ባለሜዳው አርባምንጭ ከተማ የበላይነቱን ባሳየበት እንዲሁም እንግዳው ብድን ቅዱስ-ጊዮርጊስ በተዳከመበት የመጀመሪያው አጋማሽ ገና ጨዋታው በተጀመረ በ1 ደቂቃ ነበር ጎል ለመመልከት የቻልነው፡፡ በቀኝ መስመር በኩል ከወርቅይታደስ አበበ የተላከለትን ኳስ ፀጋዬ አበራ በጥሩ አቋቋም ላይ ለነበረው ለአንበሉ አማኑኤል ጎበና አመቻችቶ በማቀበል አማኑኤል ጎበና የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር አዞዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡
ከዚችም ጎል መቆጠር በሃላ ፈረሰኞቹ የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም በ15 ደቂቃ ከጋዲሳ መብራቴ ቅጣት ምት ሙከራ ውጪ ለጎል የቀረበ ሙከራ ማድረግ ሳችሉ ቀርተዋል፡፡ በተቃራኒው አርባምንጭ ከተማ በ25 ደቂቃ ከአማኑኤል ጎበና የተላከለትን የቅጣት ምት ኳስ በተከላካዩ ተመስገን ካስትሮ በግንባር ብትመታም አግዳሚ ብረቱን ታካ ስትወጣ አዞዎቹን የግባቸውን መጠን ወደ ሁለት ከፍ ምታደርግ አጋጣሚ ነበረች፡፡
- ማሰታውቂያ -
አርባምንጭ ከተማ ከሌላው ጊዜያት አጨዋወት ስልት ተለይቶ በተገኝበት በዚህ ጨዋታ በተለይም የመሀል እና የተከላካይ ክፍል ጥምረት እንዲሁም ሀይል የበዛበት አጨዋወት የፈረሰኞቹን የአጨዋወት ስልታቸውን አዳይተገብሩ ሲያደርጋቸው ተስተውለናል ፡፡ ይህም የአጨዋወት ስልት የተሳካለቸው ባለሜዳወቹ በ37 ደቂቃ በመሀሪ መና ጥፍት የተገኝችውን ኳስ ፀጋዬ አበራ በአግባቡ በመጠቀም አዞዎቹን ወደ 2-0 መሪነት ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
ከጎሉ መቆጠር በሃላ አርባምንጭ ከተማ ወደ ፊት በመጫወት ተጨማሪ ጎሎችን ለማግባት ሲጥሩ ተስተውለናል ይህም ልፍታቸው ሰምሮ ከ6 ደቂቃዎች በሃላ አንዳለ ከበደ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ሰላዲን ቤርጌቾ በእጁ በመንካቱ የዕለቱ ዳኛ ፍፅም ቅጣት ምት መስጠታቸውን ተከትሎ እንዳለ ከበደ ጎሏን በማስቆጠር የጎላቸውን ብዛት 3 በማድረስ በሜዳው የተገኝውን ደጋፊ ሲያስደስቱ ተመልክተናል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ጣጣቸውን ጨርሰው የገቡት አዞዎቹ የአጨዋወት ስልታቸውን በመቀየር ወደ ሃላ በማፀግፈግ ነጥባቸውን አስተብቀው ለመውጣት ሲጥሩ ተመልክተናል፡፡ በአንፃሩ ፈረሰኞቹ የማጥቃት ሀይላቸውን በማጠናከር መሀሪ መናን በአበባው ቡጣቆ እንዲሁም በሃይሉ አሰፍን በአዲስ ፈራሚው ሪቻርድ አፒያ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን በ56 ደቂቃ በአበባው ብጣቆ አማካኝነት የመጀመሪ ግብ የሚሆን ሙከራቸውን ሲያደርጉ ጥሩ ብቃቱን እያሳየ ባለው ፅሆን መርድ ልትከሽፍ ችላለች፡፡ እንዲሁም በ69ደቂቃ ሪቻርድ አፒያ አክርሮ የመታው ኳስ ኢላማዋን ሳትጠብቅ ወደ ውጪ ወታለች፡፡
አርባምንጭ ከተማ በመልሶ ማጥቃት አማካኝነት በመጫወት በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀሱ በነበሩት በታዳጊዎቹ ብርሀኑ አዳሙ እና አለልኝ አዘነ አማካኝነት ተጨማሪ ጎል የሚሆኑ ኳሶችን አግኝተው ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል፡፡ በተለይም በ65 ደቂቃ ብርሀኑ አዳሙ በረኛውን በማጠፍ ወደ ግብ ቢደርስም ኳሷ ገእግሩ አምልጣው የሄደችበት አጋጣሚ የምታፅቆጭ ነበር፡፡
ፈረሰኞቹ በሁለተኛው ግማሽ ጥሩ ቢንቀሳቀሱም በአንድነት አዳነ እና በተመስገን ካስትሮ የሚመራውን የአዞዎቹን የተከላካይ ክፍል ማለፍ ተስኖት የማስተዛዘኛ ጎል ማጎግባት ሳይችል ጨዋታውበመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠሩ ግቦች በአዞዎቹ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ድሉንም ተከትሎ በምክትል አሰልጣኙ ማትዮስ እና በግብ ጠባቂው ጃክሰን ፊጣ የተመራው አርባምንጭ ከተማ ነጥብን ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠናው ሲወጣ፡፡
በአንፃሩ ቅዱስ-ጊዮርጊስ ወደ መሪዎቹ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲሰናከል አድርጎታል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ጃክሰን ፊጣ – አርባምንጭ ከተማ
ጨዋታ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ፤ በደንብ ጠንክረን ሰርተን ነው ለዚህ ጨዋታ የቀረብነው ። በቀጣይ ጠንክረን ሰርተን ወደ ተከታታይ አሸናፊነት እንመለሳለን
ሻዝ ፒንቶ -ቅዱስ-ጊዮርጊስ
በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ አልነበርን በዚህም የተነሳ 3 ጎሎች ተቆጥረውብናል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ተሽለን ብንገኝም ጎል ማስቆጠር አልቻልንም፡፡ ቀጠይ ቀሪ ጨዋታወች ስላሉ ከዋንጫው ፉክክር አልወጣንም፡፡