ኢትዮጵያ ቡና እንዳለ ደባልቄን ባህርዳር ከተማ አስፈረመ
ካሳዬ አራጌን በይፋ በዋና አሰልጣኝነት ያስተዋወቁት ኢትዮጵያ ቡና የወቅቱ 12ተኛ ፈራሚያቸውን እንዳለ ደባልቄ ከባህርዳር ከተማ አድርገዋል።
ያለፈው የውድድር ዓመት በባህርዳር ከተማ በቂ የመሰለፍ እድል ያላገኘው አንዳለ ደባልቄ በ2010 ጅማ አባጅፋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት ችሏል።ከዚህ በፊት በአጥቂ ቦታ ሠይፈ ዛኪርን ያስፈረሙት ቡናዎች አንዳለ ደባልቄን ማስፈረማቸው በዛ ቦታ ያላቸውን አማራጭ ሊያሰፋላቸው አንደሚችል ይገመታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መስከረም 5 አዲስ አበባ ላይ ሚጀምሩ ይሆናል።