ባለቀለሟ፣ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ልታስኮመኩሞት ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፤ ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ ይዛሎት ከምትቀርበው ዘገባ ውስጥ ከሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ የቅ/ጊዮርጊሱ ተከላካይ አብዱልከሪም መሐመድ ክለባቸው ሰሞኑን በአርባምንጭ ከተማ የተሸነፉበትን ጨዋታ አስመልክቶ ‘‘በሰፊ ግብ መሸነፋችን ያሟል፤ ለእዚህም ደጋፊዎቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለትና ቅ/ጊዮርጊስም የዘንድሮ የሊጉ ሻምፒዮና እንደሚሆን አስተያየቱን የሰጠበት ምላሽ ያለ ሲሆን ከእሱ ውጪም ሰሞኑን በመከላከያና በወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ መካከል በተደረገ ጨዋታ ላይ የመከላከያው ፍፁም ገ/ማሪያም ቡድኑን 2-1 የሚያደርገውን ትክክለኛ ግብ ሲያስቆጥር የወልዋሎው የቡድን መሪ ማሩ ግቧ ትክክለኛ አይደለችም በሚል ስሜት በአልቢትር እያሱ ፈንቴ ላይ የቦክስ ጥቃትን በመፈፀሙ ምክንያት የኢትዮጵያ አልቢትሮች በሁኔታው አዝነው ወደፊት በሚኖሩት ጨዋታዎች ላይ ከለላና ጥበቃ ካልተደረገልን የፕሪምየር ሊጉን ውድድር እስከ ግንቦት 20 ቀን ድረስ አናጫውትም በሚል ከውሳኔ ላይ በማህበራቸው አማካኝነት በመደረሱ ሊጉ መቋረጡ የሚታወስ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ከክለቦች ጋር ባደረገው የመፍትሄ ውይይት ላይ በተሰጡ ምላሾች በአንድአንዶቹ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ኢንተርናሽናል ረዳት አልቢትር ትግል ግዛው ማህበሩን በመወከል አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ቡናው ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ዳኞች ሊጉን አናጫውትም የሚሉ ከሆነ ዳኞችን ከጎረቤት እናስመጣለን ባሉት ምላሽ ላይ ትግል የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል፡፡ ‘‘መቶ አለቃ ፈቃደ ዳኞችን ከጎረቤት እናስመጣለን በሚል የተናገሩት የሀገራችን ዳኞችን ዝቅ ያደረገ፤ ለመንገደኛ ሰው እንኳን የማይመጥን” በማለት ምላሹን ለሀትሪክ ስፖርት የሰጠ ሲሆን፤ ነገ በስፋት ያነቡታል፤ ከእዛ ውጪም በሌሎች ሀገራዊ መረጃዎችም ነገ ሀትሪክን እንድታነቡ ተጋብዘዋል፤ ሀትሪክ ስፖርት የቀድሞ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዷም ነገ ይዛሎት የምትቀርበው የቀድሞ የኢትዮጵያ ወጣትና የዋናው ብሔራዊ ቡድን የቡናና የሐዋሳ ከተማ እንደዚሁም በተለያዩ ክለቦች ውስጥ በግብ ጠባቂነት ተጫውቶ ያሳለፈውን ሳዳት ጀማልን ሲሆን ከእሱ ጋር ሰፊ ቆይታ አድርገናል፤ ሳዳትም ከተናገረው ውስጥ ‘‘ቅ/ጊዮርጊስም ሌላ ክለብ ውስጥም ለመግባት ብዬ የለበስኩትን ማልያዬን አልሸጥኩም፤ ክብር የሰጠኝን የቡና ደጋፊንም በዚህ መልኩ የማሳዝን ሰው አይደለሁምም” በሚል ምላሹን ሰጥቷል፤ ከእዛ ውጪም እሱ ስለነበረበት የኢትዮጵያ ቡና የካሳዬ አራጌ ቡድን ስብስብም በሚመለከትም ‘‘በቡና ክለብ የምስረታ ታሪክ ያ ቡድን ዳግም ተፈጥሯል ብዬም አላስብምም” ብሏል፤ ሳዳት በሌሎች ሰፊ ታሪኮቹ ዙሪያ የሰጠውን ምላሽ ነገ ከጋዜጣው የምታገኙ ይሆናል፤ ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ስለ አርሰን ቬንገር ስንብት፣ ስለማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣይ ፈተና፤ ስለ ኤልክላሲኮ እና በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ለፍፃሜ ስለቀረቡት ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድን በተመለከተ በንፅፅር ደረጃ የቀረበና ሌሎችም የሚወዷቸው መረጃዎች ቀርቦሎታል፤ ሀትሪክ ነገ እንዳታመልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት የእኛ ብቻ ሳትሆን የእርሶም ናትና አንብቧት፤
ባለቀለሟ፣ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ስፖርት ዘገባዎችን ልታስኮመኩሞት ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች
Managing Editor at Hatricksport Website