በዮሴፍ ከፈለኝ
ወደ ከፍታ የሚጓዘው የጌታነህ ከበደ ጉዞ የሚጀምረው 2001 ሚያዚያ የቀድሞ የደደቢት እግር ኳስ
መስራችና ፕሬዚዳንት ኮ/ል አወል አብዱራሂም አይን ውስጥ ሲገባ ነው፡፡ ያኔ በብሔራዊ ሊግ ይወዳደር
የነበረው ደደቢት ነገ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የሚፈራ ቡድን ለመሆን ራሱን ማጠናከር ተያያዘ፡፡ በኮ/ል አወል
አብዱራሂም እምነት በ2001 ብሔራዊ ሊግ ብንሆንም የነበረን አቋም ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አይተናነስም
ነበር ይላሉ፡፡ ኮ/ል አወል ጌታነህ ከበደ ተኮር መረጃቸውን እንዲህ እያሉ ይቀጥላሉ… “ጌታነህ ከበደን
የመለመለው ኮ/ል አወል ነው በዚህም ደስተኛ ነኝ በ2001 እንዳየሁት ተመችቶኛል ሚያዚያ ድረስ ግን
አልነገርኩትም፡፡ ከደቡብ ፖሊስ ጋር ያለውን ግዴታ እንዲወጣ እድል ሰጠሁት፡፡ ወደ መጨረሻ ላይ
እንደምንፈልገው ነግሬው ተስማማን፡፡ የብዙ ክለቦችን ጨዋታ እመለከት ስለነበር ገና እንዳየሁት ነው ተስፋ
እንዳለው የተረዳሁት፡፡ ፍጥነቱ፣ ኳስ አያያዙ፣ አጨራረሱ ወደፊት ስኬታማ እንደሚሆን ያሳይ ነበር፡፡ ለኛ
ከፈረመ በኋላ ውሉን በጥርጣሬ ያዩት አሰልጣኞች ነበሩ፡፡ “ለፕሪሚየር ሊጉ ይሆናል ብለህ ነው ያሉኝ
አሰልጣኞችን ምክር ባለመቀበል በውሳኔ ፀናው ውሳኔው ትክክለኛ መሆኑን ያወኩት ወዲያውኑ ነው፡፡ በ2001
ፕሪሚየር ሊጉን ስንቀላቀል ፌዴሬሽኑ አላለፋችሁም ብሎ የሕግ ክፍተት ፈጥሮ ውዝግብ ተነስቶ ስህተት
መሆኑን ሲያውቅ 4 ክለቦች እንድንወዳደር ይወስናል፡፡ ከእኛ ጋር የሚወዳደሩት ኒያላ፣ ሻሸመኔና ትራንስ
ነበሩ፡፡ ሻሸመኔ ግን ራሱን በማግለሉ በ3 ቡድኖች መሀል ውድድሩ ተካሄደ ደደቢት ትራንስና ኒያላን በጌታነህ
ከበደ ጎሎች በማሸነፍ በ2002 ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማለፋችንን አረጋገጥን፡፡ የድሉ ቁልፍ ሚና የጌታነህ
ከበደ እግሮች ነበሩ ኮከብ ጎል አግቢም ሆኖም አጠናቀቀ” ሲሉ ስለጌታነህ መስክረዋል፡፡ ጌታነህ ለደደቢት
አስፈሪ ተዋጊ ሆኖ 2002 ተጀመረ፡፡ ኮ/ል አወል ይቀጥላሉ….” ለጥሎ ማለፉ ግማሽ ፍፃሜ ደርሰናል ወሩ
ሰኔ ላይ ነው መከላከያን አሸንፈን ለዋንጫ ካለፍን የዋንጫ ተጋጣሚያችን ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ
በማሸነፉ በፍፃሜ ጨዋታ ተሸነፍንም አሸነፍንም በኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን መወከላችን ይረጋገጣልና
የግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ከዋንጫው ጨዋታ በላይ ተጠባቂ ሆነ፡፡ መከላከያ በመከላከል ላይ ጥሩ ስለነበረ ጎል
ማስቆጠር አልቻልንም፡፡ በጭንቁ ሰዓት ላይ ጠርቼ ጌታነህን አናገርኩት፡፡ ምንም ይሁን ምን ማሸነፍ
አለብን አንተም ሰብረህ መውጣት አለብህ ብዬ አነሳሳሁት፡፡ ለዘላለም የማልረሳውን የደደቢት ምርጡ
ተከላካይ ማሲንቆን፣ አጥቂው ተመስገንን ተክሌና ሌሎቹንም ጠርቼ አነቃቃኋቸው ጨዋታው
ሲያልቅ በጌታነህ ከበደ ጎል አሸንፈን ማለፋችንን ስናውቅ ውስጤ በተፈጠረ ደስታ የጌታነህ
ጀግንነትና ያሰበውን የማድረግ ብቃት አይቼ ገና እድሜው 19 አካባቢ ለሆነው ለዚህ ኮከብ “ሰብሮም”
ብዬ ቅፅል ስም አወጣሁለት በቃ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስሙ እንደሚመጥነው ለአመታት በተከታታይ
ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ሰበሮም ጌታነህ ከበደ ለኔ ጀግናዬ ነው ሲሉም ኮ/ል አወል ምስክርነታቸውን
ሰጥተውለታል፡፡ በዮርዳኖስ አባይ ለ16 አመታት ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የኮከብ ጎል አግቢነት ሪከርድ ጌታነህ መረከቡ የጎል ቀበኛነቱን ብዙዎች እንዲያምኑ አስገድዷል፡፡
ደቡብ ፖሊስ፣ ደደቢት፣ ቢድቪስት ዊትስና ደደቢት ባለፉት 10 አመታት የጌታነህን ጣፋጭ ጥቅም
የቀመሱ ክለቦች ናቸው፡፡
2011 የፈረሰኞቹ ማስፈራሪያ ሆኖ ብቅ ሊል የተዘጋጀው ጌታነህ ከበደ በቀጣዮቹ 24 ወራት
ጊዮርጊስን ሊያስፈነድቅ ደጋፊዎቹ በጉጉት እየጠበቁት ነው፡፡ በነገው እለት ከኬንያ ጋር ላለባቸው
ውሳኔ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጌታነህ የአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ የልብ ፍላጎት ምላሽ ሆኖ
ከፊት ይወደራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ የዋሊያዎቹ አምበል ጌታነህ ከበደ ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር
በነበረው ቆይታ ስለኬንያው ጨዋታ፣ ስላሰለጠኑት አሰልጣኞች፣ ስለተጨዋቾች የደመወዝ ክፍያ፣
ከጥሎ ማለፍ ውጪ ስለመሆናቸው፣ ስለ ደደቢት ቆይታው፣ ዘና ስለሚልበት ጉዳይ፣ ስለሊጉ
ዳኝነት ስለሀገሪቱ የበረኛ ችግር፣ ከጊዮርጊስ ተቀበለ ስለተባለው 5 ሚሊዮን ብርና ሌሎች ጉዳዮች
ሰፋ ያለ ምላሽን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ቃለ ምልልሱን ለማድረግ
ለሰጠኸኝ ፍቃደኛነት ከልብ አመሰግናለሁ?
- ማሰታውቂያ -
ጌታነህ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- “ሰበሮም” የሚለው ቅፁል ስም
ተመችቶሃል?
ጌታነህ፡- (ሳቅ) እኔ ይመቸኛል በጣምም
ደስተኛ ነኝ
ሀትሪክ፡- የውሃ ጥም ርካታና የጎል ጥም
ርካታን እንዴት ትገልጸዋለህ?
ጌታነህ፡- (ሳቅ) ሁለቱም ይለያያሉ፡፡
ጎል ከውሃ ርካታ ጋር አይወዳደርም፡፡ ጎል
ሳስቆጥር ደስ ይለኛል በተለይ በወሳኝ ጨዋታ
ላይ ያስቆጠርኩት ጎል ከሆነ በጣም ደስታዬ
ላቅ ይላል፡፡ የውሃ ጥምም ርካታ በጣም ደስ
ይላል፡፡ ርካታውም ለየት ይላልኮ!
ሀትሪክ፡–የዋሊያዎቹ ስብስብ ምን
ይመስላል?
ጌታነህ፡- በርካታ የዋሊያ ስብስብ
አይቻለሁ ባለፉት 2 አመታት ካሉት የዋሊያ
ስብስብ የአሁኑ ይሻላል ጥሩ አሰልጣኞችም
አሉ በሁሉ ነገር የአሁኑ ብሔራዊ ቡድን
የተሻለ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ኬንያ ጋናን
አሸነፈች የሚለው
መረጃ ለናንተ
ትንሽ ደንገጥ
አላደረጋችሁም?
ጌታነህ፡- ምንም ድንጋጤ አልተሰማንም፡
፡ ኬንያ ያን ያህል ከባድ አይደለችም፡፡ ጋና
በኬንያ 1ለ0 ብትረታም የነበራት አቋም
ልዩ ነው የተሻለ ተንቀሳቅሳለች ጋና በኬንያ
መሸነፉ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የለም ኬንያኮ
በሴራሊዮን ተሸንፋለች እኛ ደግሞ ሴራሊዮንን
አሸንፈናል ሁለታችንም አንዳችን ለሌላችን
ያስተላለፍነው መልዕክት ይኖራል እንጂ ለኛ
ኬንያ ስጋት ልትሆን አትችልም፡፡
ሀትሪክ፡–በ4 ቀን ልዩነት ወደ ናይሮቢ
ታቀናላችሁና የዚያን ውጤት መገመት
ይቻላል?
ጌታነህ፡–የአሁኑ ከፍተኛ ትኩረት
ባህርዳር ላይ ስላለው ጨዋታ ነው፡
፡ በሜዳችን የምናደርገውን ጨዋታ ሙሉ
የማሸነፍ እቅዳችንን ለማሳካት የምንችለው
እናደርጋለን፡፡ ናይሮቢ ላይ ያለውን ጨዋታ
ከባህርዳሩ ጨዋታ በኋላ ቢወራ መልካም
ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡– በተጨዋችነት ዘመን
በብሔራዊ ቡድን
ተሰላፊነትህ
ካየሃቸው
አሰልጣኞች
የአሁኑ
አሰልጣኝ በምን
ይለያል?
ጌታነህ፡
— በዋሊያ
ተሰላፊነቴ
በርካታ
አሰልጣኞችን
አይቻለው ቶምሴንት
ፊትና ማሪያኖ ባሬቶ
ከውጪ፣ ከሃገር ውስጥ
ደግሞ ሰውነት ቢሻው፣
ዮሃንስ ሳህሌ፣ ገ/
መድህን ኃይሌ፣
አሸናፊ በቀለን
አይቻለሁ፡፡ የቅርቦቹን
የአሰልጣኝ ሰውነት
ቢሻው፣ ገ/መድን
ኃይሌና አሸናፊ በቀለ
አንፃር ኢንስትራክተር
አብርሃም መብራቱ
ቡድኑ በግልፅ
እንዲወያይ አድርጓል፡
፡ በፊት በፊት
ማንም ተጨዋች
አይናገርም
ምክንያቱም
የመናገር
መብቱም
አልነበረውም፡
፡ ያኔ በትጥቅ ጉዳይ መናገር
የማንችልበት ደረጃ ላይ
ሳይቀር ደርሰን ነበር፡፡
አሁን ግን የፈለግነውን
እንጠይቃለን፡፡
አሰልጣኙ ለሁሉም
መብት ሰጥቷል
የፈለግነውን
የመጠየቅ እድል
አግኝተናል፡፡
አሰልጣኞቹ ስብስባ
ብለው ጠርተው
የማያወራ
ተጨዋች የለም፡
፡ ይሄ አሰልጣኝ
አብርሃም ለኛ
የጨመረልን
አቅምና መብት
ነው፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ሜዳ
ላይ ኳስ ይዘን
እንድንጫወት
ማድረጉ ሌላ
የሚለይበት
ሁኔታ ነው፡፡
ሀትሪክ፡-እንደ
ሲኒየሪነትህ ራስህን
እንደመሪ አላየኸም?
ጌታነህ፡-
እንደመሪማ በደንብ
ነው የማየው ልጆቹን
በደንብ ማነጋገር እችላለው፡
፡ ሽመልስ በቀለ፣ በረኛው
ሳምሶንና እኔ ሲኒየር ነን፡
፡ ምናልባት ኡመድ ሲመጣ
ትንሽ ስለሚቀድመን
የኛ ሲኒየር ይሆናል
ራሴን እንደመሪ ነው
የማየው፡፡
ሀትሪክ፡
-ኢትዮጵያ
ውስጥ ካሉ
ምርጥ አጥቂዎች
ሁለቱን ጥራ ብትባል ማንን ታስቀድማለህ?
ጌታነህ፡- ጌታነህ ከበደና ሳላህዲን ሰይድ
ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡-የሳላህዲን ተተኪስ ማን
ይመስልሃል ባለፉት አመታትኮ ሳላህዲን
የለም?
ጌታነህ፡- እገሌ ብለህ የምትጠራቸው
በወቅታዊ አቋም ብዙም የሉም፡፡ የአዳማው
ዳዋ ሁቴሳን መጥራት ግን ይቻላል፡፡
ሀትሪክ፡-ለተጨዋቾች የሚከፈለው
ደመወዝ በዝቷል ወይም በተቃራኒው አንሷል
የሚሉ አሉ…. አንተስ?
ጌታነህ፡- ከሌላው አለም አንፃር ካየነው
አይገናኝም የደቡብ አፍሪካ ሊግ ከኛ በትንሹ
ነው የሚሻለው ግን ክፍያው ከፍተኛ ነው
እዚያ ግን ስለ ክፍያ አያወሩም ሁነኛ
ሃሳባቸው ስለሊጉ ጥንካሬ እንጂ ስለ ተጨዋች
አያወሩም፡፡ እኛ ሀገር ብቻ ነው ስለ ደመወዝ
የሚወራው የፊርማ ክፍያ ይቅር ቢባልም
የፊርማው ወደ ደመወዝ ከመቀየሩ ውጪ
የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም፡፡ ለኔ ይበዛልም
ያንሳልም ማለት ይከብደኛል ተመጣጣኝ
ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡–ሁልጊዜ በኛ ሀገር እግር ኳስ
የሚገርምህ ምንድነው?
ጌታነህ፡-(ሣቅ) በኛ ሀገር እግር ኳስ
ብዙ ነገር ነው የሚገርመው፡፡ በኢትዮጵያ
ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳ ውጪ ሄዶ ማሸነፍ
አለመቻሉ ይገርመኛል፡፡ በምንም ምክንያት
ይሁን ተሸንፈህ ትመጣለህ፡፡ የጨዋታ
ብልጫ ቢኖርህም አሸንፈህ ሳይሆን ተሸንፈህ
ትመጣለህ ይሄ ሁሌ ይገርመኛል፡፡ በተይ
የዳኞች ደህንነት መጠበቅ አለበት ክልል
ላይ ጨዋታ ሲኖር ተጨዋቾች ላይ ያለው
ችግር ይከፋል ደጋፊው እንዲነሳሳ የሚያደርጉ
ተጨዋቾችም አሉ፡፡ ያ እንዲቆም ፌዴሬሽኑ
ትልቅ የቤት ሥራ አለበት፡፡ ደጋፊውም፣
ተጨዋቹም ይሁን ክለቦች ላይ ተገቢና
ተመጣጣኝ ቅጣት ከተጣለባቸው ችግሩ
ሊወገድ ይችላል ብዬ አስባለው የደቡብ
ክልል ክለቦችን ለመጥቀም ቢሮ ውስጥ ያለ
የክልሉ ተወላጅ ይከራከርና ቅጣቱን ያነሳል
የሌላውም ክልል እንዲህ ሲደረግ አይቼ ይህን
ታዝቤያለው በክልል ውክልና ቅጣት እንዲነሳ
ከተደረገ ማን ማንን ፈርቶ ዲሲፕሊኑን
ያክብር? እየተጫወትንኮ ፍፁም ቅጣት ምት
ክልል ውሰጥ ጠልፌህ እስቲ ወንድ የሆነ ዳኛ
ሪጎሬ ይስጠህ ብሎ የሚናገር ተጨዋች አለኮ፡
፡ የገባ ጎል ሁሉ ሊሻር ይችላልና ፌዴሬሽኑ
በ2011 ላይ ታላቅ ስራ ይጠብቀዋል ብዬ
አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡-ደጉ፣ አዳነ፣ አበባውና አሉላ
እንደወጡ ለጊዮርጊስ መፈረምህ ምን አይነት
ስሜት አለው?
ጌታነህ፡– የተለየ ነገር የለውም፡ እነርሱ
ቢወጡም ጊዮርጊስ ቤት እነሳላህዲን ባርጌቾ፣
በኃይሉ አሰፋ፣ ሙላለም መስፍን (ደጉ)፣ እነ
ምንተስኖትም ስላሉ ብዙም ችግር አይፈጥርም
ክለቡ እንደክለቡ ሊሰራ የሚገባውን ስራ
እየሰራ መሆኑን መናገር እችላለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከጥሎ ማለፉ መውደቃችሁ
ቅር አያሰኝም?
ጌታነህ፡- ዋንጫውን መውሰድ ይገባን
ነበረና ባለመሳካቱ ቅር ብሎኛል፡፡ ነገር ግን
ሪጎሬ ሀምሳ ሀምሳ በመሆኑ ያጋጥማል
ፔናሊቲ እነ ሮናልዶም ሆነ ሜሲ ስተዋል
በዓለም ዋንጫውም ላይ ተስቷል፡
፡ ኢንትርናሽናል ጨዋታ ባለመሳካቱ
በውስጣችን ቁጭት በመፈጠሩ ለ2011
እንወጣበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለማሳካት
ያስብከው ህልም ምንድነው?
ጌታነህ፡- ብዙ ዋንጫ የለኝም በቀጣዩ 2
አመት አመታት ይህን ለማሳካት እጥራለን
ሀትሪክ፡- ጊዮርጊስ የገባኸው ዋነኛ
ምክንያት ምንድነው?
ጌታነህ፡- ዋንጫ ነው፡፡ ዋንጫና ዋንጫ
ብቻ ነው ምክንያቱ?
ሀትሪክ፡- የክለቡ አመራሮች ፈልገውህ
ጥቂት ደጋፊዎች ሲጮሁ ነበር አሁን ላይ
ምን ትላለህ?
ጌታነህ፡- የተለየ ነገር የለም፡፡ ደጋፊው
ተቆጥቶ ሲከራከርህ ሜዳ ላይ አስቀይሞናል
በማለት ቅሬታ ማቅረባቸውን ሰምቻለሁ
በአቅም ማነስ እንዳልሆነ ግን ርግጠኛ ነው
ቅሬታው ብዙም አላሰከፋኝም፡፡
ሀትሪክ፡–ጊዮርጊስ ቤት ገብተህ የገረመህ
ምንድነው?
ጌታነህ፡-የዋንጫ ቡድን ነው፡፡ ትልቁ
ግዴታህ ዋንጫ ማግኘት ነው ማሸነፍና
ዋንጫ መውሰድ ለጊዮርጊስ ግዴታ ነው ሌላው
ክለብ ጋር ግን ከተቻለ መሀል ላይ መጨረስ
ይጠበቃል ከበረታህ ዋንጫ ይታሰባል፡
፡ ጊዮርጊስ ጋር ግን ይለያል አንድና አንድ
ዋንጫ ብቻ ማምጣት ይጠበቃል፡፡
ሀትሪክ፡- የደደቢት ያለፉት 2 አመታት
ጉዞ ደከም ብሏል ብሎ መናገር ይቻላል?
ጌታነህ፡-2009 እና 2010 ከፋፍለን
እንመልከት በ2009 ጅማሮውና ወደ
መጨረሻ አካባቢ ድረስ ጥሩ ነበረን፡፡ ነገር
ግን የመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች አካባቢ
በፋይናንስ እጥረት ለተጨዋቾቹ ደመወዝ
አለመከፈሉና ቅሬታ መፈጠሩ እየወረድን
እንድንመጣ አድርጎናል፡፡ በደረጃ ካየነው 2ኛ
ሆነን ጨርሰናል ጥሩ ነበረን ማለት ነው፤
ዋንጫ ይወስዳሉ ተብለን ተገምተንም ነበር
ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ልጆቹ እየተዳከሙ መጡ
ጭራሹኑ ደመወዝ ሳይከፈል ሲቀር የልጆቹ
ሞራል ተነካ አልተሳካም፡፡ በደደቢት 2009
ላይ የማበረታቻ ሽልማት አልነበረንም፡
፡ ዘንድሮም ማበረታቻ አይታሰብም፡፡ ይሄ
ደግሞ ክለቡን ደካማ እንዲሆን አድርጎታል
ጠንካራ ለመሆን ክለቦቹ ውጤታማ መሆን
አለባቸው፡፡ ሊጉ ላይ በጥንካሬ የሚታወቁት
ክለቦች በፋይናንስ የዳበሩ ናቸው፡፡ የፋይናንስ
እጥረት የደደቢትን አስፈሪነት ቀንሷል፡፡
ሀትሪክ፡- ደደቢት መቀመጫውን ወደ
ትግራይ ማዞሩ ምን ስሜት ፈጠረብህ?
ጌታነህ፡-አዲስ አበባን የሚወክሉ ክለቦች
3 ሆነዋል፡፡ የአዲስ አበባ ክለቦች ላይ ጫና
ይፈጥራል የአዲስ አበባ ተመልካቾች ብዙ
ጨዋታ እንዳያዩም ያደርጋል ግን ክልል
ወጥቶ ሀገርን ከማየት አንፃርም ጥሩ ጎን
አለው፡፡
ሀትሪክ፡-በደቡብ ፖሊስ ቆይታህ
የማትረሣው ምንድነው?
ጌታነህ፡- (ሳቅ) ብዙ ገጠመኞች አሉኝ፡፡
ክልል ላይ ስትወጣ ብዙ ነገሮችን ታያለህኮ
ደቡብ ፖሊስ ብዙም የፋይናንስ አቅም
የለውም ነበርና ፍራሽ ተይዞ ይኬድ ነበር፡፡
ሆቴል ለ2 ሰው ከተያዘ 2 ተጨማሪ ሰዎችን
የሚያስተኛ ፍራሽ ይገባል፡፡ እኔ ግን ስሄድ
አላወኩም ነበርና ፍራሽ ይዤ ሳልሄድ ቀርቼ
ከሌሎቹ ጋር ተዳብዬ የተኛሁበትን መቼም
አልረሳም፡፡
ሀትሪክ፡-፡-ከኳስ ውጪ በምን ዘና
ትላለህ?
ጌታነህ፡- ፊልም ማየት ደስ ይለኛል
በተለይ የሀገር ውስጥ ፊልም ማየት
ያዝናናኛል
ሀትሪክ፡-ከሀገር ውሰጥ የትኛውን ፊልም
ወደድክ?
ጌታነህ፡-ብዙ ፊልሞች አሉ፡፡ ከሁሉም ግን
በጭስ ተደብቄ የሚለው ፊልም ተመችቶኛል፡፡
ሀትሪክ፡-በትወናው የወደድከው አርቲስት
አለ?
ጌታነህ፡- አዎ ግሩም ኤርሚያስ
ይመቸኛል
ሀትሪክ፡- ስለ ፖለቲካ እናውራ..
ይመችሃል?
ጌታነህ፡- ስለ ፖለቲካ ማውራት
አልፈልግም አይመቸኝም
ሀትሪክ፡- ስለ ዶ/ር አብይ አህመድ
አናወራም?
ጌታነህ፡-ይቅርብኝ… ፖለቲካውን ማወቅ
አልፈልግም (ሳቅ) የሀገር ጉዳይ ሲሆን ነው
የምከታተለው እንጂ ብዙም የፖለቲካ ሰው
ወይም ትኩረቴን አይሰብም (ሳቅ)
ሀትሪክ፡- ለማሳካት ፈልገህ ያልቻልከው…
የቀጣይ ዘመንህ እቅድ ምን ይሆን?
ጌታነህ፡-በህይወቴ በኳሱ ማሳካት
የምፈልገው ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለው
ዋንጫ ይቀረኛል ብዙም የለኝምና ከጊዮርጊስ
ጋር በርካታ ዋንጫዎችን መውሰድ
እፈልጋለው
ሀትሪክ፡- በዳኝነት የተደሰትክበት ወይም
ያዘንክበት ጨዋታ የለም?
ጌታነህ፡-ብዙ ጊዜ እንደ ክልል ሳትሰጋ
የምትጫወትባቸው ሜዳዎች አሉ፡፡ በጣም
እየፈራህ የምትጫወትበት ሜዳም አለ፡
፡ ኳስ ስትጫወት ሁለተ ነገር እያሰብክ
ሲሆን ይደብራል፡፡ ዳኝነቱን በተመለከተ
ተበሳጭቼ የወጣሁት ደደቢት ከሲዳማ ቡና
ሲጫወት ነው፡፡ 4 ጨዋታ ተቀጥቼ ተመልሼ
4 ጨዋታ በተከታታይ ጎል ሳላስቆጥር የ5
ጨዋታው ከሲዳማ ቡና ጋር ነበር ያኔ
ጎል ለማግባት ጓጉቼ ነበር ተሳክቶልኝ ጎል
ባስቆጥርም ኦፍሳይድ ነው ተብሎ ተሻረብኝ
ዳኛው አመራሩ ልክ አልነበረም በጣም
ተበሳጭቻለው፡፡ ክልል ላይም ሆኖ ጥሩ ጥሩ
የተዳኘንባቸው ጨዋታዎችም ነበሩ፡፡
ሀትሪክ፡-የውጪ ኳስ ተከታታይ ከሆንክ
የየትኛው አጥቂ አድናቂ ነህ?
ጌታነህ፡-የውጪ ሊጎችን እከታተላለሁ..
በተለይ ምሽት ላይ ያልሆኑ ጨዋታዎችን
በይበልጥ የማየት እድል አለኝ አለም ላይ
የአጥቂ ችግር በዝቷል፡፡ ሀገራችን ላይ አጥቂ
የለም ይባላል እንጂ የአጥቂ ችግር ከኢትዮጵያ
አልፎ የአለም ችግር ሆኗል፡፡ ካሉት ግን
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጎል ሲያስቆጥር ደስ
ይለኛለ፡፡ ጎል ካላገባ ደግሞ ይደብረኛል፡፡
ሀትሪክ፡- እኛ ሀገር ያለው ችግር ከአጥቂ
ዘልሎ የበረኛም ነው አይደል?
ጌታነህ፡-የኢትዮጵያ ችግር ብዙ ነው
በረኛና አጥቂ ብቻ አይደለም ብዙ ችግር
አለብን፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ 0ለ0 ሲወጣ የአጥቂ
ችግር ነው ይባላል ሲሸነፍ የበረኛና የተከላካይ
ችግር ነውም ይባላል፡፡ ሁሌ ከችግር አይፀዳም
ምክንያቱም ጎል የሚያገባው አጥቂ ብቻ
አይደለም ይሄ መዘንጋት የለበትም፡፡
ሀትሪክ፡–ሕግ ቢወጣና የውጪ በረኛ
አይቻልም ቢሆን ጥቅም አለው?
ጌታነህ፡- አዎ! ግብፅኮ ይህን ሕግ
ተጠቅማለች፡፡ የውጪ በረኛ መኖር የለበትም፡
፡ ቻይናም ተመሳሳይ ሕግ አላት፡፡ ኢትዮጵያ
ላይ ያለው የውሳኔ ችግር ነው የውጪ በረኛ ይቀራል ብለው ነግረውን ነበር
ነገር ግን ተግባራዊ አልሆነም የኢትዮጵያ
ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለመሳተፍ ገብተው
ምንም ተፅዕኖ የማይፈጥሩ የውጪ ሀገር
በረኛ ገዝተው ያጫውታሉ ይሄ መታረምና
ፌዴሬሽኑ ጠንካራ አቋም መያዝ አለበት፡
፡ ይህው መከላከያ በሀገር ውስጥ በረኛ
ተጠቅሞ የተሻለ ውጤት አምጥቷል፡፡
ይሄ ለአብነት መታየት አለበት፡፡ አንዳንድ
ክለቦችም ጥሩ ውጤት በኢትዮጵያዊያን
በረኞች እያስመዘገቡ ነው ለብሄራዊ ቡድኑ
ከታሰበ ሕጉ ቶሎ መወሰን አለበት፡
፡ ብሔራዊ ቡድናችንም ተጎድቷል፡፡
አንዳንዴ የሚመጡት በረኞች በክለቦቻቸው
ያልተጫወቱ ናቸው፡፡ ለክለባቸው ተጠባባቂ
ሆነው ለብሔራዊ ቡድኑ በቋሚነት የሚመጡ
በረኞች አመጣጥ መቅረት አለበት፡፡ ቡድኑ
እንዳይጎዳ ከታሰበ ሕጎች ሊወጡ ይገባል፡
፡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ በረኛ የለንምኮ
አንድም የለም፡፡ በበረኛ ጉዳይ ያለው ሁኔታ
አይስማማኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ፍቅረኛ እንዳለህ ሰማሁ…
እውነት ነው?
ጌታነህ፡- (ሳቅ በሳቅ) አዎ የፍቅር ጓደኛ
አለኝ
ሀትሪክ፡- ጠንካራ የበር መዝጊያ
አግኝታለች ማለት ይቻላል?
ጌታነህ፡- (ሣቅ በሳቅ)
ሀትሪክ፡- ጨረስኩ… የመጨረሻ ቃል
ካለ… ?
ጌታነህ፡- ብሔራዊ ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ
እየተዘጋጀ ነው ያለው፡፡ የተወሰኑ ተጨዋቾች
ባይመጡልንም ያለነው ጠንክረን እየተዘጋጀን
ነው (ቃለ ምልልሱ የተሰራው ሃሙስ ምሽት
ነው) የተወሰኑት ደግሞ ተጎድተውብናል፡፡ ነገር
ግን ህብረተሰቡን ለማስደሰት ተዘጋጅተናል፡፡
የባህርዳር ህብረተሰብ ደግሞ ለኳስ ልዩ ፍቅር
አለው ከሌሴቶ ጋር ስንጫወት ስታዲየሙ
ሙሉ ነበር ጨዋታው ረቡዕ ዕለት ሲካሄድም
ስታዲየሙ በደጋፊዎቻችን ሞልቶ በድል
እንደምጨርስ ተስፋ አደርጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- የመጨረሻ መጨረሻ…..
ጌታነህ 100 ሺህ ብር የፊርማ ክፍያ ብቻ
አይደለም 5 ሚሊዮን ብርም ወስዷል የሚሉ
አሉ… ሰበሮም እንደው ከ100 ሺው ውጪ
ቤሳቤስቲን የለም?
ጌታነህ፡- (ሳቅ) ብዙ ሊወራ ይችላል
ማንም ወሬውን ማቆም አይቻልም፡፡ እውነቱ
ወደ 145 ሺ ብር አካባቢ ይከፈለኛል የተጣራ
100 ሺብር በየወሩ በእጄ ላይ ይደርሰኛል በቃ
እውነቱ ይህ ነው፡፡
ስለ ጌታነህ ምን ይላሉ?
“ስለርሱ ምን የማላወራው ነገር አለኝ፤ በችግር
ጊዜ ደራሽ ነው እስቲ ስለ ደራሽነቱ ላውራህ፡
፡ ባለቤት ታማ ጥቁር አንበሳ 18ቀናት
ተኝታለች ጌታነህ 18ቱን ቀናት ከኔ ጋር
በረንዳ ላይ እያደረ ያስታመማት የአደጋ ጊዜ
ጓደኛዬ ነው፡፡ በኢትዮጵያ 16 ከ50 ውስጥ
ልዩ የአጨራረስ ብቃት ያለው እርሱ ነው፡፡
ሳላሀዲንን ካየህ ከሩቅ በሹት መትቶ ያገባል
ሲባል ጌታነህ ደግሞ የ16 ከ50 ተጨዋች
ነው ብዬ አምናለው፡፡ በኔ እድሜ ካየኋቸው
አጥቂዎች በጠቅላላ ትልቁ እርሱና ሳላህዲን
ናቸው፡፡ 16 ከ50 ኳስ ካገኘ እግሩን ሳይሆን
ጭንቅላቱን የሚጠቀም ምርጥ አጥቂ ነው
ለሀገሩ የደረሰና ሀገሩን ያስጠራ ቤተሰቡን
የሚረዳ ለቤተሰቡ ራሱን የሰጠ የቅርብ
የምለው ጓደኛዬና ወንድሜ ጭምር ነው”
አዳነ ግርማ
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ተጨዋች
“በደደቢትም በዋሊያዎቹ ተሰላፊነቴም
አብሬው ተጫውቻለሁ፡፡ ሲበዛ መሸነፍን
የሚጣላ እንኳን ተሸንፈን በጨዋታ ከተበለጥን
ተበሳጭቶ ከጓደኞቹ ጋር የሚጋጭ ውጤትና
ድል የሚጠማው አልሸነፍ ባይ ተጨዋች ነው
በኛ ሀገር ካሉ አጥቂዎች የሚለየው ያገኘውን
የጎል ማስቆጠር እድል ሳያበላሽ የሚጠቀም
መሆኑ ነው፡፡ በባህሪው ለጓደኞቹ መልካም
የሆነ ለኳስ ህይወቱን የሰጠ ተጨዋች ነው”
የቀድሞ የደደቢት አምበል ብርሃኑ ቦጋለ
(ፋዲጋ)
“ጌታነህ ትልቅ ተጨዋች መሆኑ
የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ውጪ
ወጥተው መጫወት ከቻሉ ጥቂት ተጨዋቾች
መሀል አንዱ ነው፡፡ ለብሔራዊ ቡድን
ወሳኝ ሆኖ አመታትን አሳልፏል፡፡ እሁንም
ለብሔራዊ ቡድን ወሳኝ መሆኑ ለቅዱስ
ጊዮርጊስ መፈረሙ ትልቅነቱን ያሳያል፡፡
ባለፉት አመታት ወሳኝ አጥቂ ሆኖ አቋሙ
ሳይዋዥቅ ለአመታት መጫወቱ አቋሙ
እንዳይወርድ ጠንካራ ልምምድ ሳያቋርጥ
መስራቱ የጌታነህን ምርጥ ተጨዋችነት
ያሳያል”
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ /የዋሊያዎቹ ም/ል
አሰልጣኝ/
* ፎቶ ምንጭ © ከክምችት ክፍላችን ፤ ከgoogel እና ከማህበራዊ ትስስር ገፆቹ