ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር
ኳስ የመጨረሻውን ስልጣን ጨብጠዋል፡፡
በቀጣይ አራት ዓመታትም “ያልጨረስኩት
የቤት ስራ አለ” በሚል ከፌዴሬሽኑ ፅ/
ቤት ላለመውጣት ለፕሬዝዳንትነት እጩ
ተወዳዳሪ ሆነው በድጋሚ ቀርበዋል፡፡
“ፍፁም ቅንና ግልፅ ያመኑበትን ከመናገር
ወደ ኋላ የማይሉ” ሰው ናቸው በማለት
ብዙዎች ምስክርነታቸውን የሚሰጡላቸው
አቶ ጁነዲን ባሻህ የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ
ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይየእግር ኳሱን
የመጨረሻ መሪ ጨብጠው የሚዘውሩትን
ሰው በድጋሚ እመረጣለሁ ብለው ያስባሉ?
ብሎ ጠይቋቸው “ድምፁ እግር ኳስን
ማዕከል አድርጎ ከተሰጠ ምን ገዶኝ” የሚል
እርግጠኝነት የተሞላበት ምላሽ ሰጥተውታል፡፡
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ አቶ ጁነዲን ወደ ሞሮኮ
ከማቅናታቸው በፊት በእግር ኳሱ ትኩሳት
ዙሪያ ድፍረት ያላቸው ጥያቄዎችን አንስቶ
ድፍረት ያላቸው ምላሾችን አግኝቷል፡-
ሀትሪክ፡-የፌዴሬሽኑ ምርጫ በርካታ
ወራትን መውሰዱ የስፖርት ቤተሰቡ
እንዲያዝን ብቻ ሳይሆን እንዲሰላችም
አድርጎታል፤ አቶ ጁነዲን እንደ ፌዴሬሽን
ፕሬዝዳንትና እንደ እግር ኳሱ የመጨረሻው
የስልጣን ባለቤት በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
አቶ ጁነዲን፡- እኔም ምርጫው በየጊዜው
መራዘሙ አያስደስተኝም፤ በተደጋጋሚ
በመራዘሙ ምክንያት ሰዉ እንደሚያዝነውና
እንደሚሰላቸው ሁሉ እኔም በጣም ነው
የማዝነው፡፡ ነገር ግን በሌላ በኩል ምርጫው
በዚህ ደረጃ እየተራዘመ ያለው ለምንድነው
የሚለውን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ሁለት ወገኖች
አሉ አንደኛው ወገን ስለዝርዝር ህጎች ብዙ
መስማት አይወድም፤ ስለካፍ፣ የፊፋ ህግ፣
ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መተዳደሪያ ደንብ
መስማት አይፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ቶሎ
ለምን ምርጫውን አድርገን አንገላገልም ብቻ
የሚል ነው፡፡ ለምን ስለ ህጋዊነቱና ህጋዊ
ባለመሆን በአገር ላይ የሚመጣውን ለምን
ማሰብ እንደተሳናቸው አላውቀም፡፡ በተወዳዳሪ
ተገቢነት በምርጫ መነፅር ውስጥ ማለፍ
አይፈልጉም፤ ይሄ አንደኛው ነው፡፡ ሌላኛው
ወገን ደግሞ ስለመራዘሙ ቅሬታ ቢኖረውም
በልኩ ነው የሚያስበው፡፡ ለምን ህጋዊነት
ካልተላበሰ ለፉትቦሉ ጥሩ እንደማይሆን
ያስባል፡፡ እኛ ብናደርገውም ፊፋና ካፍ
አይቀበሉት ይሆናል የሚል ስጋት ስላለው
ከዚህ አንፃር እንደዚህ ነው የሚያስብው፡
፡ ምርጫው በየጊዘው መራዘሙ የህዝቡን
ስሜት እንደጎዳውና ደስታቸውን እንደነጠቀው
ሁሉ የእኔን ደስታ ነጥቆኛል፡፡ ስለዚህ
ምርጫው ቶሎ ተደርጎ እንዲያልቅ ፍላጎቴ
ነው፡፡ ነገር ግን ለመጨረስ ሲባል ብቻ መልሶ
የሚያስቀጣ ጣጣ ውስጥ የሚከተን ፊፋና ካፍ
የማይቀበሉት ነገር መስረት አለብን ብዬም
አላምንም፤ ህግን ተከትሎ ቶሎ ቢፈፅም ጥሩ
ነው የሚል ስሜት ነው ያለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- አቶ ጁነዲን እዚህ ጋር
እንደውም አንድ ነገር ልጠይቅዎት፤ ከ130ኛ
በላይ ደረጃ ውስጥ ላለ እግር ኳስ ይሄ ሁሉ
ግብግብና ትርምስ፣ ምርጫውን ለማካሄድ
ይሄ ሁሉ ወራት መውሰዱ በውስጥዎ የሀዘን
ስሜትስ አልፈጠረም?
አቶ ጁነዲን፡- እውነት ለመናገር በጣም
አዝናለሁ፡፡ የተዳከመን እግር ኳስ ለመመራት
እንደዚህ አይነት ጦርነት (ውጊያ) መካሄዱ
ያሳዝነኛል፡፡ ክለቦቻችን አደረጃጀታቸው፣
ፋይናሽያል አቅማቸው፣ ቴክኒካል
ብቃታቸው፣ የብሄራዊ ቡድናችን ደካማ
ውጤት ብቻ ብዙ የሚያሳስቡንና ጦር ሰብቀን
ልንዋጋቸው የሚገቡን ስራዎች አሉ፡፡ በዚህ
ላይ ሰው ቢጣላ ደስ ይላል፡፡ ሰው ተመላልሶ
ሲመጣ አሁንም መልሶ የፉትቦሉ ስልጣን
ላይ ካልተቀመጥኩ ብሎ ውዝግብ ውስጥ
ሲገባ ሲታይ ያስከፋል፤ ተስፋም ያስቆርጣል፡
፡ ደግሞ ነገሮችን እያጎሉ፣ እያጋነኑ ወይም
እየጨመሩና እየቀነሱ ከኢትዮጵያ ባህል ውጪ
የሰው ስም እያነሱ ወዳልሆነ አቅጣጫ መሄድ
ሁኔታውን የበለጠ አሳዛኝ አድርጎታል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤውም ቢሆን በረጋ መንፈስ ማየት
ይኖርበታል፡፡ ከአካባቢነት፣ ከቡደንተኝነት
የፀዳ ለፉትቦል የሚጠቅም ሰው የመምረጥ
ብቃት ሊኖረው ይገባል፡፡ ለፉትቦሉ እንጂ
ነገሮችን ከግለሰብ ጋር ባናገናኝ ከክልል በላይ
ኢትዮጵያን ብናስብ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም
ኢትዮጵያን ስናስብ ክልልን እናገኛለን፡
፡ ከጥቃቅን፣ በጠረጴዛ ስርና ዙሪያ በየኮቱ
እና በየቡሉኮው ስር የሚደረጉ ግርግሮች፤
በየሆቴሉ ከሚደረጉ ዱለታዎች እራሳችንን
አፅድተን መቅረብ አለብን ብዬም አስባለሁ
እና ከልዩ ልዩ ንክኪዎች እርቀን መቀመጥ
አለብን፡፡ ምንም ድሆች ብንሆንም ክብራችንን
መጠበቅና ኩሩዎች መሆን አለብን፤
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ኩሩነት ነውና፡፡
ሀትሪክ፡- እንዲህ ሲሉ አንድ ነገር ትዝ
አለኝ፤ ምርጫውን ተከትሎ ከሚረጨው
ገንዘብ፣ ሰዎች በቡድን ተደራጅተው
ከሚያደርጉት ሩጫ፣ የጉባኤውን አባላት
ድምፅ ለማግኘት የሚደረገውን ማባበልና
ማግባባት፣ በየሆቴሉ ከሚደረጉ ድብቅ
ስብሰባና ከሚበተነው ገንዘብ አንፃር ሲታይ
እውነት ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለእግር ኳሱ
ከመጨነቅና እግር ኳሱን ለመታደግ ታስቦ
ነው ብሎ መናገር ይቻላል?
አቶ ጁነዲን፡- እንደዚህ ነው ብሎ
ማሰብ ያስቸግራል፤ ሁሉም ለእግር ኳሱ
አያስብም፣ ሁሉም በዚህ ስራ ውስጥ ነው
ብሎ መደምደም ቢያስቸግርም አንዳንዶች
የሚበትኑት ነገር ወይም የሚያደርጉት
ሩጫ ለእግር ኳሱ ከመቆርቆር ወይም
እንቅልፍ ከማጣት ነው ብሎ ለመገመት ግን
ይከብዳል፡፡ ሁሉንም የጠቅላላ ጉባኤ አባላት
እዚህ ውስጥ መደመር ቢያስቸግርም በጣም
የተወሰኑ ግለሰቦች የሚያደርጉት ግርግር
እና ወገን ይዞ መጮህ ግን የሚያሳዝን ነው፡
፡ እንደዚህ አይነት ነገሮች ከሀገር ይልቅ
ለተሰጣቸው ተልዕኮ የመወገን ነገር እንደሆነ
ለመረዳት አይቸግርም፡፡ ሚዲያውንም ይዘው
የሚጮሁት ተመሳሳይ ግለሰቦች ናቸውና
አንዳንዴም እነዚህን ሰዎች መጠንቀቅ
ያስፈልጋል፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ
የመጡበትን ጊዜ በመልካምነቱ ነው
የሚያነሱት?
አቶ ጁነዲን፡- በፈታኝነቱ ነው የማነሳው፡
፡ ከብዙ ሰው ጋር የሚያገናኝ፣ ብዙ ሰው
አእምሮውን እጅና እግሩን የሚከትበት
ቦታ ነው እግር ኳስ፡፡ ሁሉም አውቃለው
የሚልበት፣ በስሜት የሚናጥበት ቦታም ነው፡፡
በአብዛኛው ነቀፌታ የሚበዛበት፣ ወንበሩ በጣም
የሚያቃጥል ቦታ ነው እግር ኳስ ፌዴሬሽን፡
፡ እዚህ ውስጥ ሆኖ መስራት መፈተን ነው፡፡
መፈተን በራሱ የምትቋቋምበት ጠንካራ ትከሻ
ካለህ በአንድ በኩል ደስታ ይሰጥሃል፡፡ ያንን
ፈተና ተቋቁመህ እዛ ውስጥ መቀመጥ ብቻ
ሳይሆን እንደሀገር አስተዋፅኦ ማድረግ የበለጠ
ደስታ ይሰጥሀል፡፡ ይሄ ሁሉ ንትርክ፣ ይሄ
ሁሉ ጨምሮ መናገር፣ ጠዋት ማታ ጭቅጭቅ
መስማት የእግር ኳሱ አንደኛው ገፅታ ቢሆንም
በሌላ በኩል ደግሞ እግር ኳስ ብዙ ሰው
የሚወደው፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከነጋዴ
እስከ ገበሬ፣ ከገጠር እስከ ከተማ የሚያፈቅረው
ተወዳጅ ስፖርትን መምራት የተለየ ደስታን
ያጎናፅፍሀል፡፡ በዚህ በኩል ብደሰትም
የኢትዮጵያ ፉትቦል ተሻሽሎ ለውጥ አምጥቶ፣
ብሄራዊ ቡድኑ ሀገር በሚያስከብር ደረጃ ላይ
ለማቆምም አለመቻሉ ግን በውስጤ ከፍተኛ
ቁጭት ፈጥሮብኛል፡፡ አንዳንዴ ተመልሼ
ተመርጬ ልስራ የምለው ከዚህ ቁጭት አንፃር
ነውና እግዚአብሔር ለዚህ ያብቃን፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ፊፋ በቅርቡ ላከ
በተባለው ደብዳቤ የፊፋ አጣሪ ኮሚቴ ማርች
12 ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ይገልፃል፡
፡ በሌላ ወገን ደግም በተለይ እጩ ተወዳዳሪ
“ፊፋ ደብዳቤ አላካም፤ አንሰሪንግ ማሸን ነው”
በማለት ደብዳቤውን ያጣጥላሉ፡፡ እርስዎስ
ደብዳቤና አንሰሪንግ ማሸን መለየት አይችሉም፤
በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
አቶ ጁነዲን፡- እኔ በቢዝነስ ላይ ወይም
በሐረር ቢራ ስራ አስኪያጅነት ከ20 አመት
በላይ አገልግያለሁ፡፡ ከ30 አገራት በላይ
ተመላልሼ ያየሁት ወደ ፉትቦሉ ሳልገባ ነው፡፡
በዚህ ስራዬ የተነሳም ለቴክኖሎጂ በጣም ቅርብ
ነኝ፤ በስልክ፣ በፋክስ፣ በኢንተርኔት፣ በኢሚል
የተለያዩ ስብራዎችንም የማከናውን ሰው ነኝ፡
፡ ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ በጣም ቅርብ ሆኜ
እንዴት አንሰሪንግ ማሸንና ደብዳቤን መለየት
የሚያቅተኝ ይመስልሃል? ሰዎችም በዚህ
ደረጃ ወርደው ለምን ደረቅ ውሸት እንደሚዋሹ
አላውቅም፡፡ ማንን ለማስደሰት ምን ትርፍ
ለማግኘት ታስቦ እንደሆነም አይገባኝም፡፡ በጣም
የሚገርመው ትዝብት ላይ የወደቁት እኮ እነሱ
ናቸው፤ እንደዛሬው አንሰሪንግ ማሽን ተብሎ
ተዋሽቶ እንደነገ ደብዳቤ መጣ፤ ሰው እንዴት
24 ሰአት ለማይሞላ ጊዜ ይዋሻል?
ሀትሪክ፡- ታዲያ ከምን መነሻነት ደብዳቤ
ሳይሆን አንሰሪንግ ማሽን ነው የሚለው ትችት
የተሰነዘረ ይመስልዎታል?
አቶ ጁነዲን፡- በቃ ይሄ ልላ ትርጉም
የለውም፤ ሌላውን በማንቋሸሽ ራስን ከፍ
ለማድረግ ብቻ ነው፤ ይሄ ደግሞ ጊዜው ያለፈበት
አካሄድ ነው፡፡ ህብረተሰቡ ይሄ አይጠፋውም፤
በቀላሉ ነው የሚረዳው፡፡ ሌላውን ዝቅ በማድረግ
ለሌላው ያልሆነ ስም በመስጠት ራስን ከፍ አድርጎ
ወደቦታው ለምምጣት ካለ ጉጉት የመነጨም ነው፡
፡ ይሄ ደግሞ ለፉትቦሉም፣ ለባለቤቱም ለራሱ
የማይጠቅም አቅም የሌለው ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ከመጣው ደብዳቤ በፊት
ፊፋ ደብዳቤ እንደላከና አጣሪ ኮሚቴ እንደማይልክ
ምርጫውም በፌዴሬሽኑ መተዳደሪይ ደንብ
መሠረት እንዲካሄድ የፊፋ የምርጫ ምድብ
በቀጣይ ምርጫ እንዲፀድቅ ብሎ መወሰኑ
የተለያዩ ሚዲያዎችና እጩ ተወዳዳሪ ግለሰቦች
በተደጋጋሚ ሲገልፁ ነበር፡፡ ፊፋ አሁን አጣሪ
ኮሚቴ እልካለሁ ብሎ ያንን ደብዳቤ የሚቀለብስ
ውሳኔ እንዴት ሊልክ ቻለ?
አቶ ጁነዲን፡- ምን መሰለህ ከፊፋ
የሚመጣውን ደብዳቤ በተመለከተ ሚዲያውም
አንዳንድ እጩ ተወዳዳሪዎችን በራሳቸው
ስሜት ነው የሚተረጉምት፡፡ አንድ ደብዳቤ
ከፊፋ ይመጣል አይደል እጩ ተወዳዳሪውም
ሚዲያውም በራሱ መንገድ እንዲያመቸው አድርጎ
ነው የሚያናፍሰው፡፡ ከፊፋ የሚመጣው ተመሳሳይ
ደብዳቤ እንደየሰዉ ፍላጎት እየተተረጎመ ነው
ህዝቡ ሲወናበድ የነበረው፡፡ ዝም ብሎ ውዥንብር
ነው፡፡ አሁን ፊፋ አጣሪ ኮሚቴ እልካለሁ
ያለውንስ በአደባባይ አንሰሪንግ ማሸን ነው ተብሎ
የለም እንዴ?
ሀትሪክ፡- ፊፋ አጣሪ ኮሚቴ መላኩን
በተመለከተ እናንተ ተመራጮች እንዳልወደዳችሁት
ይሰማል የአጣሪ ኮሚቴ መምጣት ለምን ስጋት
ይፈጥርባችኋል?
አቶ ጁነዲን፡- እኔ ምርጫው በየጊዜው
መራዘሙ መቆየቱን ጥሩ ነው አልልም፤ማጣራት
ግን ተገቢ ነው የሚል እምነቱ ነው ያለኝ፡፡ እኔ
አንድ የማይገባኝ ማጣራት ለምን ይፈራል?
ማጣራትስ ማንን ይጎዳል? ይሄን አላውቅም።
አሁን ተማሪ በሙሉ 12ኛ ክፍል ስለደረሰ ብቻ
እንደለ ወደ ዩኒቨርሲቲ አይገባም፤ ወደዩኒቨርሲቲ
ለመግባት ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን
መስፈርትና ፈተናውን ማለፍ ያስፈልጋል፡
፡ በዚህ ማጣራት ውስጥ ሳታልፍ ዩኒቨርስቲ
መግባት የማይታሰብ ነው፡፡ ወደ ፉትቦሉ ጋር
ስትመጣም የተቀመጠ መስፈርት አለ፤ ህግ አለ፤
በዚህ የምርጫ መነፃር ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ከዚህ
ውጭ ዝም ብለህ ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ ብቻ
ሉአላዊ አገር ምናምን እያልክ የማይገቡ ነገሮች
ስለተናገርክ ብቻ መስፈርቱን ሳታሟላ አትገባም፡
፡ ሉአላዊ አገር ማለት ለምን አስፈለገ? ይሄንን
ስልህ አገራችንን አናክብር ነፃነታችንንም አንወድም
ማለት አይደለም፡፡ አለም በሙሉ የሰለጠኑ አገሮች
ከታላቋ አሜሪካ እስከ ታላቋ ሩሲያ ድረስ በፊፋ
ህግ በኢንተርናሽናል ሕጎች ነው የሚመሩት፡፡
እኛ ለብቻችን እንደ ደሴት ተነጥለን የተቀመጥን
አይደለንም፡፡ ስለዚህ ወለም ዘለም ማለት ወይም
በንግግር ብዛት የሚጨመር የሚቀነስ ነገር የለም፡
፡ እንደማንኛውም አገር እንደሰለጠነ ህብረተሰብ
በህጉ ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ጉባኤው ካርድ ይሰጣል
“እፈልግሃለሁ ስራልኝ” ካለ መስራት ነው፡፡ “አይ
አልፈልግህም ዞር በል” ካለ አመስግኖ ለሚሰራው
ሰው መልካም ተመኝቶ መሄድ ነው፤ ከዚህ ውጪ
ምን ይስፈልጋል?
ሀትሪክ፡- አቶ ጁኒዲን ምርጫው
እንዲራዘም አጥብቆ ይፈልጋል፤ የፌዴሬሽኑን
ፅ/ቤት ለቆ መውጣት አይፈልግም በሚል
ለምርጫው መራዘም ተጠያቂ ነው በማለት
ጣታቸውን ወደእርስዎ የሚቀስሩ አሉ፤ ይሄንን
ወቀሳ ይቀበሉታል?
አቶ ጁነዲን፡- እንደዚህ በደፈናው ከመናገር
እስኪ አንድ ማስረጃ ይቅረብ፤ መውጪያ በር
የተዘገባቸው ሰዎች ፈልስፈው የሚያወሩት ወሬ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- እንደዚህ አይነት አስተያየት
የሚሰጡ ወገኖች እንደማስረጃ የሚያስቀምጡት
ጁነዲን በጎን ዳብደቤ እየፃፈ የተሳሰተ መረጃ
እየሰጠ ምርጫው እንዲጓተት አድርጓል ነው
የሚሉት፡፡ ይሄንንስ ይቀበላሉ?
አቶ ጁነዲን፡- በፍፁም ሐሰት ነው፤
እስቲ እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ደረቅ
ውሸት እንደሚዋሹ ከመጀመሪያው እንይ፡፡
መጀመሪያ ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርት አየ፤
በሚቀጥለው ቀን ምርጫ አስፈፃሚው ምረጡ
ሲባል “እንመርጣለን፤ አንመርጥም” የሚል
ለሁለት የተከፈለ ውዝግብ ተነሳ፡፡ በቀጣይ ያለ
ምርጫ አስፈፃሚ ምርጫ ማከናወን አትችሉም
የሚል ደብዳቤ ከፊፋ መጣ፡፡ እንደገና ስብሰባ
ተጠራ ምርጫ አስፈፃሚ ያስፈልጋል ተባለ
አንድ ወር ተኩል እንዲራዘም ተደረገ፡፡ ከዚህ
በኋላ ደግሞ ለምርጫ የተያዘው ቀን የፈረንጆች
ገና ላይ ስለዋለ የፊፋና የካፍ ሰዎች ለመምጣት
ይቸገራሉ ተባለ፤ በሳምንቱ እንዳይሆን ደግሞ
የኢትዮጰያ ገና ሆነ፤ እንዴት ለፈረንጆች
ገና አራዝመን በራሳችን የገና በዓል ላይ
እናደርጋለን? ተብሎ ወደ ጃንዋሪ 30 ሄደ፡
፡ ያኔ ደግሞ የአስመራጭ ኮማቴው ሰብሳቢ
በአካሄዱ ላይ አንዳንድ ቅሬታዎች አሉኝ
ብለው ለፊፋ ደብዳቤ ፃፉ፡፡ ፊፋም የእሳቸውን
ደብዳቤ በመንተራስ ጉዳዩ እኛንም ያሳስበናል፤
በአራት ጉዳዮች ምክንያት ብለው ከፌብሪዋሪ 4
በኋላ ነው የሚሆነው የሚል ነገር ተቀመጠ፡
፡ በማን? በፊፋ፤ ማን በፃፈው? የአስመራጭ
ኮሚቴው ሰብሳቢ፡፡ ከፌብሪዋሪ 4 በኋላ
እንነጋገር ሲባል እኛ ስለቸኮልን ቶሎ አድርጉ
ስለምንባል ቶሎ ማድረግም ስላለብን ለምን ቀን
አስቀምጥን ፊፋን አንገፋውም ብለን ማርች 3
ቀን በማለት እኛም፣ ስራ አስፈፃሚውም፣ ፅ/
ቤቱም፣ ምርጫ አስፈፃሚውም ተስማምተን
ቀጠልን፡፡ ነገር ግን ከፊፋ መልስ ጠፋ፡፡ አሁን
በዚህ ጊዜ ዝም ብለን መቀመጥ ስለሌለብን
እኔ ደብዳቤ ፃፍኩ፡፡ ደብዳቤ የፃፍኩት ግን
ምርጫ እናድርግ የሚል አይደለም፡፡ እስካሁን
ድረስ ፊፋ በምርጫችን ላይ እንዲገኝ እንፈልግ
ነበረ፡፡ ነገር ግን ካፍ ለላክነው ደብዳቤ ምላሽ
ሲሰጥ ፊፋ አልመለሰልንም፤ ይሄ ነገር ለኋላ
ህጋዊነት አሳስቦኛል፤ ምርጫው ከዚህ ውጪ
ተደርጎ አንዱ አሸንፎ ሌላኛው የተሸነፈው
ክስ በመመስረት አገራችን ጊዜዋን በጭቅጭቅ
ማሳለፍ ስለሌለባት ሁኔታው በጣም አሳስቦኛል፡
፡ አንዳንዶች ከፍተኛ ግፍት እያደረጋችሁ
ምርጫውን ቶሎ እናድርግ ስለምትሉ ኃላፊነቱን
ውሰዱ እና በማርች 3 እናድርግ ብዬ ፃፍኩ፡
፡ እነሱም ሁኔታውን ተረድተው ተቀበሉ፡
፡ ፊፋም ደብዳቤ ፃፈ፤ “ቀኑን ከእኔ ጋር
ሳትነጋገሩ ለምን ወሰናችሁ? የማጣራው ነገር
አለ” አለን፡፡ እውነታው ይሄ ነው፤ ታዲይ የእኔ
ችግር እዚህ ውስጥ የቱ ጋ ነው? የፈጠርኩት
ስህተትስ ምንድነው? ያለ ማስረጃ ዝም ብለው
ሆኖ ይሆናል፣ ደብዳቤ ፅፎ ይሆናል፣ ስልክ
ደውሎ ይሆናል፣ ከሚል መላ ምትና ስጋት
የመነጨ የሚሰነዘር ከእውነት የራቀ አስተያየት
እንደሆነ ህብረተሰቡ እንዲረዳው እፈልጋለው፡
፡ ህብረተሰባችንንም፣ ራስንም መዋሸት
አያስፈልግም፡፡ የቸኮለው ክፍል ህጋዊነት መሸሽ
ነው የመረጠው፡፡ ለማንኛውም አሁን ቀኑ
የቀረበ ይመስላል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- እርስዎ ጋር ያለው ሀቅ ይሄ
ከሆነ ታዲያ አንድ እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ
“አቶ ጁነዲን ከምርጫው ውጣልኝ ብሎ አማላጅ
ልኮብኛል” የሚል አስተያየት ሊሰነዝርብዎ የቻለ
ይመስልዎታል?
አቶ ጁነዲን፡- የሚገርምህ ሰው ስለምርጫ
ያስባል፤ እኔ ግን ስልጣኔን ስለማራዘም፣
ስለመመረጥ ሳይሆን የምጨነቀውና የማስበው
ሀገራችን የቅጣት ሰለባ እንዳትሆን ነው፡፡
በመሬት ላይ ያለው የምንሰራው ስራ፣ ውድድሩ
ሁሉ እንዲቀጥል እፈለጋለሁ፡፡ ሕጋዊነት
ተላበሶ ጊዜው ሳይዘገይ ምርጫው እንዲፈፀምም
እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ አራት ዓመት
ያልጠቀመኝ ሁለት ወር ሶስት ወር ቢራዘም
ምን ሊጠቅመኝ ነው ስለመራዘሙ እንቅልፍ
የማጣው?
ሀትሪክ፡- ይህንን ጥያቄ ደጋግሜ ያነሳ
ሁሎት “ጁነዲን በስልጣን ላይ ለመቆየት
ያለው ጉጉት ከምርጫው እንድወጣ አማላጅ
ሁሉ ልኮብኛል” በማለት አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ
በአንድ ኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ትችት ሰንዝ
ረውቦታል፡፡ እውነት ለስልጣን ሲሉ አማላጅ
ልከዋል? የሚለውን ማወቅ ፈልጌ ነው፡፡
አቶ ጁነዲን፡- እኔ ይህንን ስላልኩ ሰው
ይወጣል ብለህ ነው? ደግሞስ ተወዳዳሪው አምስት
ነው፤ አንድ ሰው ስለወጣልኝ እመረጣለሁ ብዬ
የማስብስ የዋህ ሰው እመስልሃለሁ? ደግሞም
ቢባልም እኮ በሰለጠነው ዓለም የኃይል
ሚዛኑን አይተው “ልቀቅልኝ ልልቀቅልህ”
መባባል ያለ እኮ ነው፡፡ በከፍተኛ ፖለቲካ
ውስጥም ይህ ይታያል፤ ሪዛይን እስከማድረግ
የሚደረስበት ሁኔታም አለ፤ እኔ እራሴም ከዚህ
በፊት በአንዳንድ ከፍተኛ ምርጫዎች ሪዛይን
ያደረኩበት ጊዜም አለ፡፡ ወደ እውነቱ ስትመጣ
ግን እኔ ከምርጫው ውጣልኝ ብዬ ለማንኛውም
ዕጩ ተወዳዳሪ የላኩት ሽማግሌም አማላጅም
የለም፡፡ ለምን እንደዚህ ብለው ያውም በሚዲያ
እንደዋሹ አይገባኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ፊፋ የሚልከው አጣሪ ኮሚቴ
ምን ውጤትን ያመጣል የሚል ቅድመ ግምት
አልዎት?
አቶ ጁነዲን፡- እኔ እውነት ለመናገር ፊፋ
ነገሮች ሁሉ በሕጉ መሠረት መሄዳቸውን
ያጣራል ብዬ አምናለሁ፤ እኔ እራሴ እጩ
ስለሆንኩ ብዙ ዝርዝር ውስጥ ባልገባም ፊፋ
የሚልከውን አጣሪ ኮሚቴ ተከትሎ አቅጣጫ
ያስቀምጣል፣ ምርጫውን በሰላም እንድንጨርስ
መንገዱን ያሳያል፣ የተረጋጋ ምርጫ እንዲካሄድ
አስተዋፅኦ ያደርጋል ብዬም አስባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ፊፋ የምርጫ ሕጌ መጣስ
የለበትም በሚል ያስቀመጣቸው ነገሮች አሉ፡፡
ከዚህ ውስጥ በአስመራጭ ኮሚቴነት ማገልገል፣
የምርጫ መስፈርትን ሳያሟሉ ዕጩ ተወዳዳሪ
ሆነው መቅረብም ይጠቀሳል፡፡ ፊፋ ይሄን ቢልም
አሁንም ሕግ ጥሰው በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ
የተቀመጡ፣ በዕጩነት የሚወዳደሩ አሉ፡፡ ፊፋ
አጣራለሁ እያለ ሕግ የጣሱ ሰዎች እዚህ ቦታ
ላይ መቀመጣቸው ምን ስሜት ይሰጥዎታል?
አቶ ጁነዲን፡- እኔ እራሴ አንደኛው
ተወዳዳሪ ስለሆንኩ አሁንም እዚህ ውስጥ
ባልገባ እመርጣለሁ፡፡ በአጠቃላይ በምርጫው
ዙሪያ እንጂ ውስጡ ባልገባ እና እራሱ ፊፋ
በማጣሪያው አጣርቶ መልስ ቢሰጥበት መልካም
ነው ማለቱ ይቀለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ከእርስዎ ጋር በስራ አስፈፃሚ
ኮሚቴነት የሚሰሩ ወገኖች “ምርጫው የካቲት
23 ካልተካሄደ እራሴን አገላለሁ” በማለት
በሚዲያ ሲናገሩ ተሰምቷል፤ እንዲህ አይነት
ድምዳሜ ላይ መድረስ የተፈለገው ለምን
ይመስልዎታል? የካቲት 23 በማለፉ እነዚህ
ሰዎች ራሳቸው ከምርጫ ውጪ አድርገዋል?
አቶ ጁነዲን፡- ስለሱ የማውቀው ነገር
የለም፤ ምናልባት ምርጫው እንዳይራዘም
ከመጓጓት ይሆናል ብለን በበጎ ጎኑ ካየነው
አሊያም ደግሞ ግለሰቦችን ለማስደሰት
ከግለሰቦች ጋር ለማጨብጨብ ታስቦ ይሆናል፡
፡ ደግሞም በሚዲያ እለቃለሁ ብሎ ከመፎከርና
ጉራ ከመንፋት መልቀቅ ነው የሚመረጠው፡፡
እለቃለው የሚል ካለ ቃሉን ጠብቆ መልቀቅ
ነው፡፡ እለቃለሁ ብሎ ካለቀቀ ይሄ ሁሉ ባዶ
ወሬ ወይም ዝም ብሎ ጉራ ድንፋታ ሆኖ
ይቀራል፡፡
ሀትሪክ፡- የ2020 የቻን የአፍሪካ
ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ትልቁን
ሚና ከተወጡ አመራሮች እርስዎ በዋናነት
ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖች ግን የቻን
አዘጋጅ መሆናችንን የዓለም ዋንጫም ወደ
ኢትዮጵያ መምጣቱ ትርጉም የለውም በማለት
ያጣጥሉታል፡፡ እርስዎስ ለሀገራችን የሚሰጠው
ጥቅም ምንድነው ይላሉ?
አቶ ጁነዲን፡- እንደዚህ የሚጣጣሉት ሰዎች
ለምርጫው ሲባል እና እራስን ከፍ ለማድረግ
ሲሉ ሌላ የሰራውን ለማንኳሰስ የሚደረግ
አጉል ባህሪ ነው፡፡ አፍሪካ ሁሉ ለማዘጋጀት
እየተሽቀዳደመ ባለበት፣ የነገ እግር ኳስ
ተስፋዎች የሚታዩበት መድረክ እየሆነ፣ ለሀገር
ኢኮኖሚ የራሱን አስተዋፅኦ ጥሎ የሚያልፍ
እንደሆነ እየታወቀ፣ የራሳችንን መልካም ገፅታ
ለሌላው ዓለም የምናስተዋውቅበት የአህጉሪቱ
ሁለተኛው ሻምፒዮና መሆኑ እየታወቀ
ማጣጣሉ ለእኔ የጤንነኝነት ምልክት አይደለም፡
፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዓለም ዋንጫ በዚህ ለምን
ያልፋል? ሲባልም ሰምተናል፡፡ ይሄ ያሳዝናልም
ያስደነግጣልም፡፡ የዓለም ዋንጫ የዞረባቸውን
ሀገሮች የሚያውቅ አቀባበሉም እንዴት
እንደነበር መረጃው ያለው ሰው እንደዚህ
አይነት ስህተት አይሳሳትም፡፡ የአለም ዋንጫ
ከዞረባቸው የአፍሪካ አስር አገሮች አንዱ ሆኖ
መመረጥ ቀላል አይደለምና ይሄን የሚያወሩት
ሰዎች ዝም ብለው ሰው የሰራውን መልካም
ስራ ለማጣጣልና እና ለማሳነስ የከፈቱት ተራ
ዘመቻ ነው፡፡ በአጠቃለይ ግን የግለሰቦችን
አሉባልታዎች ትተን ስለሀገር ማሰብ ነው
የሚጠቅመው፡፡
ሀትሪክ፡- ቀጣዩን የቻን ውድድር ኢትዮጵያ
ስለማዘጋጀቷ ስጋት ያላቸው ወገኖች አሉ፤
እርስዎስ ይሄን ስጋት ይጋራሉ?
አቶ ጁነዲን፡- አትጠራጠር ይዘጋጃል፤
እኔ በዚህ በኩል ስጋት የለብኝም፡፡ እንደው
አንዳንዶች ዝም ብለው ጭንቀት ሀገር ላይ
ለመጫን ካልሆነ በስተቀር ገና ሁለት ዓመት
እየቀረ እንደዚህ አይነት መልካም ያልሆነ
ምኞት መመኘት ጤነኝነትም አይመስለኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ለፕሬዝዳንትነት ከሚወዳደሩት
ዕጩዎች ውስጥ አንዱ እርስዎ ኖት፤ በቀጣይ
ምርጫው ሲካሄድ ከፌዴሬሽኑ ወንበር
የማያስነሳ፣ በስልጣንዎ ላይ የሚያቆይ ድምፅ
አገኛለሁ ብለው ያስባሉ? የሚለው የመለያያ
ጥያቄዬ ቢሆንስ?
አቶ ጁነዲን፡- ካርዱን በትክክል እግር
ኳሱን ለሚመራ ሰው በትክክል የሚሰጥ ካለ
የብዙዎችን ይሁንታ አግኝቼ እመረጣለሁ
ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ከእግር
ኳሳዊ መንፈስ በራቀ በክልል ስሜት፣ አንዳንድ
አላግባብ በሚሰሩ ስራዎች ከሆነ አላውቅም፡፡
በእርግጥ አሁን ብዙ ነገር እየተረዳ የመጣበት
ከበፊቱ ችኩልነት ከስሜታዊነት የፀዱ ነገሮች
እየተፈጠሩ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለውና
እውነቱን ለመናገር ፉትቦሉን ማዕከል ከተደረገ
በዚህ በኩል ብዙም አልሰጋም፡፡ ምክንያቱም
በእጄ ላይ ብዙ ነገሮች አሉ፤ እኔ ከሌሎች
በተለየ መስመር ላይ ነው ያለሁት፡፡ ለነገሮች
እንግዳ እና አዲስም አልሆንም፡፡ ልምድ እና
ትምህርትም አግኝቼበታለሁ፡፡ በዚያ ላይ
ትኩስ ነኝ፡፡ ከካፍ፣ ከፊፋ ሰዎች ጋር ጤናማ
የስራ ግንኙነት ፈጥሬያለሁ፡፡ የእውቀት እና
የልምምድ ሽግግርም አግኝቼያለሁ፡፡ አሁን
ቻንን አምጥቼያለሁ፤ ቀጣይ አፍሪካ ዋንጫም
አስባለሁ፡፡ ለሀገሬ የሚጠቅሙ የጀመርኳቸውን
ብዙ ስራዎች መጨረስም እፈልጋለሁ፡፡ ጠቅላላ
ጉባኤው ይሄ ይጠፋቸዋል ብዬ ስለማላስብ
እንዲሁም ሰዎች የጀመሩትን ስራ እንዲጨርሱ
እንጂ ስራዎች እንደ አዲስ እንዲጀመሩ
ይፈልጋሉ ብዬ ስለማላስብ ድምፃቸውን
ይሰስታሉ ብዬ አላስብም፡፡