በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሀ እሚወዳደረው እክሱም ከተማ ከዋና አሰልጣኙ ሲሳይ አብርሃም ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ ማን ይረከባል እሚለው ጥያቄ በዛሬው ቀን ምላሽ አጊንቷል። ከመቐለ ከተማ ጋር ባለመግባባት የተለያየው አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን በኃላፊነት ሾሟል። መቐለ ከተማን ወደ ፕሪሜየርሊግ በማሳለፍ ደማቅ ታሪክ ያጻፈ አሰልጣኝ ሲሆን አክሱም ከተማ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እያስመዘገበ እሚገኘውን ዝቅተኛ ውጤት ለማስተካከል እምነት ጥሎባቸው ወደ ቡድኑ ሊያመጣቸው እንደቻለ ተገልጿል።
አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ከዚህ በፊት በአሰልጣኝነት ወልዋሎ አዲግራት ፤ደደቢትና መቐለ ከተማን ማሰልጠን ችሏል።
አክሱም ከተማ በ10 ጨዋታዎች በ 12ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ደረጃ 10ኛ ላይ ተቀምጧል።