ሻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታ የክረምቱ 3ተኛ ፈራሚያቸውን ኦኪኪ ኦፎላቢን ከጅማ አባጅፋር አድርገዋል።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ካልተሳካ የግብፅ ቆይታ በኃላ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀለው ናይጀርያዊው አጥቂ ኦኪኪ በ2010 አብሮት ከሰራው ገብረመድህን ሃይለ ጋር በድጋሚ ሊገናኝ ችሏል።
ብዙ ውላቸውን ያጠናቀቁ ነባር ተጨዋቾች ያሉት መቐለ 70 እንደርታ በሚቀጥሉት ቀናት ውላቸውን ሊያራዝም እንደሚችል ይገመታል።በተያያዘ ዜና ባለፋት የመልቀቅያ ደብዳቤ አስገብተው የነበሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ከክለቡ ጋር የመቀጠል አድላቸው ሰፊ ነው።