በመጀመሪያው ዙር የፕርሚየር ሊጉ የውድድር አጋማሽ ላይ ከተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ ጋር ስሙ በስፋት ሲነሳ የቆየው አዳማ ከተማ የማልያ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት የፊታችን ሀሙስ ይፈፅማል ::
አዳማ ከተማ ስምምነቱን ከዩናይትድ ቢቭሬጅ ጋር የሚፈፅም ሲሆን ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ እንደቻለችው የአምስት አመት የስፖንሰርሺፕ እንደሚፈፀም ለማወቅ ተችሏል ::
ክለቡ ስምምነቱን የፊታችን ሀሙስ በአዳማ ሮቢ ሆቴል የሚድያ አካላት በተገኙበት ስምምነቱን የሚፈፅሙ ሲሆን ለመላው የሚድያ አካልም በተላከው መረጃ መሰረት በቦታው እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል ::