የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንአበረታች መድሀኒት ሲጠቀሙ ለተገኙ አትሌቶች ምንም አይነት ይቅርታ አያደርግም አሉ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃ ሀይሌ ገብረ ስላሴ።
በወቅታዊው የፀረ – ዶፒንግ እንቅስቃሴ ዙሪያ ፌዴሬሽኑ ትናንት ለውጭ ሃገርና ለሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህ ወቅት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃሀይሌ ገብረ ስላሴ፥ አበረታች መድሃኒትተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች የእድሜ ልክ እገዳ እንደሚጣልባቸው ተናግረዋል።ፌዴሬሽኑ ለእውነተኛ እና ንፁህ አትሌቶች መብት መከበር ግን በማንኛውም ሁኔታ እስከ፡መጨረሻ ድረስ ይሟገታልም ነው ያሉት።
- ማሰታውቂያ -
ከዚህ በኋላ ከአበረታች መድሃኒቶች እና ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ከተጠረጠሩ አትሌቶች፣ ማናጀሮች እና አሰልጣኞች ጋር ፌዴሬሽኑ አብሮ የማይሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ከብሄራዊ የፀረ- አበረታች መድሃኒት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት እንደ አውሮፓውአቆጣጠር በ2017 200 ናሙናዎችን በመውሰድ ምርመራ ለማስራት ማቀዱንም ነው የገለጹት።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እና ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የእገዳ ቅጣት በተጨማሪ የኢፌዴሪ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 526ን መሰረት በማድረግ ከአበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ጋር ተያይዞ ወንጀል የሰራ ማንኛውም አካል በኢትዮጵያ ህግም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ።