ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የኣፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተመረጠ ካፍ ሚያዘጋጃቸውን ውድድሮች በከፍተኛ ብቃት መምራቱን የቀጠለው ባምላክ ተሰማ በኣፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ በግብጹ ክለብ ኣልኣህሊ እና በኣልጀርያው ኤል ሴቲፍ ሚካሄደውን የግማሽ ፍፃሜ ኣንደኛ ዙር ጨዋታን በመሃል ሜዳ መሪነት ይመራል።በሩብ ፍፃሜ በውጥረት የተሞላውን የኤስፔራንስና ኤትዋልደ ሳህል ጨዋታን በብቃት የመራው ባምላክ ከሁለት ሳምንት በኃላ በኣፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዳካር ላይ ሚካሄደውን የሴኔጋል ና ሱዳን ጨዋታ እንደሚመራ ይታወቃል።