በክረምቱ በርካታ ዝውውርን ያከናወኑት ኢትዮጵያ ቡናዎች ፍቅረየሱስ ተክለብርሃንን የግላቸው አድርገዋል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የሀዋሳ የየመሃል ሜዳ ተጨዋች ፍቅረየሱስ በክረምቱ መከላከያን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም መከላከያ በፕሪምየር ሊጉ ማይሳተፍ መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ ለክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት የካሳዬ አራጌ ቡድንን ተቀላቅሏል። ኳስ ቁጥጥር ላይ መሰረት ያደረገው የካሳዬ አጨዋወትን ለመተግበር ዋነኛ የሆነውን የመሀል ሜዳቸውን እያጠናከሩ ሚገኙት ቡናዎች ከዚህ ቀደም አለም አንተካሳ(ማርዮ)፣ታፈሰ ሰለሞን፣አዲስ ፍስሀ፣ ማስፈረማቸው ሚታወስ ነው።
በዝዋይ በመከተም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማከናወን ላይ ሚገኙት ኢትዮጵያ ቡና በሚቀጥሉት ቀናት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናሉ።