እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ፡-
ለመሆኑ ሀትሪክ የነገው ጋዜጣዋ ላይ ምን ምን ጉዳዮችን አንስታ ትወጣ ይሆን?
ሀትሪክን ነገ ረቡዕ በገበያ ላይ ሲያገኟት ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ከምታስነብቦት የሀገር ውስጥ ዘገባዎቿ መካከል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት እና የቦርድ ሊቀመንበር ለሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀል በሀገራችን ወቅታዊ የእግር ኳስ ስፖርት ክንውኖች እና የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ የውድድር ፎርማት እና ከክለባቸው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እንደዚሁም ሰሞኑን በሸራተን አዲስ ተካሂዶ ስለነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉባኤ ዙሪያ ሰፋ ያለ እና ድፍረት የተቀላቀለበትን ጥያቄዎች ለእሳቸው አቅርቦላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትም ሌላ የምታስነብቦት ዘገባ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የሸገር ደርቢ ጨዋታ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይም ከኢትዮጵያ ቡና እያሱ ታምሩን፣ ከቅ/ጊዮርጊስ ሄኖክ አዱኛን በማናገር እነሱም ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
በደርቢው ጨዋታ ዙሪያ ሁለቱ ተጨዋቾች ምን ብለው ይሆን?
“የሊግ ዋንጫውን የማንሳት ዕድላችን ጠባብ ቢሆንም ሸገር ደርቢውን እናሸንፋለን”
እያሱ ታምሩ /ኢትዮጵያ ቡና/
“ቅ/ጊዮርጊስ ዋንጫ ማንሳቱ ላይ ተስፋ አይቆርጥም፤ የደርቢ ጨዋታውንም ያሸንፋል”
ሄኖክ አዱኛ /ቅ/ጊዮርጊስ/
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌሎች መረጃዎም አላት፡፡
ሀትሪክ በነገው እትም በባህር ማዶም ለእናንተ ይዛሎት የምትቀርበው ዘገባ ነገ ማታ በኑካምፕ በሚከናወነው እና በጉጉት በሚጠበቀው የባርሴሎና እና የሊቨርፑል የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት በቀሩት ወሳኞቹ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ እና ሌሎችን አካተን የሚወዱትን ዘገባ ታቀርቦሎታለች፡፡
ሀትሪክ የእናንተው ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡