵያ ቡና ፤ ሰበታ እና በ2009 ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያሳለፈው እና በመጨረሻው ሰዓት በመቐለ ከተማ ተሸንፎ የኘሪሜየር ሊጉን ተሳትፎ ማግኘት ሳይችል ቀርቷል ፡፡
ባህርዳር ከተማ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በዘንድሮ የውድድር ዘመን በመጀመሪያው ዙር መልካም እሚባል እንቅስቃሴን አድርጎ በሁለተኛው ዙር ተዳክሞ ወድድሩ ፈፅሟል፡፡