በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ስሙ ከግብፁ ክለብ ኢኤንፒፒኣይ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በስፋት ሲያያዝ የቆየው አማኑኤል ገብረሚካኤል ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ከመቐለ 70 አንደርታ ጋር ለመቀጠል በመስማማት ዛሬ ፌርማውን አኑሯል።
በ2009 ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን መቐለን የተቀላቀለው አማኑኤል ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ አንዲያድግና ባደገ በሁለተኛ አመቱ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን አንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
- ማሰታውቂያ -
የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው አማኑኤል በመቐለ 70 አንደርታ የ3 ዓመት ቆይታው 46 ጎሎችን ለክለቡ ማስቆጠር ችሏል።