በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ትግራይ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ና ሽቶ ሚድያ ኮሚዩኒኬሽን አስተባባሪነት ተዘጋጅቶ ላለፋት 9 ቀናት በትግራይ ስታድየም ሲካሄድ የነበረው ትግራይ ዋንጫ ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል።
7 ክለቦችን በሁለት ምድብ በመክፍል የምድብ ጨዋታዎችን ያከናወነው ውድድሩ፤በውድድሩ ህገ መተዳደርያ ደንብ መሰረት ከየምድባቸው አንደኛ የወጡትን ተጋባዦቹ ወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና ለፍፃሜ ሲያገናኝ ከየምድባቸው ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁትን አክሱም ከተማ ና ሰሎዳ ዓድዋን ለደረጃ አገናኝትዋል።
ነገ 6:30 ሚጀምረው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች በሁለት ተከፍለው በሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ጅማሮውን በማድረግ የደረጃ ና የዋንጫ ጨዋታዎችን በማስከተል ፍፃሜውን ሚያገኝ ይሆናል።በየጨዋታው ኮከብ ተጨዋቾችን ስታር ታይምስ ዲኮደሮችን እየሸለመ ሚገኘው ትግራይ ዋንጫ፤የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች፣እና ኮከብ አሰልጣኝ እና ሌሎች ሽልማቶችን አካቶ ጨምሮ ነገ በደማቅ ስነ ስርአት ፍፃሜውን ያገኛል።
- ማሰታውቂያ -
የደረጃ ጨዋታ
7:30 | አክሱም ከተማ ከ ሰሎዳ ዓድዋ
የዋንጫ ጨዋታ
9:30 | ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና