ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ
ጥሎ ማለፍ ዋንጫን እሁድ ዕለት
አንስቷል፤ በተገኘው ድል ምን ተሰማህ?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- በኢትዮጵያ
ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ሐዋሳ ከተማን
በማሸነፍ ያገኘነው ድል በውስጤ
የፈጠረብኝ የደስታ ስሜት በጣም
ከፍ ያለ ነው፤ ፋሲል ከነማ እንደ
ልፋቱ፣ እንደ ጥረቱ፣ እና በሜዳ ላይ
እንደሚያሳየው ማራኪ የእግር ኳስ
አጨዋወቱ ከእዚህም በላይ ሌላ ድልም
ይገባው ነበርና ይሄን ዋንጫ በፕሪሚየር
ሊጉ አለአግባብ ላጣነው ዋንጫ እንደ
ማካካሻ ቆጥረነዋል፤ ደስታችንም እጥፍ
ድርብ ሆኗል፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ የጥሎ
ማለፉን ዋንጫ ባያነሳ እንደ ቡድኑ
አሰልጣኝነት በውስጥህ ምን ነገር
ሊፈጠር ይችል ነበር?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- ክለባችን
በእዚህ ዓመት የውድድር ተሳትፎው
ላይ ከነበረው ጥንካሬና እስከመጨረሻው
ቀን ድረስም የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ
ለማንሣት ከመፎካከሩ አንፃር የእሁድ
ዕለቱን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ባያገኝና
ዘንድሮ ያለምንም ስኬት የውድድር
ዘመኑን ቢያሳልፍ ለእኔ ብቻ ሣይሆን
ለቡድኑ ተጨዋቾች እንደዚሁም
ደግሞ በየሜዳው እኛን ለማበረታታት
እየተጓዙ፣ እየተንገላቱ፣ እየተጎዱና
ከፍተኛ መስዋትነትንም እየከፈሉ
ለሚገኙት ደጋፊዎቻችን ጭምር
ሁሉም ነገር አሳዛኝ ይሆን ነበርና በዚህ
ዋንጫ እግር ኳሳዊ ባልሆነ
መንገድ አለአግባብ ላጣነው
ዋንጫ ልንካስ ችለናልና ይሄ
መሆን መቻሉ አስደስቶኛል፡፡
ሀትሪክ፡- እሁድ ዕለት
ከፋሲል ከነማ ጋር ያሳካከው
ዋንጫ ለአንተ አራተኛው
ትልቁ ድልህ ነው ልበል?
አሰልጣኝ ውበቱ፡
– አዎን፤ ወደ አሰልጣኝነት
ህይወት ካመራሁበት ጊዜ
አንስቶ በትላልቅ ደረጃዎች
ሊጠቀሱ የሚችሉ ዋንጫዎችን
አሁን ላይ ሳገኝ አራተኛ ጊዜዬ
ነው፤ እነሱም ከእዚህ ቀደም
በ2002 ዓ.ም ላይ ከደደቢት
ጋር የጥሎ ማለፍ ዋንጫን
በ2003 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቡና
ጋር የፕሪሚየር ሊጉን እና
የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን
እና ከፋሲል ከነማ ጋር እሁድ
ዕለት የተጎናፀፍኩት የጥሎ
ማለፍ ዋንጫ ትልቁ ስኬቶቼ
ናቸውና የበፊቱን ድሎቼን
ያኔ ውጤት ባመጣንበት ወቅት
ለተገኘው ድል ክሬዲቱን በጊዜው ለነበሩት
የቡድኑ አባላቶች ስሰጥ የእሁዱን ደግሞ
ለአሁኑ የቡድናችን አጠቃላይ አባላቶች እና
ለደጋፊዎቻችን መስጠትን እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- የጥሎ ማለፉን ዋንጫ
ያገኛችሁት በፍፁም ቅጣት ምት በማሸነፍ
ነው፤ በእዚህ ዙሪያ እና በሜዳ ላይ
ስለነበረው እንቅስቃሴ ምን ትላለህ?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- ከሐዋሳ ከተማ ጋር
ያደረግነውን የፍፃሜ ጨዋታ ቡድናችን
በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፎ ዋንጫውን
ለማንሳት ቢችልም የዋንጫ ጨዋታዎች
ብዙ ጊዜ አንድ ነገር ከተሳሳትክ ዋጋ
ልትከፍል የምትችልበት ነገሮች ስላሉና
ጥንቃቄም አድርገህ የምትጫወትበት ሁኔታ
ስላለ ሜዳ ላይ ስለነበረው እንቅስቃሴ ብዙ
ማውራት ትርጉም ያለው አይመስለኝምና
በእሁድ ዕለቱ ጨዋታ የእግር ኳሱ አንዱ
አካል በሆነው የፍፁም ቅጣት ምት አሸንፈን
ዋንጫውን ስላነሳንና በኢንተርናሽናል
የውድድር መድረክም ፋሲል ከነማን
ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሳተፍ መንገዱን
ስላመቻቸንለት ይሄ ሊያስደስተኝ ችሏል፡፡
ሀትሪክ፡- በፍፃሜው ጨዋታ ከሐዋሳ
ከተማ ጋር ለመሸናነፍ ወደ ፍፁም ቅጣት
ምቶቹ ስታመሩ ምን አልክ?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- የፍፁም ቅጣት
ምቶች የጨዋታው አንድ አካል
ቢሆኑም ሁሌም ግን ከዕጣ
ያልተናነሱ ነገሮች ናቸው፤
በዚህ የፍፁም ቅጣት ምት ጊዜም
በዕለቱ ጥሩ ሲጫወቱ የነበሩት
የእነሱ መስፍን፣ ካቻና የእኛው
ደግሞ በዛብህን የመሳሰሉ
ተጨዋቾች የሳቱበት አጋጣሚ
ስለነበር ወደዛ ከማምራታችን
በፊት ምነው 30 ደቂቃ
ቢጨመር የሚል ነገር ነበር
በውስጤ ሲመላለስ የነበረውና
ቡድናችን ይሄ ዋንጫ ይገባው
ስለነበር በመለያ ምት ልናሸንፍ
ችለናል፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ
የጥሎ ማለፉ አሸናፊ በመሆኑ
በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ
ይሳተፋል፤ በእዚያ ውድድር ላይ
ቡድናችሁ ስለሚኖረው ቆይታ
ምን ትላለህ?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- የፋሲል
ከነማ እግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው
የፕሪሚየር ሊጉ ተሳትፎ
በሜዳ ላይ ያሳየው የጨዋታ
እንቅስቃሴ ደጋፊን በኳስ
ያረካ፣ በርካታ ጎል ያስቆጠረ
ትንሽ ግብ ብቻ የተቆጠረበት
እና ከፍተኛ ብርታትንም
የሚሰጡት ብዙ ደጋፊ ያለው
ቡድን ከመሆኑ አኳያ በቶታል
የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ
የሚኖረው የውድድር ተሳትፎ
ጥሩ ይሆንለታል፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ….?
አሰልጣኝ ውበቱ፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚ
የር ሊግ የእዚህ ዓመት ተሳትፎአችንን እግር
ኳሳዊ ነገሮች ባልነበሩበት ሁኔታ ዋንጫውን
ብናጣም የጥሎ ማለፉ ባለድል ሆነን በእዚሁ
ልንካስ ችለናልና ለእዚህ ላበቃን ፈጣሪያችን
ክብርና ምስጋና ይግባው፡፡
“አለአግባብ ላጣነው የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማካካሻ አግኝተናል” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ (ፋሲል ከነማ)�
Hatricksport team