የ2017 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የፊታችን ቅዳሜ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥቅምት 28 እና ህዳር 5 በደርሶ መልስ በሚደረጉት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
የግብፁን አል አህሊ እና የሞሮኮውን ዋይዳድ ካዛብላንካን በደርሶ መልስ ያገናኛል፡፡ በዚህ የፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያው ቅዳሜ ጥቅምት 28 በግብፅ በቦንግ አሌክሳንድሪያ ሲደረግ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሀል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ጨዋታውን እንዲመራ በካፍ ተመርጧል።
ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ወዮሳ የ2017 ቶታል የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 2 መክፈቻ ጨዋታ እንዲመራ በካፍ መመረጡ እሚታወስ ነው ፡፡
ጨዋታው በፍራንስቪል ከተማ በሚገኘው ፍራንስቪል ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ባምላክ በካፍ የዳኞች ደረጃ ኤሊት ኤ ላይ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ አርቢትር ነው
ከዳጅነት በተጨማሪ ባምላክ ተሰማ በሶሲዬሎጂ ትምህርት ዘረፍ በአለርት ሆስፒታል በማህበራዊ ሰራተኛ (social worker) ሆኖ በመስራት ላይ የገኛል