አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ በዋግ ህምራ ዞን ፃግብጂ ወረዳ በዳስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የገልኩ ትምህርት ቤት ሙሉ ወጪውን ችሎ ለመገንባት ቃል ገብቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ሚያዚያ 27/2011 ዓ.ም. በቦታው ተገኝቶ መሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታውን መጀመር እንደሚችል ከትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በዚሁ ዓመት ተገንብቶ የሚጠናቀቅና በመጪው ዓመት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
- ማሰታውቂያ -
via- ENA 📷