በይስሀቅ በላይ
ሀትሪክ፡- በናይጄሪያው ሬንጅረስ 2ለ0
በሆነው ውጤት ከተሸነፋችሁ በኋላ ኒጀርያዊ
ዳኛ ስትወቅስና ስታማረር ነበር፤ ይህ ድርጊትህ
ምክንያት ለመደርደርና ሽንፈትህን ላለማመን
ያደረከው ያህል አያስቆጥርብህም…?
አሰልጣኝ ስዩም፡- ከመነሻው እኔ ምክንያት
በመደርደር የማንም ሰው አይደሁም፤ በአግባቡ
ተበልጬ የሚገጥመኝን ሽንፈትም የምቀበል
የምማርበት እንጂ ምክንያት እየደረደርኩ
ሽንፈቴን የማሽሞነሙን ሰውም አይደለሁም፡
፡ በናይጄሪያ የደረሰብኝ ሽንፈት ግን ከፍተኛ
የዳኝነት ተፅዕኖ የተፈጠረብን በመሆኑ ነው
ያማረርኩትና ዳኛውን የወቀስኩት፡፡
ሀትሪክ፡- ይሄን ያህል ለምሬት የሚያበቃ
ምን አይነት የዳኝነት አድልዎ ተፈፅሞብህ
ነው…?
አሰልጣኝ ስዩም፡-ቀደም ሲል በምዕራብ
አፍሪካ የሚደረጉ ጨዋታዎችን በተመለከተ
ከዳኝነትና ከፍትህ ማጣት ጋር በተያያዘ በወሬ
ደረጃ ስሰማው የነበረውን ነገር በአይኔ አይቼ
አረጋጋጫለሁ፡፡ ገና ከአዲስ አበባ ለጨዋታው
ተነስተን ስንሄድም ከተጨዋቾቼ ጋር በዳኝነት
ይደርሳል የተባለውን ችግር ፍራቻም ጥንቃቄ
እንዲያደርጉ በደንብ ተነጋጋረን ነው የሄድነው፡
፡ በተለይ 16፡50 አካባቢ በጣም ጥንቃቄ
እንድናደርግና ለዳኛው ኢ-ፍትሀዊ ውሳኔ
እንዳንጋለጥ ማስጠጋት እንደሌለብን ነው
ተነጋገረን የገባነው፡፡ ሜዳ ላይም ተጨዋቾቼ
ይሄን ለመተግበር 16፡50 ላለማስጠጋት ጥረት
ቢያደርጉም ዳኛው ንክኪን እንደጥፋት በማየት
ከአንድም አምስት ጊዜ አሳማኝ ያልሆኑ የቅጣት
አሰልጣኝ ዘማርያም እና አሰልጣኝ ስዩም
ከበደ ስለወሳኝ ጨዋታቸው ይናገራሉ
ክለቦቻችን በኢንተርናሽናል መድረክ
ምቶችን ሲሰጥብን የነበረው፤ በጣም የሚገርምህ
በጨዋታ ሳይቆጠርብን ሁለት ፔናሊቲ
ተሰጥቶብን ነው ተሸንፈን የመጣነው፡፡
ሀትሪክ፡- የፍፁም ቅጣት ምቶቹ (ፔናሊ
ቲው) መሰጠት የማይገባቸው ናቸው በአንተ
እምነት…?
አሰልጣኝ ስዩም፡- አሁንም ምክንያት
ለመደርደር አይደለም፤ የመጀመሪያው 76ኛው
ደቂቃ ላይ የተቆጠረብን እሺ ይሁን ሃምሳ ሃምሳ
ነው ሊያሰጥ ይችላል ብለን አልተቃወምንም፡
፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃ ሲቀረው
የተቆጠረብን ግን በምንም አይነት የማያሰጥ
ሆን ተብሎ የእነሱን እድል ለማስፋት የተሰጠ
ፔናሊቲ ነው፡፡ ተጨዋቹ ዳይቭ ራሱ ወድቆ
ፔናሊት መስጠቱ የተሻለ እድል ይዘን
እንዳንመለስ ያደረገ ኢፍትሃዊ ውሳኔ በመሆኑ
በዳኛው ውሳኔ ስሜታችን ክፉኛ ነው የተጎዳው፤
በጣምም ነው የተበሳጨነው፡፡ ይሄ ደግሞ
ምን ያህል እውነት ለመሆኑና ለሽንፈታችን
ምክንያት ለመደርደር እንዳልሆነ ከጨዋታው
መጠናቀቅ በኋላ በነበረው (Paost match
Interview) ከጋዜጦች ጋር በነበረው ቃለ-
ምልልስ ሁሉም ጋዜጠኞች ተመካክረው የመጡ
ይመስል “የዕለቱን ዳኛና የዳኝነት ውሳኔውን
እንዴት አገኘኸው?” ነበር ጥያቄያቸው፡፡
ሀትሪክ፡-ምን ምላሽ ሰጠሃቸው…ታዲያ…?
አሰልጣኝ ስዩም፡– አሁን በቅርቡ
የተደረገውን የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ
ጨዋታ በግብፁ አል-አሀሊና በቱኒዚያው
ኤስፔራንስ መካከል የተደረገውን ጨዋታ
የመራው ኢትዮጵያዊው በአምላክ ተሰማ
ነው፤ጨዋታውን እንዴት እንደመራው፣
እንዴ ክብርና ሞገስ ያገኘ ትልቅ ዳኛ እንደሆነ
አይታችኋል፡፡ እኛ የመጣነው እንደዚህ አይነት
ዳኛን ከፈጠረች ሀገር በመሆኑ በተቃራኒው
እንደዚህ አይነት ዳኝነት ስናይ በጣም ያሳዝናል
ብዬ ነው የመለስኩላቸው፡፡ በአጭሩ ጋዜጠኞቹ
ምንም እንኳን የሀገራቸው ቡድን ቢያሸንፉም
በውሳኔው መከፋታቸው ከጥያቄያቸው
ያስታውቃል፡፡ የፔናሊቲውን ከፍ አድርገን
አነሳነው እንጂ ዳኛው ተጨዋቾቹን እያስፈራራ
በእያንዳንዱ ንክኪ ፋውል ነው እያለ እያስቆመ
ቅጣት ምት እየሰጠ በነፃነት እንዳንጫወት
አድርጎናል፡፡ በዚህ ጨዋታ ስድስት የቢጫ ካርድ
ነው ለቡድናችን ያደለው ብልህ ታምናለህ?
ሀትሪክ፡- ከዚህ በመነሣት ሬንጀሮሶች
ሣይሆኑ የኒጀሩ ዳኛ ነው ያሸነፋችሁ ማለት
ይቻላል…?
አሰልጣኝ ስዩም፡- እንደዚህ አይነት
ድምዳሜ ላይ አልደረስኩም፤ በወቅቱ የነበረው
ዳኝነት ግን ውጤት ብቻ ሣይሆን የተጨዋቾችን
በነፃነት የሚጫወት ፍላጎት ነጥቋቸዋል፡
፡ የሬንጀርስ ተጨዋቾች ወደ ግብ ክልላችን
በመጡ ቁጥር ህጉ በሚፈቅደው መሠረት
ለመነካካት ሲፈሩ ከአሁን ከአሁን ቅጣት ምት፣
ከዚያ ከፍ ሲልም የፍፁም ቅጣት ምትና ቢጫ
ካርድ ይሰጥብናል ብለው እንዲሰጉ ተሸማቀው
እንዲጫወቱ በኢፍትሃዊ ውሳኔው በስነ-ልቦና
በኩል ከፍተኛ ጫና አሳድሮባቸዋል፡፡
ሀትሪክ፡- የዚህን ሁሉ የዳኝነት በደል
ምክንያት ከምን ጋር እናያይዘው…?
አሰልጣኝ ስዩም፡- ከላይ ብዬሃለሁ
በምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በእግር ኳስ ላይ
የሚሰሩ ሸፍጦችን በወሬ ደረጃ ብቻ ነበር
ስሰማ የነበረው፤ አሁን ግን በአይኔ አይቻለሁ፡
፡ ውጤት በሜዳ ላይ ጨዋታ ብቻ አይደለም
የሚፈልጉት፡፡ እኔ እንደገባኝ ሬንጀርሶች ወይም
የክለቡ አመራሮች ማንኛውም ቡድን እጅ
እንደማይሰጥና በቀላሉ ማሸነፍ እንደማይቻል
ስለሚገምቱ ውጤቱን ሀገራቸው ላይ ለመጨረስ
ካላቸው ህልመኝነት በመነሣት ይመስለኛል
ይሄን ሲያደርጉ የሚታዩት፡፡
ሀትሪክ፡- መከላከያ ሁለት ጎል በፍፁም
ቅጣት ምት ቢቆጠርበትም ውጤቱን ለማስቀየር
ግብ አስቆጥሮ በዳኛው አልተሻረበትም በማለት
በተቃራኒው ጥያቄ የሚያነሱ አሉ…?
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ስዩም፡-የዳኛው ውሳኔ የቡድኑን
የማሸነፉ መንፈስ ረብሾታል፤ በሙሉ ስሜት
ከመጫወት ይልቅ በስጋት መጫወት ውስጥ
እንዲወድቁ ጫና ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ግብ
ባናስቆጥርም በእኔ እምነት መቶ ፐርሰንት ግብ
መሆን የሚችሉ እድሎችን ፈጥረን አምክነናል፡
፡ በተለይ ዳዊት እስጢፋኖስ በጥሩ ቅብብል
ገብቶ እኛም ገባች ብለን ለመጨፈር ስንዘጋጅ
ልክ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ አዲስ አበባ ላይ
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ሲጫወቱ ሳላህዲን
ሠይድ ወደ ግብ ልኳት የናይጄሪያው ተከላካይ
ከመስመር ላይ ተንሸራቶ እንዳወጣበት አይነት
ኳስ የሬንጀርስ ተከላካይ ያወጣብን ኳስ እጅግ
የሚያስቆጭ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ምንይሉ ራሱ
ገብቶ ባላንስ ባለመጠበቁ እንዲሁም አንድ ሌላ
ኳስ ሁሉንም አምልጦ ከገባ በኋላ ከአርቲፌሻል
ሜዳው ጋር ባለመጣጣሙና ችካል አድርጎ
አጨራረሱን ባለማሣመሩ የሳታቸው ኳሶች
የሚያስቆጩ ግብ መሆን የሚችሉ ሙከራዎች
ናቸው፤ አልተሳካልንም እንጂ በዚህ ሁሉ
ችግሮች ውስጥ ሆነን ሞክረናል፤ ባናገባም ወደ
ጎል ጥሩ ደርሰናል፡፡
ሀትሪክ፡- 2ለ0 ነው ተሸንፋችሁ ነው
የተመለሳችሁት፤ ከዚህ ውጤት በመነሣት
ጨዋታው አልቋል ብሎ መናገር ይቻላል…?
ውጤቱን መቀልበስስ ይቻላል?
አሰልጣኝ ስዩም፡-አልቋል ብሎ መደምደም
አይቻልም፤ ጨዋታው ባለማለቁም ነው
የመልሱን ጨዋታ የምናደርገው፤ ከዚህ
አንፃር ጨዋታው አልቋል ብለንም አናምንም፡
፡ ውጤቱ ይቀለበሳል ወይ? ላልከው ከዚህ
በፊት በእግር ኳስ የተቀለበሱ ውጤቶችን
ስታይ ያገኘናቸውን እድሎች በአግባቡ መጠቀም
ከቻልን የማይቀለበስበት ምክንያት አይኖርም፡፡
አል-አሀሊ በሜዳው 3ለ1 አሸንፎ ጨዋታው
አለቀ ሲባል 3ለ0 ተሸንፎ ዋንጫ አጥቷል፣
ባርሴሎናም 3ለ0 ተሸንፎ ከውድድር ወጣ
ሲባል የሆነው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፣
የኢትዮጵያ ወጣት ቡድንም ግብፅ ላይ 5ለ1
ተሸንፎ በመልሱ ጨዋታ 5ለ1 ያሸነፈበት
ውጤትም አይረሣም፡፡ እነዚህ ነገሮች
የሚያስተላልፉት መልዕክት ተስፋ መቁረጥ
አስፈላጊ እንዳልሆነም ነው፤ እኛም በተለይ
በጨዋታው መጀመሪያ አካባቢ ባሉት ደቂቃዎች
ቀድመን ካገባን ነገሮች የሚለወጡበት ሁኔታ
ይፈጠራል፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው ግን በእለቱ
በምታሳየው አቋምና ቀድመህ የምታገኛቸውን
አጋጣሚዎች መጠቀም የመወሰን አቅም
ስላላቸው የሁላችንም ተስፋ ያለው እዛጋ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ሬንጀርስ ምን አይነት ቡድን
ነው…?
አሰልጣኝ ስዩም፡-በጣም ጥሩ ቡድን ነው፤
አካል ብቃታቸው በጣም የተሟላ ነው፤ ከመሃል
ሜዳ ጀምሮ እስከ አጥቂ ያሉት ተጨዋቾቻቸው
ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያውቁ ናቸው፡
፡ ይሄን ስልህ ግን ተከላካይ ክፍላቸው መጥፎ
ነው እያልኩህ አይደለም፤ ተከላካይ ክፍሉ
ኳስ ይዘን እንጫወታለን እያለ የሚዘናጋው
ነገር ስላለ ነው፤ ከዚህ ውጪ ግን ከአማካይ
ክፍሉ ጀምሮ ፉል ባኮቻቸው አጥቂዎቻቸው
የሚደንቅ ክህሎት አላቸው፤ ጠቅላላ እንደ
ቡድንም ስታያቸው በጣም የተጠናከረ ቡድን
ማለት እችላለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የጨዋታው መጠናቀቂያ ፊሽካ
ሲሰማ የውጤት ሰሌዳው መከላከያ ስንት?
ሬንጀርስ ስንት ይላል? ገምት…እስቲ?
አሰልጣኝ ስዩም፡- ግምት በእግር ኳስ
አስቸጋሪ ነው…፤ ቀድመን ግብ ማስቆጠር
ከቻልን ግን የአሸናፊነቱ ሚዛን ወደ እኛ ሊመጣ
ይችላል፡፡ ካልሆነ እኛም እንደ እነሱ ተመሳሳይ
ግብ አስቆጥረን ወደ ፔናሊቲ ልንሄድ የምንችል
ይምስለኛል…
ሀትሪክ፡- አንተ ወደ መከላከያ ከመጣህ
በኋለ ቡድኑ በውጤትም በእንቅስቃሴ ለውጥ
እያሳየ ነው፤ በሀገር ውስጥ ሊግስ ምን
እያሰብክ ነው…?
አሰልጣኝ ስዩም፡- በሀገር ውስጥ የመከላ
ከያን ባህል ለመቀየር እየሰራሁ ነው፤ ወደ
ክለቡ እንደመጣሁ ከክለቡ የቦርድ አመራሮች
ጄኔራሎች ጋር ስንነጋገር መከላከያ እንደ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቡናና እንደሌሎች ክለቦች ለምንድነው
ለሻምፒዮንነት የማይጫወተው? ይሄ
አመለካከት ተሰብሮ ለሻምፒዮናነት የሚፎካከር
ቡድን ነው መገንባት ያለብን አልኳቸው፡፡ እነሱም “በዚህ አመት የክለቡን እስትንፋስ በሊጉ አቆይልን፤ በሚቀጥለው አመት ግን ለሻምፒዮና የሚወዳደር ቡድን ለመገንባት ሞክር፤ እኛ ከጎንህ ነን” አሉኝ፡፡ አሁን በነበሩት ልጆች ላይ የጨመርኳቸው ልጆች አሉ፤ እነዚህ በእጄ ላይ ያሉት ልጆች በአቅም ደረጃ ስታያቸው ከማንም ክለብ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ ከጨዋታ ጨዋታ እየተናበቡ ነው፤ የመጫወት ውህደቱም የተሻለ ነገር ነው ያለውና አሁን ለሻምፒዮናነት ለመወዳደር ነው የምንጫወተው፤ ለዚያም ለሚያደርሰን ነገር አልመን እየሰራን ነው፡፡ ሀትሪክ፡-ቅ/ጊዮርጊስ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ሰበታ፣ የመን ድረስ ሄደን አሰልጥነሃል፤ ስኬታማም ሆነሃል፤ መከላከያ ላይ ምን የተለየ ነገር አየህበት? የስራ ነፃነቱስ? አሰልጣኝ ስዩም፡- መከላከያ ጥሩ የሥራ አየር የሚነፍስበት ትልቅ ክለብ ነው፤ የቦርድ አመራሮች ከሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊነትና ውጥረት እንዳለባቸው ቢታወቅም ለክለቡ ትኩረትና ጊዜ ሰጥተው ይከታተላሉ፡ ፡ እየደወሉ አጋርነታቸውን ያሳዩኛል፤ ይሄ በጣም ትልቁ ነገር ነው፡፡ በጽ/ቤት አካባቢም፣ ከቴክኒካል ስታፎቼ ጋርም በጣም ተናበን እየሠራን ነው ያለነው፡፡ በቆይታዬም በሥራዬም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ገደብ የሌለው የሥራ ነፃነትም ነው ያለኝ፡፡ ክለቡ በዚህ ደረጃ መዋቀሩ የተሻለ ነገር እንድታሰብ ያደርግሃል ለብሔራዊ ቡድን ሶስት ለኦሎምፒክ ቡድኑ ሁለት በድምሩ አምስት ተጨዋቾችን ሀገርን እንዲጠቅሙ ሰጥተናል፡፡ በአጠቃላይ በጥሩ ስሜት መስራት የሚያስችል የአየር ድባብ ያለበት ክለብ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ |