-
- ሌሎች ክልሎችም የትግራይን መንገድ እንዲከተሉ ተጠየቀ
- የትግራይ ክልል ሴቶች ቢሮ እና የሴቶች ማህበር
-
- የአቶ ተኽለወይኒ አሰፋን ንግግር አወገዘበ
ይስሀቅ በላይ
አለማችን በተለያዩ ጊዜያት አዕም
ሮአቸውና አንደበታቸው ሳይሰማሙ
ቀርተው በሚናገሯቸው ያልታረሙ
ቃላቶች ብዙዎችን አንገት ያስደፉ
የስፖርት ሰዎችን በተለያየ ጊዜ አብ
ቅላ ታዝበናል፡፡ እ.አ.አ 1999 ዓ.ም
የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ
የነበሩት ግሌን ሆድል አካል ጉዳተኞችን
አስመልክቶ ባልታረመ አንደበታቸው
የሰጡት አስተያየት ከእንግሊዝ የካቢኔ
ሚኒስትሮች፣ ከአካል ጉዳተኞች
ግሩፕ፣ ከፖለቲከኞችና ከህዝቡ የጠነከረ
ተቃውሞ ገጥሟቸው ከብሄራዊ ቡደን
ኃላፊነታቸው በውርደት ተነስተዋል፡
፡ በቅንነትና ካለማገናዘብ በመነጨ
“በሴቶች ሠዓት አልገባም ብዬ ነው”
በሚል በሰጠው አስተያየት አትሌት ቱርቦ
ቱሞም ምህረት ያደረገለት ሰው አላገኘም፡
፡ ይልቁንም የሴቶች ጉዳይን ጨምሮ
ከየአቅጣጫው መሸከም ከሚችለው በላይ
በርካታ ጫናዎችና ተቃውሞ እንደዝናብ
ወርዶበታል፡፡
አሁን ደግሞ በሳምንቱ መጨረሻ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል
ፕሬዘዳንት በመሆን ብቅ ያሉት አቶ
ተኽለወይኒ አሰፋ የትግራይ ሴቶችን
ብቻ ሳይሆን እናትና እህት ያለውን
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያሸማቀቀና አንገት
ያስደፋ አስተያየት ያውም የአገሪቱ እግር
ኳስ ወሳኝ አካል በሆነው ጠቅላላ ጉባኤና
በተለያዩ ሚዲያዎች ፊት መስጠታቸው
የአገሪቱን ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆን የባህር
ማዶ ሚዲያዎችንና የማህበረሰብ ትስስር
ገጾችን ጭምር አጨናንቀው ሰንብተዋል፡፡
በአብዛኛውን ጊዜ የስራ ልምድ
ሲጠየቁ “ነባር ታጋይ” የሚለውን ቃል
ለማስፈራሪያነት በሚመስል መልኩ
ደጋግመው ሲናገሩ የሚደመጡት አቶ
ተኽለወይኒ ባለፉት አራት ዓመታት
በፌዴሬሽኑ ውሰጥ በነበራቸው ቆይታ
በተለይ ባሳለፍነው ሳምንት በተጠናቀቀው
ጠቅላላ ጉባኤ ላይ “ስፖርቱ ለእሳቸው፤
እሳቸውም ለስፖርቱ” እንዳልተፈጠሩ
በሚሰጧቸው አስተያየት ራሳቸውን
አጋልጠው ሰጥተዋል፡፡
አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ ባለፈው
አርብ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል
በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፈፅሞ
ጨዋነትን የተላበሱና በስነ-ምግባር
የታነፁትን እንዲሁም የኢትዮጵያዊነት
መገለጫ የሆኑትን የትግራ ክልል
ሴቶችን አስመልክተው ባልታረመ
አንደበታቸው የሰጡትን አስተያየት
አስመልክቶ የትግራይ ክልል ለአቶ
ተክኽወይኒ የሰጣቸውን ውክልና
በማንሳት የብዙዎችን ቁጭት ያበሰ
ውሳኔን በፍጥነት አስተላልፏል፡፡
አቶ ተኽለወይኒ በእለቱ የሰጡት
አስተያየት ያሳዘነውና ያዋረደው
የትግራይ ክልል ሴቶችን ብቻ ሳይሆን
የጉባኤውን አባላት ጭምር ነው በማለት
ቅሬታቸውን ቁጣ በተቀላቀለበለት ስሜት
የሚሰጡ ወገኖች የጠቅላላ ጉባኤውን
ክብር ዝቅ ባደረገ መልኩ ይሄን
አስተያየት ሲሰጡ ለመቃወም የሞከረ
አባል አለመታየቱ ሁኔታውን አስገራሚ
እንዳደረገው ነው እየተነገረ ያለው፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ለተፈጠሩት ውዝግቦች፣ አሁን እየታየ
ላለው የቡድንተኝነትና የግለሰብ አጀንዳን
በመሪነት የማራመድ ሃላፊነትን
ወስደው የሚንቀሳቀሱ የሚመስሉት
አቶ ተኽለወይኒ በተለይ በአሁኑ ጠቅላላ
ጉባኤ ላይ ለታየው ገመድ ጉተታና
ለእግር ኳሱ መንደር መታመስ ተዋናይ
ሆነው ታይተዋል በሚል በብዙዎች
እየተወቀሱ ይገኛሉ፡፡ ከዚሁ መነሻነት
የትግራይ ክልል አቶ ተኽለወይኒ
የገጠማቸውን የአፍ ወለምታ ተከትሎ
ውክልናቸውን በማንሳቱና ከቀጣዩ የስራ
አስፈፃሚ ምርጫ ውጪ እንዲሆኑ
ማድረጉ ለእግር ኳሱ መንደር ትልቅ
እፎይታን የፈጠረ ሲሆን በትግራይ
ሴቶች ላይ በሰነዘሩት አስተያየት ውስጡ
የተጎዳ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ካለ
አቶ ተኽለወይኒ በዚህ አይነት ስብዕና
የኦሎምፒክ ኮሚቴን የመምራት ሞራል
የለህም” በሚል አይነት ስሜት ከምክትል
ፕሬዘዳንትነት በማንሳት እርምጃ ወስዶ
ለህዝቡ ማሳየት ይጠበቅበታል በማለት
በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
የሀትሪክ ታማኝ ምንጮች ከዚህ ዜና ጋር
በተያያዘ እንደሚገልፁት አቶ ተኽለወይኒ
በገጠማቸው የአፍ ወለምታ ያሳዘኑት
በዋናነት የትግራ ክልል ሴቶችንና
ሌሎች እናትና እህቶችን በይፋ ይቅርታ
መጠየቅ ሲገባቸው ስህተት እንዳልሰሩና
በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ውሳኔውን ካሳለፉት
ወገኖች ጋር ለመነጋገር ማሰባቸውን ሲገልፁ
መደመጡ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኖ
ተገኝቷል፡፡ “ምነው በእንቁላሉ በቀጣሽኝ
እንደተባለው አቶ ተኽለወይኒ አሰፋ በኤፍ
ኤም 107.8 የአገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር
ክቡር አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝን
ለአንድ የአገር መሪ ቀርቶ ለሌላ ሰውም
ሊነገር በማይገባ መልኩ ያውም በሚዲያ
እንደዚያ ከፍ ዝቅ አድርግው ሲናገሩ
ለምን ብሎ የሚጠይቃቸው ሰው ባለመኖሩ
ለተጨማሪ የአፍ ወለምታ ዳርጓቸው
ብዙዎችን እንዳሳዘኑ የሚናገሩት አስተያየት
ሰጪዎች የእሳቸው በዚህ መልኩ ከእግር
ኳሱ መንደር ዞር ማለት ትልቅ እፎይታን
ብቻ ሳይሆን እሳቸውን መሳሪያ አድርገው
የሚንቀሳቀሱትን ወገኖች የቡድን ስራም
የሚያበላሽ ዋጋ የሚሰጠው ውሳኔ ነው ካሉ
በኋላ ሌሎች ክልሎችም ድሬደዋም ደቡብም
ላለፉት አራት አመታት የእግር ኳሱን
መንደር ሲያምሱት የነበሩ እጩ አመራሮች
ላይ ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ለእግር
ኳሱ ያላቸውን ተቆርቋሪነት በተግባር
ማሳየት ይጠበቅበቸዋል፡፡ ይህ በእንዳህ
እንዳለ ያልተረጋገጡ የዜና ምንጮች
እንደጠቁመት ድሬደዋ አስተዳደርም ለአቶ
አበበ ገላጋይ በሰጠው ውክልና ዙሪያ
ዳግም እያሰበበት ሲሆን የተረጋገጠ መረጃ
ባይገኝም የአቶ ተኽለወይኒ እጣ ፈንታ
ሊገጥማቸው እንደሚችልና ዛሬ ወይም ነገ
በዚህ ዙርያ ክልሉ ውሳኔ ያስተላልፋል
ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው እየተነገረ ያለው
፡፡
በመጨረሻም ማምሻውን ወደ ህትመት
ልንገባ ስንል ባገኘነው ዜና የትግራይ ክልል
ሴቶች ቢሮ እና የሴቶች ማህበር በጋራ
ባወጡት መግለጫ የአቶ ተኽለወይኒ አሰፋን
ያልታረመና አሳፋሪ ንግግር ትናንት በይፋ
አውግዘዋል፤ የትግራይ ክልል ሴቶች ቢሮ
እና የሴቶች ማህበር ትናንት በጋራ በሰጡት
ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “አቶ ተኽለወይኒ
አሰፋ የትግራይ ክልል ሴቶችን አስመልክቶ
የተናገሩት ንግግር የትግራይ ክልል ሴቶችን
ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያንንም
ክብር የነካ ነው፤ በዚህም አዝነናል፤
ይቅርታም መጠየቅ ይኖርባቸዋል” ብለዋል፡፡