ኢትዮጵያ ሁለት ስታድየሙዎቻ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ በካፍ ፍቃድ ተሰጣቸው
ከቀናት በፊት እንጋፋውን የእዲስ እበባ ስታድየም ምንም እይነት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች እንዳያስተናግድ የከለከለው ካፍ፤ለሁለቱም ትግራይና ባህርዳር ስታድየም ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ ገድብ ያለው ፍቃድ ሰጠ።
ዛሬ ካፍ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በፈረንጆች እቆጣጠር እስከ ጥቅምት 8 ድረስ ገደብ ያለው ፍቃድ እንደተሰጣቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት ኢሳያስ ጅራ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ እያይዘውም
ምንም እንካን ፈቃዱ ቢሰጥም አሁንም ግን መሰራት ያለባቸው ስራዋች እንዳሉ እስገንዝበዋል።በተጨማሪም አቶ ኢሳያስ ጂራ የሚመለከታቸው የክልልና የፌደራል የመንግስት አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በዚህም መሰረት በእፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን ሚወክሉት መቐለ 70 እንደርታና ፋሲል ከተማ ጨዋታቸውን በትግራይና በባህርዳር ስታድየም ያደርጋሉ።