ኢትዮጵያ ቡና በይፋዊ ገፁ በተጫዋቾች ዙሪያ ይሄን አስፍሯል፡፡
———————————-
“የኢትጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የጂማ አባቡናው የተከላካይ አማካኝ ክሪዚስቶም ንታምቢ ለማስፈረም ተስማማ፡፡ የፍረሚያውን በቅርቡ አጠናቆ ወደ ሃዋሳ ለቅድመ ዝግጅተ እንደሚያቀና ይጠበቃል፡፡በቅረቡ ከአዳማ ከነማ በነበረው ውዝግብ ችግሩ ተፈቶ ተጨዋቹ የክለባችን መሆኑን ተረጋግጧል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ 2010 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፕሪሚርሊግ ቅድመ ዝግጅት ከመጀመሩ በፊት የተጨዋቾችን ዝውውር በማካሄድላይ ሲሆን አስከ አሁንም
- ማሰታውቂያ -
ቶመስ ስምረቱን ከ ወላይታ ዲቻ ——-ተከላካይ
ወንደሰን እሸቱን ከወላይታ ዲቻ———ግብ ጠባቂ
አለማየሁ ሙለታ ከአዲስ አበባ ከተማ———የግራ ተከላካይ
ክሪዚሰቶም ንታምቢ ከጅማ አባቡና—————የተከላካይ አማካኝ
ሮቤል አስራት ከጅማ ከነማ———————የግራ ተከላካይ
አብዱል ሰላም አማን ወልዋሎ —————————የቀኝ ተከላካይ
አስራት ቶንጆ ከጅማ ከነማ————————– አማካኝ
ድንቅነህ ከበደ ከአንበሪቾ ከነማ—————-አጥቂ
በረከት አድማሱ ከአንበሪቾ ከነማ,–,————–የተከላካይ አማካኝ
ትግስቱ አበራ ከሀላባ ከነማ ———————የመሃል ተከላይካይ
የፈረሙ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ቦታዎች ላይ አሰልጣኙ ክፍተት አሉቢኝ ባሉበት እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል፡፡ ተጨዋቾቹ የኩፐር ቴስት ወይም የአካል ብቃት ምዘና ያአደርገው ሲሆን ቅዳሜ ወደ አዋሳ ለቅድመ ዝግጅት እንደሚያቀኑ ይጠበቃል ፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ”