ሀትሪክ በነገው እትሟ
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣን በአነጋጋሪ ዘገባዎቿ ነገ ይጠብቋት
ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውል የሚከተሉትን ዘገባዎች ይዛሎት ትቀርባለች፤ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል እና የአርቢትር ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በተለያዩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሃቅ በላይ ጋር ቆይታ አድርጎ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል፡፡
ከእነዛም ምላሾቹ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡፡
““በዳኝነት ላይ ፍትሀዊ አሰራር እንዳይኖር በማድረግ ክለቦችን ለመጉዳት ኃይማኖቴም፣ አስተዳደጌም፣ ስብዕናዬም አይፈቅድም” ያለው የሚጠቀስ ሲሆን በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በሌላ ዘገባዋም የፕሪምየር ሊጉን ውድድር አስመልክቶ እና በኳስ ህይወቱ ዙሪያ የወልዋሎ አዲግራቱን ተጨዋች እንየው ካሳሁንን በተለያዩ ጥያቄዎች አናግረነው ምላሹን ሰጥቶናል፡፡ ወልዋሎ አዲግራትና መቐለ 70 እንደርታ ባደረጉትና 1-1 በተለያዩበት ጨዋታ ዙሪያም ጥያቄ አቅርበንለት በምላሹ
“ወልዋሎ አዲግራት ለመቐለ 70 እንደርታ ይለቃል
ያሉትን ዝም ያስባልንበት ጨዋታ ነው በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎችም የአውሮፓ ሊግ የውስጥ ውድድሮችን እና የተጨዋቾችን ወቅታዊ ብቃት በማስመልከትም የሚወዱትን ዘገባ አቅርቦሎታለች፤ ሀትሪክ የእናንተው ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡